2016-11-25 16:06:00

የቅድስት መንበርና የኢጣሊያ ረፓብሊክ አገር ክሌአዊ ግንኙነት


እ.ኤ.አ. ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢጣሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. መቀመጫ በሆነው በፋርነሲና ሕንጻ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ፓውሎ ጀንቲሎኒ የቅድስት መንበር አቻቸው የቅድስት መንበር የውጭ ግኑንኘት ጉዳይ ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሪቻርድ ገላገር ተቀብለው ማነጋገራቸው የግንኙነቱ ስነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ አስታወቁ።

ጓራሺ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት እንደተቻለውም በተካሄደው ግኑኝነት አንገብጋቢው የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታና ከዚሁ ጋር በማያያዝም የስደተኞች ጸአት ርእስ ዙሪያ ሰፊ ውይይት እንዳካሄዱና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሪቻርድ ገላገር የሶሪያና የኢራቅ ሁከት መንሳኤውና እንዴትስ እልባት ያግኝ በሚለው ጥያቄ ዙሪያ እንደተወያዩና ቅድስት መንበርና ኢጣሊያ አሳሳቢው የመካከለኛው ምስራቅ ሁኔታ እልባት አሰጭ ሃሳብ ላይ ስምምነት እንዳላቸው ያረጋገጠ ግንኙነት እንደነበርም ለማውቅ ተችሏል።

በዚህ አጋጣሚም እ.ኤ.አ. ህዳር 23 ቀን 2016 ዓ.ም. የረፓሊካዊት ሶሻሊስት ቨትናም ርእሰ ብሔር ትራን ዳይ ኩዋንግ በአገረ ቫቲካን ይፋዊ ጉብኝት በማካሄድ ከቅዱስ አባታችን ጋር ያካሄዱት ግንኙነት አመርቂ እንደነበርም የሚታወስ ሲሆን። ይኸንን ጉዳይ በተመለከተና በተጨማሪም የምሕረት ቅዱስ ዓመት ሂደትና የፍጻሜ ስነ ሥርዓት የተዋጣለት እንደነበር ብፁዕ አቡነ ገላገር በተካሄደው ግንኙነት ጠቅሰው፡ የጋራ ጥቅም ብሎም ዓለም አቀፋዊ ጥቅም ላይ በማተኮር የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ መሰረታዊ ጥያቄ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውና በታካይነትን በቨትናም እግብር ላይ የዋለው በአገሪቱ የሚገኙት ሃይማኖቶች በቀጥታ የሚመለከተው ሕግ መንግስት በአገሪቱ የሚገኙትን የተለያዩ ሃይማኖቶች በማሳተፍ አማክሮ ወጥኖ ያረቀቀው መሆኑንም ገልጠው፡ የዚህ ዓይነቱ አሰራር ለመልካም ግኑኝነት ለማኅበራዊ ሰላም መሰረት ነው እንዳሉ ጓራሺ ገልጠው፡ የኢጣሊያው የውጭ ጉዳይ ሚኒ. ጀንቲሎኒ በበኩላቸውም፥ የኤውሮጳ ኅብረት በየቀኑ በሚቀያየሩትን በተለያዩ አገሮች ከራራ ፖሊቲካ አቀራረቦች በሚከስትዋቸው መርሃ ግብሮች አማካኝነት የሚቀያየር ፖለቲካ ሳይሆን የኅብረቱ መለያ የሆነ መሠረታዊ ርእየት ያለው ነው። ስለዚህ ማንኛውም ዓይነት ለውጥ ይኽንን ራእይ የሚክድ አይደለም እንዳሉና የስደተኛው ጸዓት በተመለከተም ኢጣሊያ በቀጥታ ምላሽ ከሚሰጡት አገሮች በቀዳሚነት የምትጠቀስ ብቻ ሳይሆን የጽዓቱ መንስኤ ለይቶ መፍትሔ ለማሰጠት በሚደረገው ጥረት ስደተኛው ከሚነሳባቸው የአፍሪቃ አገሮች ጋር በቅርብ የምታከናውነው ምክክር ከፈረንሳይና ጀርመን ጋር በመተባበር ኤውሮጳዊ ቅርጽና ይዘት እንዲኖረው በሚደረገው ጥረት አብነት ነች እንዳሉ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.