2017-01-03 10:11:00

ቅዱስነታቸው "የእግዚኣብሔር እናት የሆነችውን ማሪያምን መቀበል 'መንፈሳዊ ባዶነት' እንዳይሰማን ያደርገናል አሉ"።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በታኅሣሥ 23/2009 ዓ.ም. እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር ከተከበረው አዲስ ዓመት ጋር አብሮ በተከበረው ማሪያም የእግዚኣብሔር እናት ዓመታዊ ክብረ በዓልን አስምልክተው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት የእግዚኣብሔር እናት የሆነችውን ማሪያምን መቀበል “መንፈሳዊ ባዶነት” እንዳይሰማን ያደርገናል ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በስብከተቸው ጨምረው እንደ ገለጹት በተለይም ደግሞ ውሳኝ እና አደገኛ በሆኑ ጊዜያት ውስጥ በምንገኝበት ወቅት ሁሉ ተስፋን እና ኋይልን የምታጎናጽፈን እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በመሆኑዋ እርሷን አጥብቀን መያዝ ይጠበቅብናል ብለዋል።

የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያምን ባሕሪ ለልጆቻቸው ሕይወትን ከሚሰጡ እናቶች ጋር በማነጻጸር ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን የጎርጎሮሳዊያኑን አዲስ ዓመት በምናከብርበት እለት ማሪያም የእግዚኣብሔር እና የእኛም እናት መሆኑዋን በምንዘክርበት ወቅት ሁሉ “ወላጅ አልባ” እንዳልሆን እንዲሰማን ያደርገናል ብለዋል።

“እናቶች የሌሉበት አንድ ማኅበረሰብ በጣም የቀዘቀዘ ማኅበረሰብ ብቻ ሳይሆን ልብ የሌለው እና የቤተሰብ ጣዕምን የማያውቅ ማኅበረሰብ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እናቶች የሌሉበት ማኅበረሰብ ምሕረት አልባ ማኅበረሰብ ነው ካሉ ቡኋላ ምክንያቱም አሉ ቅዱስነታቸው ምክንያቱም እናቶች ርኅራኄን፣ ቅድመ ሆኔታ ያልተቀመጠበት እገዛን ስለሚያደርጉ እና የተስፋችን ሁሉ ብርታት የሚመነጨው ከእነርሱ በመሆኑ የተነሳ በመሆኑ ነው ብለዋል።

በዙን ጊዜ እናቶች ሕይወት ሰጪ መሆናቸውን እንዘነጋለን ያሉት ቅዱስነታቸው እናቶች በማንኛውም ሁኔታ ቢሆኑ ለልጆቻቸው የተሻለውን ነገር ለመስጠት ሁል ጊዜም ጥረት እንደ ሚያደርጉም ገልጸዋል። እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር ይህንን 2017 አዲስ ዓመት ስንጀምር እግዚኣብሔር በማሪያም በኩል ያደረገልንን መልካም ነገሮችን ሁሉ በማሰብ እና እናት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያናችንም ያደረገችልንን መልካም መልካም ነገሮችን በማሰብ፣ እናቶቻችን ስላደረጉልን መልካም ነገር በማሰብ እና በማመስገን ይህንን አዲስ ዓመት ልንጀምር ያስፈልጋል ብለዋል።

መንፈሳዊ ባዶነት ስሜት በሚሰማን ወቅቶች ሁሉ በጸጥታ ውስጣችንን እየቦረቦረ ነብሳችንን እንደ ሚያጠፋ የካንሰር በሽታ ይሆናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ስሜት ቀስ በቀስ የብቸኝነት ስሜት እንዲሰማን በማድረግ ማንነታችንን እንድንዘነጋ ያደርገናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ይህ የብቸኝነት ስሜት ደግሞ የርኅራኄ ስሜት እና መንፈሳዊ ብርታትን እንድናጣ በማድረግ መንፈስዊ ስር መሰረታችንን እንድንዘነጋ ያደርገናል ብለዋል።

ማሪያም እግዚኣብሔር በእርሷ ሕይወት ውስጥ የፈጸመውን ነግሮች ሁሉ በማሰላሰል የኖርች ሴት ነበረች በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በቅዱስ ወንጌል ውስጥ ማሪያም የሰራችው ሥራ በስፋት በይገለጽም ነገር ግን የኢየሱስ ተልዕኮ ከፍጻሜ እንዲደርስ ከፍተኛ እገዛ ማድረጉዋ የማይካድ ነገር መሆኑን ገልጸው መስቀሉን ተሸክሞ በሚሄድመት ወቅት ሁሉ እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ ነገሮችን ሁሉ በዝምታ በውስጡዋ ታሰላስል ነበር ብለዋል።

በእየ አድባራቱ፣ በየገዳማቱ፣ መፈሳዊ ንግደት በሚደረግባቸው ስፍራች ሁሉ፣ በእየ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ተሰቅለው የምናያቸው የማሪያም ምስሎች የማሪያምን ታላቅነት ይገልጹልናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በጭንቀት ውስጥ በምንሆንባቸው ጊዜያት ሁሉ ማሪያም የእናትነት ባሕሪዋን ታሳየናለች ካሉ ቡኋላ እናት ባለችበት ቦታ ሁሉ ርኅራኄ አለ፣ ማሪያም በእናትነቱዋ ትህትና እና ርኅራኄ የደካማነት ስሜት መገለጫዎች ሳይሆኑ በተቃራኒው የብርታት መገለጫዎች መሆናቸውን ታስተምረናለች ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት እናታችን ቅድስት ማሪያም በእናትነት ጸጋዋ ትጎበኘን እና ከወላጅ አልባ ስሜት ውስጥ እንድንወጣ ትረዳን ዘንድ ልንማጸናት ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ በተጨማሪም ወንድማማቾች እንደ ሆንን በመረዳት እርስ በእርሳችን አንዱ ለሌላው ርኅራኄን እንድያሳይ ትርደን ዘንድ መምጸንም ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ተስፋን፣ ርኅራኄን፣ ወንድማማችነትን እንድንዘራ እንድታግዘን መማጸንም ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ማሪያም የእግዚኣብሔር እናት መሆንዋ እኛም ወላጅ አልባ ሳንሆን እናት እንዳለን እንድንገነዘብ ያደርጋል ይህንንም እውነታ መመስከር ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.