2016-12-02 16:46:00

በርጠለመዎስ ቀዳማዊ፥ ከር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር የዓለምን ህመም ለመፈወስ


የወቅቱ ዓለም የከስተው ሰብአዊ ማሕበራዊ ውጣ ውረዶችና ችግሮች ሁሉ አሳሳቢ ናቸው። እክሎቹንም በተገቢ ምላሽ ለመቅረፍ የምንከተለው ዓላማ ጉዳዩን ለማጤንም ያለን የመቀራረብ ጠባይ ከሮማ ጳጳስ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር የሚያዋህድናቸው መሆኑ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ በቱርክ ኢስታምቡል ከተማ እ.ኤ.አ. ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በተከበረው በቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ ንግሠ በዓል በተሳተፉት የኵላዊት ቤተክርስቲያ ልኡካን በኩል ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት እንደገለጡ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከልምን ማኅበራዊ ነጻነት ፍቅርና መተሳሰብ የተሰኙት እሴቶች እንደሚገናኙና በዚህ በሚያገናኙዋቸው እሴቶች አማካኝነት በጋራ እንደሚያነቃቁና ግኡዛዊነት ሳይሆን ወንድማማችነት ስግብግብነት ሳይሆን ተካፍሎ መኖርን እንዲሁም ማንኛው ዓይነት ግለኝነትና ፍጆት ብቻ የሚል ባህል የሚቃወም በሃይማኖት ነጻነት ላይ የጸናው የሰው ልጅ የሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ እንዲረጋገጥ የሁለቱ ኣቢያተ ክርስቲያን መሪዎች የሚሰጡት ትምህርት በመካከላቸው ላለው መቀራረብ ምስክር መሆኑ አብራርተው ማንኛውም ዓይነት ርእዮተ ዓለም ፍጹም አድርጎ የማቅረቡ ሂደት በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል የሚታየው አልቀበል ባይነት መንፈስ በመካከላቸው ተጨባጭ መቀራረብ እንዳለ ያረጋግጣል የሚል ሃሳብ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ ባስተላለፉት መልእክት እንዳሰመሩበት ሲር የዜና አገግሎት ይጠቁማል።

ለንግሠ በዓሉ የቅድስት መንበር ልኡካንን በመምራት ኢስታምቡ የተገኙት በዋና ጸሓፍቶቻቸው ብፁዕ አቡነ ብራይን ፋአልና ብፁዕ አቡነ አንድረያ ፓልሚየሪ የተሸኙት የክርስቲያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ መሆናቸው የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ በዚሁ የልኡካን ቡድን በቱርክ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ፖውል ሩሰል መሳተፋቸውም ጠቁሞ፥

የቅድስት መንበር ልኡካን ሱታፌ ለሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ግንኙነትና ውይይት አቢይ ግባት ነው

ብፁዕ ወቅዱ በርጠለመዎ ቀዳማዊ የቅድስት መንበር ልኡካን በበዓሉ መሳተፍ በሁለቱ አቢያተ ክርስትያን መካከል ያለው የፍቅር ወንድማማችነትና እውነት ውይይት  የደረሰበት ደረጃ አመርቂ ደረጃ የሚመሰክርና ውጤት መሆኑ ልኡካኑን ተቀብለው ባስደመጡት ቃል ገልጠው አክለውም በቅርቡ በአሲሲ በሁሉም የተለያዩ ሃማኖቶች የጋራ ጸሎት ስለ ሰላም በመሳተፉ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር እንደተገናኙና በዚያኑ ወቅትም ሁሉም አቢያተ ክርስቲያን እንዲሁም ሁሉም ሃይማኖቶች አክራሪነት ሽብርተኝነት በጠቅላላ ጸረ ሰላም የሆነውን ተግባር ሁሉ በጋራ ሕዝቦችን በሰላም ዙሪያ በማነጽ ነቅተው መቃወም በሚለው በቀረበው ጥሪ ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ውህደት እንዳላቸው ገልጠው በዚህ አጋጣሚም ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ የቅድስት መንበር ልኡካን እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. ሰማንያ ዓመት ዕድሜአቸውን ለሚያከብሩት ቅዱስ አባታችንን መልካም የልደት ቀን ምኞታቸውን እንዲያደርሱላቸው አደራ እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.