2016-11-28 16:15:00

ኢየሱሳውያን ልኡካን ማኅበር ለ 25 ዓመት በጠቅላይ አለቃነት የመሩት አባ ሃንስ ኮልቨንባኽ


በሰላሳ ሦስተኛው የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ ጉባኤ የተመረጡት የኢየሱሳውያን ማኅበር እ.ኤ.አ. ከ 1983 እስከ 2008 ዓ.ም. ለ 25 ዓመት በጠቅላይ አለቃነት የመሩት እ.ኤ.አ. በ 1928 ዓ.ም. በአገረ ሆላንድ የተወለዱት እ.ኤ.አ. በ 1961 ዓ.ም. በሊባኖስ ማዕርገ ክህነት የተቀበሉ በመካከለኛው ምስራቅ ለኢየሱሳውያን ልኡካን ማኅበር አለቃ በመሆን ያገለገሉት አባ ፐተር ሃንስ ኮልቨንባኽ እ.ኤ.አ. ህዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ስለ ነፍሰ ኄር አባ ፐተር ሃንስ ኮልቨንባኽ አስመልከተው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የዮሴፍ ራትዚንገር ማኅበር መስተዳድር ምክር ቤት ሊቀ መንበር የኢየሱሳውያን ማኅበረ አባል አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ፥ አባ ኮልቨንባኽ ጠቅላይ አለቃ አባ አሩፐ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለዩ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ አባ ደዛን ማኅበሩን ወደ ጠቅላይ አለቃ ምርጫ ለማሻጋገር የሚያስፈልገውን ቅድመ ዝጅት እንዲመሩ በማድረግ የሳቸው ወኪል አድርገ እንደሸሙዋችው ባጭር ጊዜ ውስጥ በተካሄደው አባ ቦርጎሊዮ (በመቀጠል የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት ሆነው የተሸሙት ከዛም ካርዲናል ለመሆን የበቁትና አሁን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ፍራንቸስኮ) በአርጀንቲና የኢየሱሳውያን ማኅበር አለቃነት እንዲሁም አሁን በቅርቡ በ36ኛው ጠቅላይ ጉባኤ የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ ሆነው የተመረጡት አባ ሶዛ በዚያኑ ወቅት ወጣትና በቨነዝዋላ የኢየሱሳውያን ማኅበር አለቃ በነበራቸው ኃላፊነትና እሳቸውም አባ ሎምባርዲ የኢጣሊያ የኢየሱሳውያን ማኅበር በነበራቸው የወኪልነት ሥልጣን መሰረት በተሳተፉበት በ 33ኛው የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ ጉባኤ ለማኅበሩ ጠቅላይ አለቃነት የተመረጡ ማኅበሩን ለ25 ዓመት የመሩ ምንም’ኳ ኤውሮጳዊ አናስር የነበራቸው ቢሆንም በመካከለኛው ምስራቅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አለቃ በመሆን መላ ሕይወታቸው በዚያ ክልል በተለይ ደግሞ በሊባኖስ ልኡከ ወንጌል ሆነው ያገለገሉ ጥንቁቅ አስተዋይ ሁሉን የማኅበሩ ጉዳይ በተባባሪዎቻቸው ብቻ ሳይሆን በቀጥታ በመከታተል የማኅበሩ ጥልቅና ሰፊ ግንዛቤ የነበራቸው ለሁልም የማኅበሩ አባላት ቅርብ እንደነበሩ አስታውሰው፡ ወደ ሰማንያ አመት ሲጠጋቸው ምንም’ኳ የኢየሱሳውያን ጠቅላይ አለቃ ሆኖ መመረጥ ለመላ የሕይወት ዘመን የሚል ቢሆንም ቅሉ በገዛ ፈቃዳቸው አቅሙም ብቃቱም በእድሜ መግፋት ምክንያት ያንሰኛል ብለው የጠቅላይ አለቃነት ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ልቅዱነታቸው ልሂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንደ ፈቃደዎት በማለት ማመልከቻ አስገብተው ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አወንታዊ ምላሽ አግኝተው ከሳቸው በኋላ የኢየሱሳውያን ማኅበር ጠቅላይ አለቃ እንዲሆኑ ማኅበሩ ባካሄደው 35ኛው ጠቅላይ ጉባኤ አባ አዶልፎ ኒኮላስ በገዛ ፈቃዳቸው በእድሜ መግፋት ምክንያትም ሃላፊነቱ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደ ፈቃድዎት ላስረክብ በማለት ጠይቀው የይሁንታ ምላሽ አግኝተው ይኸው ማኅበር በቅርቡ ባካሄደው 36ኛው ጠቅላይ ጉባኤ አባ ሶዛን መርጧል።

አባ ኮልቨንባኽ በሊባኖስ የቅዱስ ዮሴፍ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩና የማኅበረ ጠቅላይ አለቃ ሆነው ለ 25 ዓመት አገልግለው በገዛ ፈቃዳቸው ወደ ሊባኖስ ተመልሰው የመንበረ ጥበቡ ቤተ መዝገብ ተራ ሠራተኛ በመሆን አገልግለዋል። የዋህ ጥንቁቅ ወንጌላዊ ድኽነት የኖሩ አብነታዊ ሕይወት ያስተጋቡ ናቸው። ባንድ ወቅት ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው አበይት የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ባለ ሥልጣናት ብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት ላካሄዱት መንፈሳዊ ሱባኤ ሰባኬ እንዲሆኑ መርጧቸው እንደነበርም ያስታወሱት አባ ሎምባርዲ አያይዘው እኚህ የቅዱስ ኢግናዚዮስ ሰነዳች ሊቅ የማኅበሩ መንፈሳዊነት ጥልቅ አዋቂና ተንታኝ በእውነቱ ማኅበሩን በመሩበት 25 ዓመት ውስጥ በቅዱስ ኢግናዚዮስ መንፈሳዊነት ማኅበሩት ያሳደጉ ናቸው ብሏል።

በመጨረሻም ማኅበሩን በቤተ ክርስቲያን ከቤተ ክርስቲያን ለቤተ ክርስቲያን በሚል መንፈስ የመሩ ናቸው። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያናዊነት መቼም ቢሆን እንዳይዘነጋ በቃልና በሕይወት ያስተማሩ በቤተ ክርስቲያን ሥር ልኡክ መሆን እንዲስተዋልና እንዲኖር ያደርጉ ናቸው በማለት አባ ሎምባርዲ ትውስታቸውን በሰጡት ቃለ መጠይቅ አጠር ባለ መልኩ ገልጠውልናን።








All the contents on this site are copyrighted ©.