2016-12-07 13:15:00

ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር ርኅሩ መሆኑን የማያውቅ ሰው የክርስትና እምነት ዋንኛ እሴቶችን አያውቅም ማለት ነው አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንታንው እለት ማለትም በኅዳር 27/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት እግዚኣብሔር ርኅሩ መሆኑን የማያውቅ ሰው የክርስትና እምነት ዋንኛ እሴቶችን አያውቅም እንደ ማለት ይቆጠራል ማለታቸው ተገለጸ።

በእለቱ በተነበበው የወንጌል ቃል ጠፍቶ ስለትገኘው በግ ምሳሌ ያወሳ የነበረ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚህ ምሳሌ ላይ ተመርኩዘው እግዚኣብሔር ማንኛውንም ዓይነት መንገድ ተጠቅሞ እኛን ከጠፋንበት ለመፈልግ እንደ ሚወጣ ጨምረው ገልጸዋል።

እግዚኣብሔርን ተንከባካቢ እንደ ሆነ፣ በርኅራኄ እንደ ሚመለከተን፣ እኛን ለማዳን ሁሉንም ጥረት እንደ ሚያደርግ አንድ ዳኛ አድርገን መቁጠር እንችላለን በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የሚመጣው ሊፈርድብን ሳይሆን ልያድነን ነው” ካሉ ቡኋላ እርሱ እያንዳንዳችን በተናጥል ይወደናል፣ በየስማችንም ይጠራናል ከነማንነታችንም ይቀበለና ብለዋል።

በዛሬው ወንጌል ላይ የሰማነው የጠፋው በግ ምሳሌ፣ ይህ በግ የጠፋው እውነትም መንገድ ጠፍቶበት ሳይሆን “የታመመ ልብ ስለነበረው ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከጌታው ለመራቅ ፈልጎ በሸሸበት ወቅት ውስጡ ጨልሞ ነበር ብለዋል።

እግዚኣብሔር እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮችን በሚገባ ስለሚገነዘብ መቼም ቢሆን የጠፋውን በግ ከመፈለግ ታክቶ አያውቅም ያሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ረገድ የይሁዳን ታሪክ መመልከት አግባብነት አለው ብለዋል።

“ይሁዳ በወንጌል ውስጥ ከተጠቀሱ ምሳሌዎች በተሻለ ሁኔታ የጠፋውን በግ በሚወክል መልኩ የተገለጸው የእርሱ ታሪክ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “መራራ የሆነ ልብ ያለው ሰው፣ ሁልጊዜም ቢሆን ሌሎችን ለመውቀስ የማይሰንፍ፣ ከሁሉም ጋር መገናኘት የማይፈልግ ሰው ነበር ዩሁዳ ብለዋል። አብሮ ከመኖር የሚመነጨውን ጣፋጭ የሆነ ሕይወት ከሌሎች ጋር መኖር ስለማይፈልግ ይሁዳ ይህንን ጣፋጭ የሆነ ሕይወት አጣጥሞ አያውቅም ያሉት ቅዱንስነታቸው እርካታ የማይሰማው ሰው እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

ይሁዳ በልቡ ውስጥ ጨለማ በመኖሩ ምክንያት ነው ከመንጋው የተለየው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአጠቃላይ ጨለማ ሁለት ዓይነት ሕይወት እንድንኖር ያደርገናል፣ ይህም ያለመታደል ሆኖ በሚያሳምም መልኩ በብዙ ክርስቲያኖች፣ በካህናት እና በጳጳሳት ሕይወት ውስጥ እንደ ሚንጸባረቅ ሁለት ዓይነት ሕይወት እንደ ሚመሩ ሰዎች ነው ብለዋል።

ይሁዳ ራሱ ከመጀመሪያዎቹ ጳጳሳት አንዱ ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እርሱም እንደ ጠፋ በግ ሆነ፣ የጠፋው በግ ምን ማለት እንደ ሆነ መረዳት ያስፈልጋል፣ እያንዳንዳችን የጠፋውን በግ ገጽታ የሚወክሉ ነገሮች በውስጣችን ይገኛሉ በለዋል።

