Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ፍትሕና ሰላም

በዓለ ልደት በአፍሪቃ፥ ብፁዓን ጳጳሳት ሰላምና በመከባበር ተቻችሎ መኖር

በዓለ ልደት በአፍሪቃ፥ ብፁዓን ጳጳሳት ሰላምና በመከባበር ተቻችሎ መኖር - AFP

28/12/2016 16:39

የተለያዩ የአፍሪቃ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች በተለይ ደግሞ በዚያ ጦርነት ውጥረት በሚታይባቸው ክልሎች የሚገኙት በላቲን ሥርዓት የተከበረው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሚከበርባቸው አገሮች ሰላ እርቅ ፍቅር በመከባበር ላይ የጸና ተቻችሎ መኖር በተሰኙት ቁልፍ ነጥቦች የተመራ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታውቋል።

በአይቮርይኮስት የአቢጃን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ዣን ፔር ኩትዋ ባስተላለፉት የበዓለ ልደት መልእክት ከዚያ ካለ ምንም አግላይነትና ነጣይነት ሁሉን የሚያፈቅር የተካፍሎ መኖር ሐሴት የሰላምና የምህረት መንገድ አብነት ከሆነው ከሕፃነ ኢየሱስ እንማር ስለዚህ የአገሪቱ ክርስቲያን ምእመናን የፖለቲካ አካላት የሃይማኖት መሪዎች ሁሉ ማንኛው ዓይነት የመከፋፈል ጨለምተኝነትና ጥላቻን እምቢ በማለት ሰላምና እርቅ እንዲገነቡ አደራ እንዳሉ ፒሮ አስታውቋል።

በማውሪሸስ የፖርት ልዊስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ማውሪሰ ፒያት የዚህች የአገሪቱ ርእሰ ከተማ ለአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያን ኤነስት በጋራ በበዓለ ልደት ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት ትልቁ ስጦታና ፍቅር ገዛ እራስ አሳልፎ መስጠት መህኑ በማብራራት ይኽ ደግሞ ሰው ሆኖ ስጋችንን ለብሶ የመጣው የእግዚአብሔር ልጅ በቃልና በተግባር በሰጠን ልዩና የላቀ አብነት አማካኝነት ገጦልናል በማለት ባለንጀራን እንደ ገዛ እርስ አፍቅር የሚል ጥሪ የተማከለበት መልእክት ማስተላለፋቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘው፥

በቶጎ የሎሜ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ደኒስ አሙዙ ድዛክፓህ ያስተላለፉት የበዓለ ልደ መልእክት የጥልቅ ሰላምና አቢይ የትብብር መንፈስ ላይ ያተኮረ ሲሆን፡ በደሞክራሲያዊት ረፓሊክ ኮንጎ የኪንሻሳ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ላውረንት ሞሰንግዎ ፓሲንያ በበኩላቸውም የአገሪቱ ክርስቲያኖች አመጽን በመካድ የሰላም መሣሪያ ሆነው እንዲገኙ ጥሪ ሲያስተላልፉ ይኽ ደግሞ በአገሪቱ እ.ኤ.አ. ከ 2001 ዓ.ም. ጀምሮ በስልጣን ላይ  ያለው የርእሰ ብሔር ጆሰፍ ካቢላ መንገሥት ርእሰ ብሔሩ እንደ ሕገ መግንሥቱ መሠረት ለቀጣይ ምርጫ እንዳይቀርቡ የሚለው አዛዥ የውሳኔ አንቀጽ ለአራተኛ ጊዜ እጩ ሆነው ለመቅረብ በሚያስችላቸው እይታ ለማስተካከል ያላቸው ፍላጎት ገሃድ ካደረጉበት ቀን ጀምሮ የተቀሰቀሰው ውጥረት እ.ኤ.አ.. ህዳር ወር ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቅ የነበረው የርእሰ ብሔር ምርጫ ገና ቀጠሮ ወዳልተያዘለት ቀንና ጊዜ እንዲዛወር ማድረጋቸው የከሰተው አለ መግባባት የሕዝብና የአገር ጥቅም ላይ በማተኮር አገራዊና ሕዝባዊ ልክነት ያለው ምላሽ እንዲያገኝ በማሳሰብ አያዘውም የዜጎች ሰብአዊ መብትና ክብር እንዲጠበቅ የበዓለ ልደት ሰላም የእርስ በእርስ መገዳደል ቅትለና ዓመጽ አግሎ በምትኩ ፍትሕ ፍቅርና እውነት ይጸግው ካሉ በኋላ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በለገሱበት ቀን ሁሉም የኮንጎ ዜጎች  በዚህ የአገሪቱ ታሪክ በቋፍ ላይ በሚገኝበት ፈታኝ ወቅት የሰላም የእርቅ መሣሪያ ሆነው እንዴገኙ አደራ ብለው የፖለቲካ አካላት ኅሊናቸው እንዲያደምጡና የሕዝባቸው ከባድ ስቃይ ለመመከት ብቃቱ እንዲኖራቸው በልባቸው የጋራው ጥቅም እንዲያስቀድምና ለዚህ ዓላማም እንዲጠመዱ በማለት አስተላልፈዉት ነበረው ጥሪ ብፁዕ ካርዲናል ላውረንት ሞሰንግዎ ፓሲንያ ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ ፒሮ አስታውቋል።

በሰነጋል የዳካር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ በንጃሚን ንዲያየ እ.ኤ.አ. በ 2004 ዓ.ም. ከአገሪቱ ሕገ መንግሥት ዘንድ ካለው የወንጀለኛ መቅጫ ሕገ አንቀጽ ውስጥ ተካቶ የሚገኘው የሞት ቅጣት የሚፈቅደው ሕግ ከሰረዘ ወዲህ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የሚታይው በወንጀል ቡድኖች የሚፈጸሙት ከባድ ወንጀልችና ሕገ ጥሰቶች ግምት በመስጠት ዳግም የሞት ፍርድ የሚፈቅድ ሃሳብ በማቅረብ የሞት ፍርድ ለማካተት የሚሻ እየተሰማ ያለው ፖለቲካዊ ፍላጎት ሌላ አማራጭ መፍትሔ በማፈላለግ ወንጀሎችን መዋጋትና ወንጀለኛን ማነጽ ያለው አስፈላጊነት በማብራራት አቋራጭ ሳይሆን በሳል ሃሳብ የሚያፈልቅ የህይወት ባህል በሚያነቃቃ  አመለካከት እንጂ የሞት ፍርድ መፍትሔ ሆኖ አያውቅም የሚል ሃሳብ ያካተተ በበዓለ ልደት ምክንያ ባስተላለፉት መልእክት በማብራራት በሴቶች በሕጻናት ላይ የሚፈጸሙት ዓመጾች ብዙውን ጊዜ በአገሪቱ ማኅበረሰብ ዘንድ የሚታየው ቅቡል ዝንባሌ የአገሪቱ ስነ ምግባራዊ ግብረ ገባዊ መመዘኛዎችና እሴቶችን በማክበር እንዲቀረፍና ያንን በፍጆታ በቁስ አካላዊ ጽንሰ ሃሳብ በሚያስፋፋው ባህል እየተበከለ ያለው ማኅበራዊ ኅሊና ይታረም ካሉ በኋላ በዓለ ልደት እግዚአብሔር የቸረው የሕይወት ውህበት የሚከበርበት በዓል ነው ይኽ የከበረ በዓል የእግዚአብሔር ሰላም በልባችን ያስርጽ በማለት ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አስታውቋል።

28/12/2016 16:39