2016-12-12 16:32:00

አበ እስፓዳሮ፥ ቅዱስ አባታችን በተረጋጋ መንፈስ የቤተ ክርስቲያን ኅዳሴው በማቅናቱ ሂደት


ስካይ አትላንቲክ የቴለቪዥን የሥርጭት መርሃ ግብር ከኢየሱሳውያን ማኅበር አባልና በማኅበሩ ለሚታተመው ካቶሊካዊ ሥልጣኔ ለተሰየመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ጋር በመተባበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ዙሪያ ያጠቀረው ሰነዳዊ ፊልም እ.ኤ.አ. ታህሳስ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 11 ከሩብ ለትርኢት መቅረቡ ዘገባውን ያጠናቀሩት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸቶፋንቲ አስታውቋል።

አባ ስፓዳሮ ስለዚሁ ሰነዳዊ ፊልም በማስመልከትም ከቫቲካ ርዲዮ ለቀረበላቸው መጠይቅ ሲመልሱ፥ ትርኢቱ ልበ ወለዳዊ ፊልም ሳይሆን ምእመናን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ላይ ያላቸው ተስፈኛ ጥባቄ አቢይ ግምት የሰጠ ስለ እሳቸው የሚባለው የተለያዩ ምእመናን ከእነዚህም ውስጥ የፊልም ደራሲና ቀራጭ የተባበሩት የአመሪካ ዘጋ ማርቲን ስኮርዘሰ የሰጡት ቃል ያካተተ ሲሆን፡ ብዙውን ጊዚ እንደሚባለውም ገር ር.ሊ.ጳ. ተብለው እንደሚገለጡት የዋህ ናቸው ተብሎ እንደሚነገርላቸው ሳይሆን ከዚህ ሰነዳዊ ፊልም እንደንረዳው ብዙ ውጣ ውረድን ያለፉ መሆናቸውና ገናም ውጣ ውረዱ ቢኖርም በጥበብና በጸሎት በሊቅነት ነገሮችን እየለዩ መልስ ለመስጠት የሚጥሩ የዋህነት ገርነት መልካምነት ከእውነት ጋር በማዛመድ በቃልና በሕይወት የሚኖሩ ናቸው። ከዚያ እ.ኤ.አ. 2013 ዓ.ም. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡበት ቀን ናሰዓት ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ መታወቅን ሲጀምሩ ሁሉም ማንነታቸውን ታሪካቸው ለማወቅ በተለያዩ የጋዜጠኛ ዘርፍ በደራሲያንና በፊልም ቀራጮች ፍተሻውን እንደተያያዘውና እሳቸው  ስለ ገዛ ርራሳቸው ምን ይላሉ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ከተለያዩ ዓለም አቀፋዊና ብሔራዊ አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ጋር ባካሄዱት ቃለ መጠይቅ የሰጡት መልሱ ስርዓት ባለው ሂደቱን በማካተት ሌሎች ስለ ቅዱነታቸው የሚሉትን ተራኪ ሰነዳዊ ፊልም ነው ብሏል።

ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ሰማንያ ዓመት እድሚያቸውን ያከብራሉ።  ዕለቱንም ሁሌ እንደሚደያደርጉት አለ ምንም የተለየ ሁኔታ እንደ ወትሮው በሚኖሩት ሥልት እርሱም በጸሎና በአስተንትኖ ጌታ የሰጣቸውን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታነት ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን በመኖር የዕለቱ የተያዘው መርሐ ግብር በመኖር የንደሚያሳልፉት የተረጋገጠነው። ስለዚህ ለየት ያለ ነገር እንደማይኖር ነው ያሉት አባ ስፓዳሮ አክለው ቅዱስነታቸው በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እያረጋገጡት ያለው ኃዳሴ በማስመልከትም የተቀባይነት ሃሳብ ኅዳሴውን ለጥያቄ የሚያቀርቡ የተለያዩ አስተያየቶች ሁሉ ይቀርብባቸዋል ሆኖም እሳቸው እንደሚሉት ስለ እኔና ስለ ቤተ ክርስቲያን መጸለይ ነው። ስለዚህ የቀረበው ሰነዳዊ ፊልም የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተክለ ሰብነት ለማስተዋል አስችሏል ስለዚህ ሰነዳዊው ፊልም በሳቸው የተደረሱ ዓዋዲ መልእክቶች፡ ሐዋርያዊ ምዕዳኖች የሚለግሱት ትምህርት ስብከት የሚያስተላልፉት መልእክት ሁሉ በጥልቀት ስትመልከትና ለመተንተን ስትሞክር በእውነቱ ተክለ ማንነታቸውን ለማስተዋል ይቻላል፡ ደሞም እያንዳንዱ የቅድሱ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆን በእግዚአብሔር ፈቃድ የሚመረጠው ለሚመረጥበት ወቅት የእግዚአብሔር መልስ ናቸው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.