2016-12-09 16:33:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ቤተ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት የምትደግፍ የውበትና ውህበት ገነት ትሁን


ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢና የጳጳስውያን መናብርተ ጥበብ አቀናጅ ምክር ቤት የሚያሰናዳው የመላ ጳጳሳዊ መናብርተ ጥበብና ተቋሞች የጋራው ዓውደ ጉባኤ ምክንያት የዘንድሮ 21ኛውን ዓውደ ጥናት “ብልጭታ ውበት፥ ለከተሞቻችን የአዲስ ሰብአዊ ገጽታ” መሚል ርእስ ሥር ተመርቶ መካሄዱ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶቦራ ዶኒኒ አያዘው የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን ለጉባኤው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያስተላልፉት መልእክት በማንበብና ኣሳቸው ባቀረቡት አስተምህሮ እንዲሁም የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤትና የጳጳስውያን መናብርተ ጥበብ አቀናጅ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ባስደመጡት ንግግር እ.ኤ.አ. ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓ.ም. መካሄዱንም አስታውቋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት መልእክት፥ ቁምስናዎች በተለይ ደግሞ በከተሞቻችንና በህልውና ጥጋ ጥግ ክልሎች የሚገኙት ቁምስናዎች ባላቸው ትህትና የተሞላው ተራ በሆነው ኅላዌአቸው አማካኝነት ለኅብረትሰብ የሰናይና ጥዑም ውህደት እድገት የሚያረጋግጠው ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት የሚያነሳሳው የማስተናገድ ተግባር ውበት ማእከል መሆን ይጠበቅባቸዋል። የሰዎች በተለይ ደግሞ የእነዚያ ገዛ እራሳቸውን ለመከላከልም ሆነ ለማቀብ ለሚሳናቸው ሰብአዊ መብታቸውና ክብራቸውን ለመጠየቅ ለሚሳናቸው ያንን በዓለማችን የሚታየውን አለ ማስተናገድ ሌላውን በማጥላላት እንዲታይ የሚያደርገው ስግግብነት ብዙውን ጊዜ የሚታይባቸው ከተሞቻችን ጥበቃና እንክብካቤ መቀራረብና መስተንግዶ የሚከወንባቸው ሥፍራ እንዲሆን የሚያነቃቃ ነው።

ከያንያን ውበትን ይንከባከባሉ ውበት ደግሞ ለቁስሎቻችን ፈውስ ይሆናል

ከያንያን የጥበብ ሰዎች በተለይ ደግሞ አማንያን ከያንያን አቢይ ኃላፊነት አለባቸው። በሚያቀርቡት ግብረ ክየና የውበት ልሳን በመሆን በዚያ ግድየለሽነት ክፋት የተሞላውን ሥፍራ የተስፋ ብልጭታ እንዲያስገቡ በማለት የተማጠኑ ቅዱስነታቸው በማስከተልም የሥነ ምህንድስና የሥነ ቅብ ሥነ ንድፍ ብሎም ገጣሚዎች ሙዚቀኞች የሥነ ሲነማ ጠቢባን ደራሲያን የሥነ ቀረጻ የሐውልት ሥራ ሙያተኞች በጠቅላላ ሁሉም የተለያዩ የሥነ ክየና ሙያተኞች በዚያ ዕለታዊ ኑሮ ጨለማና ድንግዝግዝ አምባገነን በሆነበት ሥፍራ ሁሉ ውበት ቦግ እንዲል ያድርጉ። ከሳቸው በፊት የነበሩት አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት እንዳሉትም ከያንያን ለሰብአዊ ፍጡር የተስፋ ምስክሮች ይሁኑ ብለው በማስተጋባት፡ ውበትን ተንከባከቡ። ውበት ደግሞ በዚህ በምንኖርበት ዘመን የቆሰለውን የሰው ልጅ ልብ ይፈውሳል እንዳሉ የገለጡት ዶኒኒ አያይዘው፥

