2016-11-02 12:12:00

ቅዱስነታቸው የሁለተኛውን ቀንና የመጨረሻውን የስዊዲን ጉብኝታቸውን በመስዋዕተ ቅዳሴ አጠቃለሉ።


የሉቴራን ቤተ ክርስቲያን ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር 1517 በጊዜው የነበረው የቤተ ክርስቲያን ሁኔት ታድሶ ሊደረግበት ይገባል በሚል አቋም በይፋ መለየቷ የሚታወቅ ሲሆን ይህንን በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መኋከል የተፈጠረውን ልዩነት ለማጥበብና ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት መሠረታቸውን ያደረጉት በአንዱ ክርስቶስ ላይ በመሆኑ ከ50 አመት ወዲህ ተቀራርበው መስራት የሚያስችላቸውን አንድ አንድ ግንኙነታቸውን የማሻሻያ እርምጃ መውስድ በመጀመራቸው የተነሳ በግንኙነታቸው ላይ ከፍተኛ የሆነ አዎንታዊ ለውጥ እያስገኘ መምጣቱ ይታወቃል።

ይህንንም ግንኙነት ይፋዊ በሆነ መልኩ ለመግለጽ በማሰብ ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት የተለያዩበትን 500ኛ አመትን መዘከር አስፈላጊ ሆነ የተገኘ ሲሆን ይህንንም እለት ይፋዊ በሆነ መልኩ ለመዘከር በማሰብ “አብረን በተስፋ ከጥላቻ ወደ ኅብረት” የሚል ዓላማን ያነገበ 17ኛው የቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የሁለት ቀን ሐዋሪያዊ ጉብኝት ይህንኑ ሐሳብ የሚያጠናክርና ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት የእመንታቸው መሠረት ክርስቶስ በመሆኑ ከጥላቻ ይልቅ በአንድነት የክርስቲያናዊ እሴቶችን ለመመስከር የምያስችላቸውን የመሠረት ድንጋይ እንዲጣል ያደረገ ታላቅ እምርታን ያስገኘ ታሪካዊ ጉብኝት ነው።

ቅዱስነታቸው የሁለተኛውን ቀን የስዊዲን ሐዋሪያዊ ጉብኝታቸው መዳረሻ ያደረጉት ማክሰኞ እለት ማለትም በጥቅምት 22/2009 ቀደም ብሎ በወጣው መርዐ ግብር መሠረት ከማልሞ ከተማ 3 ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ በሚገኘውና 18ሺ ሰዎችን የመያዝ አቅም ባለው የእግር ኳስ መጫዎቻ ስፍራ ወይም ስታዲዬም ውስጥ በተዘጋጀው ሥፍራ መስዋዕተ ቅዳሴን ለማሳረግ የሄዱ ሲሆን በእለቱም ይህንን ለማከናወን ከዓለም የሉቴራን ፌደረሽን መሪዎች ጋር ሆነው የተገኙ ሲሆን በእለቱም በስዊዲን የሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ይህንን ሥርዓተ-ቅድሴ ለመታደም መገኘታቸውም ታወቅ ሲሆን በስዊዲን የሚገኙ የካቶሊክ ምዕመናን ምንም እንኳን ቁጥራቸው በቁጥር አንስተኛ የሚባል ቢሆኑም ቅዱስነታቸው በእለቱ ባሰሙት ስብከታቸው የቅዱሳንን ፈለግ መከተል እንደ ሚገባቸው ማሳሰቢያ መስጠታቸውም ታውቁኋል። ከካቶሊክ ምዕመናን ባሻገር በስዊድን የሚገኙ የተለያየ እምነት ተከታዮችም ከእያሉበት በመምጣት ሥርዓተ ቅዳሴን መታደማቸውና ለቅዱስነታቸው ሞቅ ያለ አቀባባል እንዳደረጉላቸውም ታውቁዋል። በተያያዘ ዜና በስዊድን አንድ የካቶሊክ ሀገረ ስብከት ብቻ እንደ ሚገኝ ተያይዞ የደረሰን ዜና አመልክቱኋል።

