2016-12-07 16:41:00

ቅዱስ ከፈን (ቅዱስ መግንዝ) በሥነ ምርምርና እምነት


“አየና አመነ” ቅዱስ ከፈን በሥነ ምርምርና እምነት ምስጢረ ትንሣሴ ማወጅ በሚል ርእስ ሥር እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 13 እስከ ታህሳስ 14 ቀን 2016 ዓ.ም.  በጳጳሳዊ ረጂና አፖስቶሎሩም ባለው የጉባኤ አዳራሽ ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ ዛሬ በቫቲካን ረዲዮ ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መርሐ ግብር ዙሪያ የተሰጥው ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ  ጋብሪኤላ ቸራዞ አስታወቁ።

በከፈኑ ላይ ታትሞ የሚገኘው ምስል የማን ነው። ያ ሰው ማን ነው የተሰኙት ጥያቄዎች ሥነ ምርምርም ሆነ የተለያዩ ዘርፈ ጥናቶች መልስ ለመስጠት ሙከራ አድርገዋል እያደረጉም ነው፡ ይኸንን ጥያቄ ለረዥም ዓመት ሲያጤኑና መልስ ለመስጠት የሞከሩ የሥነ ቅዱስ ከፈን ተመራማሪና ሊቅ የሰራዊተ ክርስቶስ ማኅበር አባል አባ ሄክቶር ጉወራ የዛሬ አንድ ዓመት በፊት ከዚህ ዓለም መለየትና ከፈኑ በተኖረበት በቶሪኖየ የዛሬ 10 ዓመት በፊት ስለ ቅዱስ ከፈን የቀረበው ትርኢት ምክንያት በማድረግ የሚካሄድ መሆኑ የሥነ ምርርና እምነት ተቋም ዋና አስተዳዳሪ የሰራዊተ ክርስቶስ ማኅበር አባል ኣባ ራፋኤል ፓስኳለ፥ ቅዱስ ከፈኑን ማበሰር ምን ማለት ነው፡ ከፈኑን ወደ ቃል ለውጦ ለሌላው ማሳወቅ ። ከፈኑ ለዛሬው ዓለም መልእክት ይኖረዋልን? ሰዎች ቅዱስ ከፈኑ የሚናገረውን ቃል ለማንበብ ለማዳመጥ ይችላሉን? የተሰኙት ጥያቄዎች የሁለቱ ቀናት ዓውደ ጥናት መልስ ለመስጠት ይሞክራል። ቅዱስ ከፈን በአራቱ ወንጌላውያን ሥር ማንበብ፡ በዚህ ብቻ ሳይታጠርም በዚሁ ቅዱስ ከፈን ዙሪያ ከተደረሱት መጻሕፍት ውስጥ የቶሪኖ ምሥጢር በሚል ርእስ ሥር በመክሲካዊ አዳ ግሮሲ ቀጥሎም የእግዜአብሔር ሌባ፡ መቶ አርባ ዘጠኝ ዓምት እና ጲጥሮስ ዮሴፍና ከፈኑ በሚል ርእስ ሥር የተደረሱት መጻሕፍት ሥር ቅዱሱን ከፈን ለማንበብ ይሞከራል። ከፈኑን መተንተን ማንበብ የሚናገረውን ቃሉና መልእክቱን ማዳመጥ ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ይሉት እንደነበም ቅዱስ ከፈን ለሰብአዊ ማስተዋልና አእምሮ ተጋጦ ነው። ስለዚሁ ሁሉም ይኸንን ተጋርጦ ገጥሞ በከፈን ውስጥ ያለው መልእክተ ቃሉ ለማንበብ ተጠርተዋል። ከፈኑና በከፈኑ ታትሞ የቀረው ምስል ወደ ኢየሱስ ይሸኘናል።

ከፈኑ ቃል ነው ቋንቃም ነው እውነተኛ የተኰነ ታሪክም ነው በማለት ነፍሰ ኄር አባ ሄክቶር ጉወራ ያሉት ቃልና በከፈኑ ዙሪያ ያሰፈሩት ጽሑፍና ሰነዶች ዙሪያ ጽማሪ የሚቀርብበት ዓውደ ጥናት መሆኑ ቸራዞ ገልጧል።








All the contents on this site are copyrighted ©.