Social:

RSS:

የቫቲካን ሬድዮ

ከዓለም ጋር የሚወያይ የር.ሊ.ጳጳሳትና የቤተ ክርስትያን ድምጽ

ቋንቋ:

ኅብረተሰብ \ ጤናና አከባቢ

ለዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን ቅዱስ አባታችን የሚያስተላልፉት መልእክት

ለዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን ቅዱስ አባታችን የሚያስተላልፉት መልእክት - REUTERS

16/12/2016 16:48

እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን ኵላዊት ቤተ ክርስትያን በምታከብረው ቅድስት ማርያም ዘሉርድ ዓመታዊ በዓል ቀን ጋር ተያይዞ እ.ኤ.አ. በ1992 ዓ.ም. ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ውሳኔ መሠረት እ.ኤ.አ. ከ1993 ዓ.ም. መታሰብ የጀመረው ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ በዓለ ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ባከበረችበት ቀን የፈረሙበት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የህሙማንና የህክምና ባለ ሙያዎች ሐዋርያዊ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ይፋ ያደረገው 25ኛው ዓለም አቀፍ የህሙማን ቀን መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር የዜናና ሕትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

የዚህ እ.ኤ.አ. የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም. ታስቦ የሚውለው 25ኛው ዓለም አቅፍ የሕሙማን ቀን መሪ ቃል “ኀያል የሆነው እርሱ ታላቅ ነገር አድርጎልኛልና…” (ሉቃ. 1,49) እግዚአብሔር ለሚፈጽመው ድንቅ ሥራ ለመደነቅና ለአግርሞት ምክንያት መሆን እንደሚገባው ቅዱስ አባታችን በዚህ ባስተላልፉት መልእክት በማሳሰብ በዚያ በሉርድ ባለቸው የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ረዳኢተ ህሙማን ቅዱስ ምስል ፊት በመንፈስ ገዛ እራሴን በማኖር ሁላችሁ በስቃይና በህመም የምትገኙትን ወንድሞቼና እህቶቼ ቤተሰቦቻችሁንም እንዲሁም በተለያየ ተልእኮና ጥሪ መሰረትም በተለያዩ የጤና ጥበቃ ተቋማት ሥር በመታቀፍ አገልግሎት የሚሰጡት የህክምና ባለ ሙያዎች ሁሉንም ለጥበቃዋ አቀርባችኋለሁ በጸሎቴም አስባችኋለሁ እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አመለከተ።

ቅዱስ አባታችን በዚህ መልእኽታቸውንም ሁሉንም በስቃይ በሕመም የምገኙትን በማጽናናት ሃኪሞች የጤና ጥበቃ ባለ ምያዎች የህሙማን ቤተሰቦች የበጎ ፈቃድ አገልጋዮችን ሁሉ ለዚያች ለእያንዳንዱ ሰው ልጅ የጌታ የዋህነት ዋስትና የሆነቸውን ገዛ እራስ ለእግዚኣብሔር ፈቃድ በሙላት በማቅረቡ ረገድም አርአያ ለሆነቸው ረዳኢተ ህሙማንና የሁሙማን ጤንነት የሆነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምን እንዲያስተነትኑና በቃልና በቅዱሳት ምስጢራት አማካኝነት የሚበረታው እግዚአብሔርንና ወንድሞቻችን በተለይ ደግም በሕመምና በስቃይ ላይ የሚገኙንት ለማፍቀር የሚያስችል እምነት ጋር እንዲገናኙ እንዳበረታቱም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።

በጤና ጥበቃው ረገድ እየተደረሰ ያለው እድገትና እደ ጥበባዊ ምጥቀት የማንኛውም ህመምተኛ የማይጣሰው ችላ ሊባል የማይችለው ሰብአዊ መብትና ክብር የሚያረጋግጥ በሕይወት ጉዳይ በተመለከተ ያለው ተልእኮ ምንም’ኳ ከፍተኛ ጉዳትና ስንክልና ያለው ከባድ በሽታም ይኑረው ሕይወትን ጤናንና ተፈጥሮን የማክበርን የመንከባከብ ባህል የሚያስፋፋ ይሁን። ዳግም በመታደስም የሰው ልጅ ሙሉና ሰብአዊ ክብር ለማስጠበቅ ለሚደረገው ጥረት የስነ ሕይወት ሥነ ምግባር ዙሪያ ገዛ እራሳቸውን ለመንከባከብና ለመከላከል የማይችሉትን ደካሞችና ተፈጥሮን ለመንከባከብ የሚያስችል በተገባ አቀራረብ አወንታዊ ግፊት ይሁን።

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን ሲያጠቃልሉ፥ ሁሉም የእነዚያን ብሩህ መስካሪያ የእግዚአብሔር ጓደኞች ከእነርሱም ውስጥ የማከሚያ ቤቶችና የጤና ጥበቃ ባለ ሙያዎች ጠባቂ ቅዱሳን ዮሐንስ ዘመስቀልና ቅዱስ ካሚሎ ዘለሊስን እንዲሁም የእግዚአብሔር የዋህነት ልኡክት የሆኑትን ቅድስት ማድረ ተረዛ ዘካልኩታን ብሩህ ምስክርነትን በመምሰል የእግዚአብሔር ህላዌና ፍቅር ደስተኛ ምልክቶች ሁኑ እንዳሉ መልእክቱን ጸምሮ የዘገበው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

16/12/2016 16:48