2016-12-07 16:30:00

ማኅበረ ክርስቲያንና የሂንዱ ሃይማኖት ተከታይ ማኅበረሰብ፥ ለዓለም ብርሃንና መንገድ ለመሆን የጋራ ውይይት


“ብርሃንና ሰላም፡ ማኅበረ ክርስቲያንና የሂንዱ ተከታዮች ለጋራ ውይይት” በሚል ርእስ ሥር የተለያዩ ሃማኖቶች የጋራ ውይይት የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤት አነሳሽነት ከጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ብሔራዊ የአቢያተ ክርስቲያን ለውህደና ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ድርገት ከኢጣሊያ ሳንታና ድሃርማሳምጋ ሂንዱ ሃይማኖት ኅብረት ካቶሊካዊ የአፍቅሮተ ዘቤት እንቅስቃሴ ሃይማኖቶች ለሰላም የተሰየመው በኢጣሊያ ከሚገኘው ጽሕፈት ቤት  ጋር በመተባበር ያሰናዳው ዓውደ ጉባኤ ሮማ በሚገኘው በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የጉባኤ አዳራሽ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 6 ቀን 2016 ዓም. ከተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራ ውይይት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲና ዣን ልዊስ ታዉራንና የጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ የኢየሱሳን ማኅበር አባል አባ ከይኖት አድረስ በተከታታይ ባስደመጡት ንግግር መጀመሩ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ገለጡ።

ብፁዕ ካርዲናል ታውራን፥ ዓመጽ መከፋፈልና አለ መቻቻል የሚዘሩትን ለመቃወም የሰላም መልእክተኞና ሰላም ገንቢዎች የሚያካሂዱት ዓውደ ጉባኤ መሆኑ አሳስበው፡ በዚህ ዓውደ ጉባኤ መገኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውም ገልጠው በወዳጅነት የእርስ በእርስ መከባበርና መቀባበል መንፈስ ሰላምና በሰላም በሰላማዊ የጋራ ኑሮ ውህደትና ቅንጅት በሕዝቦች መካከል የመገንባቱ ሂደት የእያንዳንዱ ሃይማኖት ኃላፊነት ነው እንዳሉ ዘጋቢ ማሶቲ ገልጠው እ.ኤ.አ. በ 2009 ዓ.ም. በህንድ ቦምበይ ከተማ በተካሄደው ተመሳሳይ ዓውደ ጉባኤ ለመጀመሪያ ጊዜ መሳተፋቸውና ቀጣዩ ዓውደ ጉባኤ በሎንደን ከዛም በዋሽንግተን መካሄዱ አስታውሰው የተለያዩ ኃይማኖቶች አማኞች በሚፈጽሙት ቃለ እምነት አማካኝነት በመገናኘት የሃይማኖታችን ማእከላዊ እሴት በማስተዋወቅ ሃይማኖተኛነት ገጠመኞቻችንን ስንለዋወጥ በእውነቱ ለእርስ በእርስ መከባበር የሌላው ሃይማኖት ተከታይ ሕይወትና እምነት የማክበሩ ኃላፊነት የሁሉም መሆኑ ያረጋግጣል። እንተም በተራህ ኃላፊነቱን እንድትወጣ ያነቃቃሃል።

ዛሬ ዓለማዊነት ትስስር እጅግ በተስፋፋበት ወቅት ይኽ ትስስር በተለያዩ ኃይማኖቶች መካከል የጋራ ውይይት እንዲበረታ ይደግፋል የጋራው ውይይት አማራጭ ሳይሆን አስፈላጊ ነው። ሃይማኖቶች ፍቅር አንድነት መተሳሰብን እንጂ ጥላቻን አያበስሩም ይኸንን ሃሳብ ዓመጽ ሃይማኖትን የሚጻረር የውድምት መሣሪያ ነው በማለት ባንድ ወቅት ቅዱስነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ያሉትን ሃሳብ ጋር አያይዘው ካብራሩ በኋላ ሃይማኖቶች የችግር መንስኤ ሊሆን አይችሉም፡ ስለዚህ ሃይማኖቶች ለየት ባለ መልኩ ባክራሪያን ስውር ፍላጎት ለሚፈጥሩት ችግር መፍትሔ ናቸው። ሃይማኖት መፍትሄ እንጂ ችግር አይደለም። አክለውም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን ጠቅሰው  ሃይማኖቶች ሰላም ይቅር ባይነት መማማር ቁስሎችን ፈዋሽ ጠባብነትና ያስተሳሰብ ዝግታማነትን እንዲቀረፍ በመተባበር የበለጠ ዓለም ለመገንባት የሚያነቃቃ የሰላም መሣሪያ ነው እንዳሉ ማሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.