2017-01-11 17:01:00

ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ፥ የሃይማኖቶች ልዩነት የሚፈጥረው አለ መግባባት እግዚአብሔርን በመካድ የሚወገድ አይደለም


እ.ኤ.አ. እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. የሚዘልቀው በፓሪስ  የመላ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ኅብረትና በኤውሮጳ የሚገኙት የኦርቶዶክስ አቢያተ ክርስቲያን አምስተኛው የጋራው ጉባኤ እ.ኤ.አ. ጥሪ 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የፓሪስ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል አንድረ ቪንግት ትሮይስ የመላ ደቡብ ኤውሮጳ ለቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ቡፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ኤዛርቆስ በኢጣሊያ ሚጥሮፖሊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ  ገናዲዮ ዘሳሲማንና እንዲሁም የኤስቶርጎምና ፑዳፐስት ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኤርዶ ባቀረቡት የጉባኤ አስጀማሪ ንግግር መከፈቱ ሲር የዜና አገልግሎት የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ኅብረት ይፋዊ ድረ ገጽ ጠቅሶ የገለጠ ሲሆን፡ ብፁዕ ካርዲናል ኤርዶ ባስደመጡት ንግግር፥

የሃይማኖ ገጠመኝ ወይንም ተመክሮ ማፈን መፍትሄ አይሆንም በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ያለው ልዩነት የሚፈጥረው አለ መግባባት  እግዚአብሔርን በመካድና ኢእግዚአብሔርነት ባህል በመከተል ማስወገድ አይቻልም። ባተቃርኖ ሃማኖትና ግብረ ገብ ከባህል የሚደልዝ ባህል ወደ አለ መረጋጋት የሚወስድ መንገድ ነው፡ ኤውሮጳ በጸንፈኞችና አሸባሪያን የሚሰነዝሩት የሽበራ ጥቃት የሚወልደው ፍርሃት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር እንዲሁም የሃማኖት ነጻነት ለአደጋ እያጋለጠ ነው። አሸባሪነት በኤውሮጳና በኤውሮጳ ዜጎች መካከል ብዙ ፍርሃት እያዳደረ ከመሆኑም ባሻገር ጤናማ የሃማኖት ነጻነት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ተከባብሮና ተቻችሎ መኖር እንዲያሽቆለቁልና ብዙ ወጣቶች ለሃይማኖ አክራሪነት ምርጫ እየማረከ ነው፡ ጸንፈኛነት የሃይማኖት ነጻነት የሚቃወም የሌላውን ሃይማኖት የሚክድ ተግባር ነው። ኢየሱስ እንደሚያስተምረው ግን እግዚአብሔር አምላክህን አፍቅር ባለ እንጀራህንም እንደ ገዛ እራስህ አፍቅር ሲል ነው፡ እግዚአብሔርን የሚያፈቅር ሰው ባለ እንጀራውን ሊጠላ አይችልም እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎ ይጠቁማል።

ፍርሃት የኤወሮጳ ስልጣኔ የመዳከሙ ውጤት ነው፡ ግለኝነት እኔነት ፍጆታነትና ውጫዊ ጥቃት ኤውሮጳ ያላትን ስልጣኔ ለአደጋ እያጋለጠ ነው። ፍርሃቱ የሚመነጨው ሽበራው ስላለ ሳይሆን ሽበራው የኤውሮጳ ስልጣኔ መዳከሙ የሚወልደው ፍርሃት ገሃድ ስለ ሚያደርገው ነው። ይህ ሲባል አሸባሪነት ፍርሃት ሊወልድ አይችልም ማለት አይደለም፡ ለሥጋት ለአመጽ የሚዳርገን ጥሩነታችን የማይሻ ሁሉ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ግድ የማይለው ውጫዊ አካል ሊኖር ይችላል። እየታየም ነው። ክርስቲያኖች ከቀድሞው ለኤውሮጳ አሁን እጅግ አስፈላጊ ናቸው። የክርስትናው ባህል እጅግ አሁን አስፈላጊ ነው። ስለዚህ ጉባኤው ለሁሉም በኤውሮጳ ለሚገኙት ማኅበረ ክርስቲያን የሚያጽናና ብርታትን የሚያሰጥ ክርስትናን በፈረቃ ሳይሆን በዕለታዊ ሕይወት በመኖር ፍትህ ሰላም የጋራ ጥቅም መሻት የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር የሃይማኖት ነጻነት ጥበቃ እንዲያነቃቁ ሊደግፍ ይገባዋል። ለሁሉም መለኰታዊ ምሕረት መስካሪ በመሆን የኤውሮጳ ስልጣኔ ለአደጋ ከሚያጋልጡ ተግባሮች ነጻ የሚያወጣ ነው እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አመለከተ።








All the contents on this site are copyrighted ©.