2016-12-05 16:25:00

ሰላም በኰሎምቢያ


በኰሎምቢያ መንግሥትና በአገረ ኰሎምቢያ አብዮታዊ ግንርባ መካከል የተደረሰው የሰላም ስምምነት መሠረት ገዛ እራሱን ፋርክ በሚል አህጽሮተ ቃል የሚጠራው የኰሎምቢያ አብዮታዊ ግንባር ተዋጊ ኃይሎች ትጥቃቸውን መፍታት እንደጀመሩ ሲነገር። ይኸንን ተከትሎም በመግሥት ወታደሮች ቍጥጥር ሥር የሚገኙት በጠቅላላ በወህኒ ቤት ተይዘው የሚገኙት የአቢዮታዊው ግንባር ታጣቂ ኃይል አባላት ነጻ ይለቀቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ከአገሪቱ የሚሰራጩ ዜናዎች ይጠቁማሉ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም የሰላሙ የስምምነት ሰነድ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ለኵሎምቢያ ሕዝብ ውሳኔ ቀርቦ ሕዝብ ውድቅ ያደረገው ቢሆንም ቅሉ መግሥትና ታጣቂው ኃይል ፍሪማቸውን በማኖር የተቀበሉት የሰላም ሰነድ ያሰፈራቸው መጠይቆችና ቅድመ ሁነቶች ለማክበር ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ቃለ መጠይቅ ያከናወኑት በኢጣሊያ ሞደናና ረጆ ኤሚሊያ መንበረ ጥበብ የታሪክ መምህር የታሪክ ሊቅ ፕሮፈሰር ጃኒ ላ በላ ገልጠው፡ ይኽ በመገናኛ ብዙኃን በኩል ዳግማዊ ስምምነት ተብሎ የሚገለጠው የሰላም የስምምነት ሰነድ በመንግሥትና በታጣቂው ኃይል መካከል መተማመን እንዲኖር ከማድረጉም አልፎ ሰነዱ ያሰፈራቸው ጥያቄዎች እየተተገበሩ ናቸው። ስለዚህ የአብዮታዊ ግንባር ታጣቂው ኃይል ትጥቁን ከፈታ በኋላ ከሰላማዊ ሕዝብ ጋር ተቀላቅሎ ለመኖር የሚያስችለው እድል መፍጠር ሰላማዊ ኑሮ እንዲጀምሩ ተገቢ ድጋፍና ትብብር እንዲያገኝ የማድረጉ ጉዳይና በጅምላ ቅትለ ተጠያቂ የሆኑትን ለፍርድ ለማቅረብ እንዲቻልም አንድ የሰላምና የፍትሕ ፍርድ ቤት ማቋቋም የተሰኙት የስምምነቱ ሰነድ ካሰፈራቸው ቅድመ ሁነቶች ውስጥ ቀጥለው እግብር ላይ ይውላሉ ተብሎም ይጠበቃል። ተጠያቂዎችን ለፍርድ ማቅረብ የሚለው ጉዳይ ቀላል ሥራ እንደማይሆንም ገልጠው  ይኽ አገሪቱን ለ 50 ዓመታት ያደማው የእርስ በእርስ ግጭት ያደረሰው የሕይወት እልቂት ቀላል አይደለም በመሆኑም ቤተ ክርስቲያን ፍርድ ሳይሆን ፍትሕና እርቅ እንዲረጋግጥ በማድረግ ሂደት እንዲመራ ጥሪ በማቅረብ ላይ ተገኛለች። ተፈላጊው ፍትሕና እርቅ ነው። የጥላቻ መንፈስ ማስወገድ ነው። የመበቀል ፍላጎት እንዲያበቃለት ነው። ከዚህ አንጻር ሲታይ ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉ ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ሰላም እንዲረጋገጥ ያደረገችው ጥረት አቢይ ግምት የሚሰጠው ሆኖ እየደጋገመች እያቀረበችው ያለው ጥሪ ማኅበራዊ እርቅ ሰላም ሙሉ በሙሉ እንዲረጋገጥ የሚያደርግ መሆኑ ላይ  የጽና ነው ብሏል።

በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ባላት አቢይ ታማኝነትና ለሁሉም በተለይ ደግሞ በሰላም በስምምነት በእርቅ በምህረት በማነጽ ረገድ ሕዝቡ የአገር ጥቅም በማስቀደም ብሎም መንግሥት የሕዝብና የአገር ጥቅም እንዲያስቀድም በማሳሰብ የምትሰጠው የቃልና የሕይወት መስክርነት በሁሉም የሚታይ ብቻ ሳይሆን ተደማጭነት ያላት ታምኝ አስተማሪ መሆንዋ መንግሥትና ሕዝብ ጠንቅቀው የሚያውቁት በመሆኑም ከእርሷ የሚቀርብ የሰላም ጥሪ ሁሉ ተደማጭነት እንደሚኖረው በእርግጠኝነት ለመናገር ይቻላል በማለት ያካሄዱት ቃል ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.