በመቀጠልም እንደ የአውሮፓዊያን የሥርዓተ-ሉጥርጊያ አቆጣጠር የተከበረውን “የሁሉም ቅዱሳን ቀን” መሠረት ያደረገ መስዋዕተ ቅዳሴ በቅዱስነታቸው መሪነት መፈጸሙን የታወቅ ሲሆን በእለቱ በሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት የተነበበው የእግዚኣብሔር ቃል በቀዳሚነት የተወሰደው ከመጀመሪያው የዩሐንስ መልዕክት 1.1-3 የተጠቀሰው ሲሆን በዚህም መልክቱ ሐዋሪያው “ከመጀመሪያ ስለነበረው ስለ ሕይወት ቃል እንጽፍላችኋለን፣ ይህ የሕይወት ቃል የሰማነውና በዐይናችን ያየነው፣ የተመለከትነውና በእጃችን የዳሰስነው ነው” የሚል ጭብጥ የያዘ ሲሆን የእለቱ የወንጌል ቃል ደግሞ የተወሰደው ከማቴዎስ ወንጌል 5.1-12 ላይ የተጠቀሰውና ወንጌላዊው “በመንግሥተ ሰማይ የምታገኙት ዋጋ ትልቅ ስለ ሆነ ደስ ይበላችሁ በደስታም ፈንድቁ” የሚልው የኢየሱስ ቃል ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው በነዚህ በተነበቡት የእግዚኣብሔር ቃል ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን አሰምተኋል።

ቅዱስነታቸው በእስፓኒሽ ቋንቋ ባደረጉት እና ወደ ስዊድን ቋንቋ በተተረጎመው ስብከታቸው እንደ ገለጹት ቅድስና የሚገለጸው ታላላቅ የሆኑ ተግባራትንና አስደናቂ ክስተቶችን በማከናውን ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በምስጢረ ጥምቀት ለገባናቸው ቃላት ሁልጊዜ ታማኝ ሆኖ በመኖር ጭምር እንደ ሆነ ገልጸኋል።

ዛሬ መላው ቤተ ክርስቲያናችን የሁሉም ቅዱሳን በዓልን ታከብራለች በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በዓል በምናከብርበት ወቅት በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ቅዱሳን የተባሉትን ሰዎችን  የምናስታውስበት እለት ብቻ አለመሆኑን ማስታወስ ይጠበቅብናል ካሉ ቡኋላ በጣም ብዙ የሚባሉ ክርስቲያን  እህቶቻችንና ወንድሞቻችን የክርስትና እምነታቸውን በእምነት ሙልኋት የኖሩና በፍቅር በመልካም ሁኔታ ኑረው ያለፉ ነገር ግን ይህ ማንነታቸው ተደብቆ የቀረ ብዙ ሰዎች እንዳሉም ማሰብ ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ በእርግጠኛነት ከነዚህ ውስጥ በርከት ያሉ የቤተሰብ አባሎቻችን፣ ዘመዶቻችን፣ ጓደኞቻችንና የምናውቃቸው ሰዎች ይገኙበታል ብለዋል።

ቅድስና ለእግዚኣብሔር እና ለወንድሞቻችን በፍቅር የሚደረግ ተግባርን ያካተተ መሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እናቶቻችንና አባቶቻችን ምንም እንኳን ሁል ጊዜ ቀላል ነገር ባይሆንም ሆን ብለው የራሳቸውን ፍላጎት ወደ ጎን በመተው ራሳቸውን ለቤተሰቦቻቸው አሳልፈ እንደ ሰጡ ሁሉ እኛም የቅድስናን መንገድ ለመከተል ራስን እስከ መርሳትና ራሳችንን ለሌሎች አሳልፎ እስከ መስጠት የሚያደርስ ታማኝ ፍቅር ሊኖረን ይገባል ብለዋል።

