2016-11-09 15:53:00

ብፁዕ ካርዲናል ፊሎኒ፥ በዛምቢያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብርቱ የወንጌላዊ ልኡክነት መንፈስ ያላት ነች


በአገረ ማላዊ በሰበካ ሊሎንግወ ክልል በማውላ የተገነባው አዲስ ካቴድራል እ.ኤ.አ. ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም. የመባረኩ ሥነ ስርዓት እንዲመሩ የአሕዛብ አስፍሆተ ወንጌል ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ፈርናንዶ ፊሎኒ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮበ ተሰይመው እ.ኤ.አ. ህዳር 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ማላዊ በመሄድ ከአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት፡ ውሉደ ክህነት ገዳማውያን የዘረአ ክህነት ተማሪዎችና አለማውያን ምእመናን ጋር በመገናኘት ምክርና አስተምህሮ ለግሰው በማላዊ የሚገኙት በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚተዳደሩትን የግብረ ሠናይ ማእከላትና የአገልግሎት መስጫ ማእከሎችን ጎብኝተው እ.ኤ.አ. ህዳር 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ለቅዱስ ዮሴፍ የተወከፈውን አዲሱን ካቴድራል የመባረክ ሥነ ስርዓት አከናውነው፡ እሁድ እ.ኤ.አ. ህዳር 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በሊሎንግወ በሚገኘው በቅዱስ ፓሪክ ቁምስና መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፡ በማላዊ ያካሄዱት ሐዋርያው ጉብኝት አጠናቀው እ.ኤ.አ. ህዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ዛምቢያ በመሄድ ሉሳካ የሚገኘውን የቅድስት እናቴ ተረዛ ማእከል ጎብኝተው እ.ኤ.አ. ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅዱስ ዶመኒክ የዘርአ ክህነት ትምህርት ቤት መሥዋዕተ ቅዳሴ አቅርበው  በዚያኑ ዕለት ከሰዓት በኋላም በገዳመ ክላሪሰ ጸሎተ ዘሰርክ መርተው እ.ኤ.አ. ህዳር 9 ቀን 2016 ዓም. በዛምቢያ ብሔራዊ የካቶሊክ ዓውደ ጉባኤ ባስደመጡት ቃል መጀመሩ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታውቋል።

ብፁዕነታቸው ከዛምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ጋር ተገናኝተው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ ሰላምታንና ሐዋርያዊ ቡራኬን አድርሰው የዛምቢያ ቤተ ክርስቲያን በአስፍሆተ ወንጌል የምታከናውነው ሐዋርያዊ አገልግሎት አመርቂነቱ ለኵላዊት ቤተ ክርስቲያን አቢይ ጸጋ ነው፥ በዚህ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በዛምቢያ ህልው የሆነችበትን 125ኛውን ዓመት እያከበረች ባለችበት ወቅት እዚህ  ከእናተ ጋር መገናኘቴ እቢይ ደስታ ይሰማኛል እድለኛም ነኝ። የካቶሊክ እምነት በዛምቢያ ያስፋፉት ቀደምት ልኡካነ ወንጌልን የከፈሉት መሥዋዕትነት ሁሉ የወለዳችሁ የእነዚያ የእምነት ጀግኖች ልጆች ናችሁ ካሉ በኋላ የመጀመሪያ ዛምቢያዊ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ዱፖንትን አስታውሰው በዛምቢያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ወንጌላዊ ልኡክነትን የምትኖር ልኡካነ ወንጌል የምታበረታታ አገር ነች እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ብፁዓን ጳጳሳቱ የሕይወት ቤተ መቅደስ ተብሎ የሚጠራውን ቤተሰብ እንዲያንጹ እንዲደግፉ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የወንጌል ሐሴት የተሰየመውን ሓዋርያዊ ምዕዳን ጠቅሰው እንዲሁም በ 2014 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ለሐዋርያዊ ጉብኝት አገረ ቫቲካንን የገቡትን የዛምቢያ ብፁዓን ጳጳሳት ተቀብለው የለገሱት ምዕዳን ወደ አሕዛብ የተሰየመው የቫቲካን ሁለተኛው ጉባኤ ውሳኔ በዛምቢያ ሕያው መሆኑ ያሰመሩበትን ሃሳብ ጠቅሰው አደራ ካሉ በኋላ ኢየሱስ ክርስቶስን ወደ አሕዛብ ከአሕዛብ ጋር ሆኖ ማድረስ በተለይ ደግሞ ይኸንን ተልእኮ በግንባር ቀደም የሚያነቃቁ የሚያቀናጁ ምስጢረ ጥምቀት በተቀበለ ሁሉ ዘንድ ያለው ኢየሱስን የማሳወቁ ተልእኮ በማነቃቃት ሊያበረታቱ ይገባል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

ጥሪ የሚያነቃቃ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎና የመገናኛ ብዙኃን የአጠቃቀሙ ብስለት

እጅግ ጥልቅ በሆኑ ሕንጸትና አበ ነፍስነት ብሎም ጥልቅ ማስተዋል ባጣመረ መንፈስ ጥሪ በማነቃቃት ወጣቶችን ለማነጽ በዛምቢያ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እየሰጠችው ያለው አገልግሎት የሚመሰገን ነው ብለው በዛምቢያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የመገናኛ ብዙኃን ወንጌልን በማስፋፋቱ ረገድ የምትከተለው ያጠቃቅሙ ስልት አድንቀው ወንጌላዊ ጥሪ እንዲያነቃቁ አደራ እንዳሉም ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.