ልብ በሚታመምበት ወቅት በጉ እንዲቅበዘበዝ ያደርገዋል ይህንንም በሽታ የሚዘራው ሰይጣን ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነትቻው ይህንንም እውነታ በተከፋፈለው የይሁዳ ልብ ውስጥ መመልከት ይቻላል ብለዋል። ይሁዳ በመጨረሻው ሰዓት ያ የተከፋፈለው ልቡ በማኅበረሰቡ ውስጥ ያስከተለውን መጥፎ መዘዝ በተገነዘበበት ወቅት፣ ልቡ ጨለማ በመሆኑ የተነሳ በሰይጣን ተሞልቶ ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም የጨለማ ሕይወት ከመንጋው ተለይቶ እንዲጠፋ አስገድዶት የጌታ ያልሆነውን ብርሃን ለመፈለግ መውጣቱን ገልጸው ይሁዳን አጋጥሞት የነበረው ትክክለኛው የጌታ ብርሃን ሳይሆን ልክ አሁን በየመንገዱና በእየቤቱ እንደምንመለከተው የገና መብራት ዓይነት ነበር በእዚህም የተነሳ ይሁዳ ተስፋ ቆርጦ ነበር ብለዋል።

መጽሐፍ ቅዱሳችን “እግዚኣብሔር መልካም ነው፣ የጠፋውን በግ ለመፈለግ ከመውጣት ታክቶ አያውቅም” እንደ ሚል በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይሁዳ ራሱን ማጥፋቱ መጸጸቱን የሚያሳይ እንደ ሆነም መጽሐፍ ቅዱሳችን ይገልጻል ብለዋል።

“ጌታ ‘መጸጸት’ የሚለውን ቃል በመገንዘብ ይሁዳን ከእርሱ ጋር ይኖር ዘንድ እንደ ሚያመጣው አምናለሁ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ ድረስ እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር በመሆነ በእርሱ ነብስ ውስጥ ተግባሩን ያከናውን ስለነበረ ነው በለዋል።

በገና በዓል የምንቀበለው መልካም ዜና የሚያመጣልን መልዕክት ይህንኑ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም በቅንነት በመደሰት ልባችንን ወደ መቀየር እንድናመራ በጌታም እንድንጽናና ነው እንጂ በመሸሽ መጽናናትን እንድንፈልግ አይደለም ብለዋል።

ኢየሱስ የጠፋውን በግ ባገኘበት ወቅት ምንም እንኳን ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እየሱስ ላይ ደርሶበት የነበረ ቢሆንም አልነቀፈውም ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ስቃይ የሚቀበልበት ሰዓት በአታክልቱ ቦታ በነበረበት ወቅት ይሁዳን ‘ጓደኛዬ’ በሚል አኩኋን ነበር የጠራው ይህም የጌታን እንክብካቤ ያሳያል ብለዋል።

“እግዚኣብሔር ተንከባካቢ እንደ ሆነ የማይረዳ ሰው የክርስቲያን እምነት ዋንኛ አስተምህሮን አያውቅም ማለት ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እግዚኣብሔር ይንከባከበው ዘንድ የማይፈቅድ ሰው እርሱ የጠፋ ሰው ነው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት በእግዚኣብሔር የምንጽናናበት ምክንያት ርኅራኄ በማሳየት አድኖን ወደ ቤተ ክርስቲያን መልሶ ስለሚቀላቅለን ነው ካሉ ቡኋላ “የገናን በዓል በምንጠባበቅበት በአሁኑ ወቅት፣ በርኅራኄ ልያጽናናን የሚመጣውን የእግዚኣብሔርን ኋይል በምንጠባበቅበት በአሁኑ ወቅት ኋጥያታችንን በቅንነት መረዳት እንድንችል እግዚኣብሔር ፀጋውን ይስጠን ዘንድ መጠየቅ ያስፈልጋል” ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠቃለዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.