2016-12-09 14:37:00

ቅዱስነታቸው ያለ አዳም ኋጥያት የተጸነሰች እመቤታችን ቅድስት ማሪያም ሐውልት ሥር የአበባ ጉን ጉን አኖሩ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትነው እለት ማለትም በኅዳር 29/2009 ዓ.ም በአውሮፓዊያን የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር የተከበረውን ያለ አዳም ኋጥያት የተጸነሰች ማሪያም አመታዊ ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሮም ከተማ በሚገኘው በእስፓንሽ አደባባይ ጳጳሳት ለአለፉት 50 ዓመታት ያህል ይህንን በዓል በመታሰቢያነት ለመዘከር  ንግደት በማድረግ ለያለ አዳም አጥያት የተጸነሰች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ክብር ይሰጡ እንደ ነብረ የሚታወቅ ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህንን ልማድ እና ወግ በጠበቀ መልኩ በትላንትነው እለት በእስፓኒሽ አደባባይ መገኘታቸው ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው ከሮም ከተማ ከንቲባ ጋር በመሆን ያለ አዳም ኋጥያት የተጸነሰች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም አውልት ሥር 5 ነጫጭ የጽጌሬዳ አበባዎችን ማስቀመጣቸውና ጸሎት ማድረጋቸው ተያይዞ ተጠቅሱዋል። ቅዱስነታቸው በእለቱ ያደረጉት ጸሎት በጎዳና ላይ ለሚኖሩ ሕጻናት፣ በከፍተኛ የኑሮ ጫና ውስጥ ለሚገኙ ቤተሰቦች እንዲሁም በሥራ እጦት እየተቸገሩ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ጸሎት ማድረጋቸውም ተገልጹዋል።

“ያንችን ዓይነት ንጹሕ የሆነ ልብ እንዲኖረን፣ በነጻነት መውደድ እንድንችል፣ ጭንብልአችንን አውልቀን ጥለን በትህትናና በእውነት ያለምንም ማንገራገር ለሌሎች መልካም ነገርን መመኘት እንድንችል” እርጅን ብለው መጸለያቸው የታወቀ ሲሆን በአንቺ ጥበቃ በመታመን ራሳችንን፣ ከተማችንንና ዓለማችንም  ሙሉ በሙሉ ለማደስ እንድንችል አብቂን ብለው መጸለያቸው ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው ካሳረጉት ጸሎት ቡኋላ በቦታው የነበሩትን ሰዎችን ሰላም ብለው የታመሙና አረጋዊያን የሆኑ ሰዎችን ከባረኩ ቡኋላ ወደ ቫቲካን መመለሳቸው ታውቁዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.