ውበትን ለማስተንተን ቆም ካልተባለ ነገር ሁሉ የአመጽ ማስተግበርያ ሆኖ ይቀራል

ያ እ.ኤ.አ. በ 1542 ዓ.ም. የተመሠረተው ለላቁ ከያንያን የሚሰጠው ጥንታዊ ሽልማት ምክንያት እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. የሽልማቱ ሥነ ስርዓት በተካሄደውበት ወቅት ቅዱስንታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ተካሂዶ ለነበረው ዓውደ ጉባኤ ባስደመጡት ንግርር ከያኒ ማኅበራዊ ሕይወት ባለበት ሥፍራ ሁሉ ማኅበራዊው ሰብአዊ እንዲሆን ያድረጉ ያሉትን ሃሳብ ጠቅሰው ሰብአዊ በማድረጉ ሂደት ከፍ የሚያደርግ ያየከተሞቻችንና የህልውናችን ጥጋ ጥጉ ክልል ሰብአዊ ብቃት ያለው እንዲሆን የሚያደርግ ሰብአዊ ውበት ከከተማዎች ቅዋሜ በፊት እንዲቀድም የሚያደርግ ነው፡ ደራሲው ኢታሎ ካልቪኖ እንደሚለውም ከተሞቻችን ሕልም ምኞትና ፍርሓት ይወልዳቸዋል። ይኸንን መሠረት በማድረግም ቅዱስነታቸው ከተሞቻችን ያየን እንደሆን ፍርሃት የወለዳቸው ናቸው የሚመስሉት። ግንብ መገንባት ለያይ አጥሮ ከፍ የሚልባቸው ሆነዋል፡ መልካሙን ህልማችንን በተለይ ደግሞ የወጣቱን ህልም በመካደ ስልት የሚገነቡ ናቸው። ይሴባሕ በተሰኘው ዓዋዲ መልእክታቸው ዘንድ ውበት ግብረ ሕንጸትና ተፈጥሮን ለመንከባከብ ዓቢይ ግምት የሚሰጥ እንጂ ውበት ብቻ በሚለው ውበትን ከጥልቅ ትርጉሙ በመነጠል ሃሰተኛ ውበት ማስፋፋት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዘነ ይሆናል።  ምሉእ ሰብኣዊነትና የተፈጥሮ ምሉእነት ግምት የማይሰጥ ውበት ውበትን ላልተገባ አጠቃቀም እንዲውል ያደርጋል እንዳሉ ገልጠዋል።

ለዘንድሮው ሽልማት ብቁ ተብለው የተመረጡት ከያንያን፡ በሥነ ሙዚቃና ሥነ ድርሰት በጥዑም ውሁድ ሙዚቃዊ ቅኝት የበለጠ ሥራ ላበረከቱት ዶክተር ክያራ በርቶሊዮን፡ በየሥነ ግጥም ምርምር በተለይ ደግሞ ወቅታዊው ሥነ ግጥም ርእስ ዙሪያ ድንቅ የምርምር ሥራ ላበረከቱ ለገጣሚ የሥነ ግጥም ሊቅ ዶክተር ክላውዲዮ ካንፋሊዮኒና ለአባ ዳቪድ ማሪያ ቱሮልዶን፡ በቦሎኛ ለሚገኘው ለቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መዘምራን መምህር ሚከለ ቫነሊን፡  ፀሐይ ለተሰየመው የሙዚቃ ቡድን መሥራች ደራሲና ሙዚቀኛ ፍራንቸስኮ ሎረንዚን መሆናቸው ዶኒኒ ገልጠው። ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት መልእክት፥ ሁሉንም ከያንያን ለዚያች የእግዚአብሔር ውበት እውነተኛ ብልጭታ ሁለተና ውበት ለሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ አወክፋለሁ በሚል ጸሎት ማጠቃለላቸው አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.