2016-12-26 15:27:00

በዓለ ልደት በቅድስት መሬት


በሮቻችን እንክፈት ወንድሞቻችንን እናገኛለን፡ በእየሩሳኤም የላቲን ሥርዓ ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ፒየርባቲታ ፒዛባላ በቤተልሔም በሚገኘው በባዚሊካ ዘልደቱ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በሮቻችንን እንክፈትና ከወንድሞቻችንን ጋር እንገናኛለን የሚል ሃሳብ ያሰመሩበት ስብከት መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሳራ ፎናሪ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳ ተችሏል።

በእየሩሳሌም የላቲን ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ሐዋርያዊ መስተዳድር ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፒዛባላ በዚህ የፍልስጥኤም ብሔራዊ ርእሰ መሥተዳድራዊ መንግሥት ርእሰ ብሔር ማህሙድ አባስ በእንግድነ የተገኙበት የክልሉ ማኅበረ ክርስቲያን ባሳተፈው በተለያዩ የልደት መንፈሳዊ መዝሙሮች ተሸኝቶ ለበዓለ ልደት ዘእግዚእነ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ፥ ሊከወን የሚገባው መስተንግዶንና ተቀባይነትን የሚጠይቀው የድኅነት ብሥራት፡ የተኖረው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ፍጻሜ ማግስት በዓለ ልደት እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ለማዳን ከዚህ ድህነት ከተጠማው ጋር ለመገናኘት በሩን ከፍቶ ወደ የኅልውናና የከተሞቻችን ጥጋ ጥግ ክልል ከእያንዳንዳችን ጋር ሱታፌ ሊኖረው ወደ እያንዳንዳችን ይመጣል፡ በሮቻችንን ከፍተን ይገባ ዘንድ ስንፈቅድለት የመዳንን ጥሪ ይጎበኘናል። ስለዚህ በዓለ ልደት ፈጽሞ ለማዳናችን የማይዘጋው የጌታ በር ዘወትር ክፍት መሆኑ የሚያረጋግጥልን የጌታ ሰው መሆን እኛ ወደ እርሱ ማለቱን ብናቋርጥም እርሱ መሆናችንን ተላብሶ ወደ እኛ ሊመምጣት ፈቅዷል።

የተከፈተው የእግዚአብሔር በር፥ ስለዚህ እርሱ በቤታቸው በልባቸው ውስጥ እንዲወለድ ፈቅደው በራቸውን ክፍት ለሚያደርጉለት በእነርሱ ዘንድ ይገባል፡ እንደ ሄረዶስ በሮቻቸውን ለሚዘጉበት በቤተታቸው ሥፍራ የለም በማለት ማንኳኳቱን ግድ ሳይሰጡ በሮቻቸውን ለዘጉበት። የሚጠብቁትና የሚንከባከቡት የከበረ ሃብት ወይንም የግል ሃሳብና ጽንሰ ሃሳብ ያላቸው አይ ብለው በራቸውን እንደዘጉበት ነን፡ የተከፈተ ወይንም የተዘጋ በር መከወን ነጻነታችን ነው። ሰላም ነጻነትና ድህነት የሆነውን ለመቀበል በሮቻችን ብንከፍት ለእኛ ይበጀናል። ተስፋ ድንግዝግዝ በሆነበት ዓመጽና ግብረ ሽበራ በሚፈራረቅበት እነዚህ ሁሉ አሉታዊ ሁነቶች አጥሮቻችን ከፍ ለማድረግ በሮችን አጠንክረው ለመገንባት የሚራወጥ ዓለም፡ በተቻለ መጠን በታማኝ ተስፋ በሩን ከፍቶ ከመጠበቅ ይልቅ ከሁሉም እርቆ በሩን ዘግቶ ለመኖር የሚይገፋፋ ነው።

ነገር ግን የተዘጉ በሮች በሚገባ ጥብቃ በሚከናወንባቸው ድንበሮች በእውነቱ የሚታየው አመጽና ችግር ሁሉ እንዲከወን የሚያደርግ ነው። ብዙ አገሮች በምግባረ ብልሽት ተውጠው የብዙዎች ተስፋ ተሟጦ ሁሉ በዚህ የሰው ልክንነት በሌለው ሁነት ተጥለቅልቆ ገንዘብ መግሥት ሥርዓት አምላክ በሆነበ ዓለም በሶሪያ በኢራቅ በግብጽ በዮርዳኖስ የሚታየው ለያይ ገንጣይ ዓመጽ፥ በዚህ በቅድስት መሬትም ጭምር ያለው የፍትሕ የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ መጓደል የእውነት ጥማት የእውነተኛ ፍቅር ጥማት እርስ በእርሳችን ከመቀባበል ከመደጋገፍ ይልቅ ከእውንተኛው ፍቅር ርቀን እርስ በእርሳችን እየተከዳዳን እንገኛለን። የምንኖርበት ዓለም የጠላትነት አመክንዮ ሥነ አምእሮአዊ ጫና በሆነበት ማኅበራዊውና ግላዊው ስነ ልቦና በዚህ የጠላትነት አመክንዮ ተገዥ ሆኖ ይኽ መገዛትም የማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መመዘኛ እየሆነ አልቦ ተስፋ ወደ ሆነው ያኗኗ ሥልት እየዳረገን ነው። ይኽ ሁሉ ከግል እስከ ብሔራዊ አገር ያሉት በሮች ሁሉ እንዲዘጉ እየዳረገ ነው፡ አለ መተማመን መጠራጠር በቁራኛ መተያየት ግፉእነት ጦርነትንም ሁሉ እያዛመተ ነው። ሁላችን የተነጠልን የተገፋን ሆነን ይሰማናል።

በሮቻችን ከከፈትን በዓለ ልደት አንድ ልዩ ሐሴት ሰላም ድህነት ወደ ውስጣችንና ወደ ቤቶችን እንዲገባ ያደርጋል። የእግዚአብሔርን ቅዱስ ፈቃድ የምንጋራ ከሆን ሰላም ይኖረናል። የጠላጥነት መንፈስ ለሚሰብከው ርእዮተ ዓለም እምቢ ለማለት ይቻለናል። በጠላትነት ከመተያየት በወንድማማችነት መንፈስ እንድንተያየ እንድንቀባበልና እንድንከባበር ያደርገናል። በርን መክፈት። ልብንና በርን ከመዝጋት ለጋስነት ምኅረትና ይቅር ባይነት ከተበቃይነት። በዚያ በሰው ልጅ አመኔታ በማድረግ ሰው ሆኖ ለመምጣት በፈቀደው እግዚአብሔር ላይ አመኔታ ይኑረን። እርሱ በእኛ አመኔታ ካደረገ እና ታዲያ መሮቻችንን ለመክፈት እንዴት ይከብደናል?

ከዝግታምነታችን እንላቀቅ እንውጣ። እንዲህ ካደረግን ወደ እኛ ወደ ሚመጣውና ወደ ሚጠራን ጌታ እናቀናለን። በሥልጣኑ በግል ፍላጎት በግል ሃብት መከላከል ላይ ተዘግቶ ከመኖር ይልቅ መዳኑን እንቀበላለን። ኢየሱስ ማንንም የማይነጥል የማያገል የእግዚአብሔር ክፍት በር በእኛ ውስጥ እምነት ተስፋን ያነቃቃ ህያው ያድርግ። እንተ ተስፋችን ነህ፡ ተደናግረን ተወናብደን አንቀርም። እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፎናሪ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.