አንደኛውና ዋንኛው የቅዱስና መገለጫ ባሕሪ “እውነተኛ የሆነ ደስታን የተጎናጸፉ ሰዎች መሆናቸው ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህ ምክንያት የተነሳ ነው ብጽዕናቸውን ለዋቅ የምንቻለው ብለዋል። ቅዱስነታችው በስብከታቸው ወቅት በማሳያነት የጠቀሱዋቸው ቅዱስናን መካከል በ14ኛው ክፍለ ዘምን በስዊዲን ትኖር የነበረች ቅድስት ብርጅትና እርሳቸው በቅርቡ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ቅድስናዋን ያወጁላት የህክምና ባለሙያ የነበረችሁና የ20ኛ ክፍለ ዘመን ቅድስት ኤሊዛቤት ሄስልብላድ በዋቢነት ጠቅሰዋል። ቅዱስነታቸው እነዚህ ሁለት ቅዱሳን ላይ ተኩረቱን ባደረገው ስብከታቸው እንደ ገለጹት በጸሎታቸውና በተግባራቸው በክርስቲያኖች መካከል ግንኙነትና መስማማት እንዲፈጠር በማድረግ ይህንን የለውጥ ጎዳና በጋራ እንድንዘክር ረድተውናል ብለዋል።

እውነተኛ ደስታ አንድ ክርስቲያን የክርስቶስ ተከታይ መሆኑን የሚያሳይ የመታወቂያ ደብተሩ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የተጠራነው መከራንና በጊዜያችን የሚታየውን ጭንቀት በመንፈስ ቅዱስና በኢየሱስ ድጋፍ በመጋፈጥ ብጹዐን እንድንሆንና ኢየሱስን እንድንከተል ነው ብለዋል።

ቅዱሳን ያሳዩን አብነት አሉ ቅዱስነታቸው አሁን የሚያጋጥሙንን ተግዳሮቶች አዲስ በሆነ መንፈስዊ ጉልበት ለመጋፈጥ ያስችለናል ብለው ለዛሬ ክርስቲያኖች ይመጥናል ያሉትንና ወደ ቅድስና መንገድ እንድናመራ ይረዳል ያሉትን ለምሳሌም ለተረሱትና ለተገለሉት ሰዎች ሁሉ ቅርበትን የሚያሳዩ ብጹዐን ናቸው ፣ የጋራ መኖሪያችንን የሚጠብቁና የሚንከባከቡ የተባረኩ ናቸው፣ በክርስቲያኖች መኋከል አንድነት ይፈጠር ዘንድ የሚጸልዩና ለዚህም አበክረው የሚሠሩ ሰዎች ብጹዐን ናቸው የሚሉትን በብነት ጠቅሰዋል።

“የተወደዳችሁ ወንድሞቼና እህቶቼ! የቅድስና ጥሪ ለሁሉም ሰው የተላለፈ ጥሪ ስለሆነ  ይህንን ጥሪ ከጌታ በእምነት መንፈስ መቀበል ይኖርብናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ለተግባራዊነቱም ቅዱሳን ያበረታቱናል፣ ከእግዚኣብሔር ዘንድ ሆነው ስለሚያማልዱልን እኛም በበኩላችን ቅዱሳን ለመሆን አንዳች ለአንዳችን እናስፈልጋለን ብለዋል። ስለሆነም በጋራ ይህንን ጥሪ በደስታ መቀበል እንድንችል ፀጋውን ይሰጠን ዘንድ መጸለይ ያስፈልጋል ያሉት ቅዱስነታቸው ወደ ፍጻሜውም ለማድረስ አብረን መሥራት ይጠበቅብናል በማለት አክለው ገልጸኋል። በመንግሥተ ሰማይ የምትገኘውና የቅዱሳን ሁሉ እናት የሆነችው እናታችን ማሪያም ትረዳን ዘንድ ሁለንተናችንን በደራ እየሰጠናት፣ ክርስቲያኖች ሁሉ በሙልኋት ይዋሀዱ ዘንድና ብጹዐን እንድንሆን ኋይል ታሰጠን ዘንድ፣ በኅብረት ወደ ቅድስና መጓዝ እንድንችል ታማልደን ዘንድ መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኋል ስብከታቸውን አጠንቀኋል።   

 








All the contents on this site are copyrighted ©.