2016-10-27 13:20:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅርቡ ማለትም በጥቅምት 21/2009 ሲውዲንን እንደ ሚጎበኙ የቫቲካን የሕትመት ቢሮ ገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በቅርቡ ማለትም በጥቅምት 21/2009 ሲውዲንን እንደ ሚጎበኙ የታወቀ ሲሆን ዓላማውም የሉቴራን ቤተ ክርስቲያ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ተሃድሶን በመሻት እንደ አውሮፓዊያ የቀን አቆጣጠር 1517 ተገንጣል በወጣችበት በእነዚህ 500 አመታት ውስጥ በካቶሊክ እና በሉቴራን አብያተ ክርስቲያናት መኋከል “ከአሁን ቡኋላ የሚተያዩት እንደ አንዱ የአንዱ  ታቃዋሚ ሳይሆን” ነገር ግን ሕብረት ያላቸው መሆኑን ለመገልጸ የታሰበ ግንኙነት በመሆኑ ግንኙነቱን ታሪካዊ እነ ሚያደርገው ተገልጹአል።

በቅድስት መንበር የሕትመት ቢሮ አላፊ የሆኑ አቶ ግሬክ ቡሬክ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 16/2009 ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በጥቅምት 21/2009 ዓ.ም በሲዊድን የሚያደርጉትን ጉብኚት አስመልክተው ለጋዜጠኞች እንደ ገለጹት ቅዱስነታቸው እና የዓለም አቀፍ የሉቴራን ፌዴሬሽን ዋና ጸኋፊ በጋራ በሐይማኖቶች መኋከል ሕብረት ይመጣ ዘንድ በሲዊድን በሚገኘው ሉንድ ካቴድራል በጋራ የጸሎት ፕሮግራም እንደ ሚያከናውኑ መግለጻቸውን የጠቀሱ ሲሆን በመቀጠልም በማልሞ ከተማ የብዙኋኑን የማሕበረሰብ ክፍል ምስክርነትን እንደ ሚታደሙ መገለጹም ታውቁኋል። በማግስቱም ማለትም እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በህዳር 1/2016 “የሁሉም ቅዱሳን ቀን” በሚከበርበት ቀን ቅዱስነታቸው በማልሞ ከተማ ለሚገኙ በጣም ጥቂት የካቶሊክ ምዕመናን መስዋዕተ ቅድሴን እንደ ሚያሳርጉ ከመግለጫው ለመረዳት ተችልኋል።

በቫቲካን የሕትመት ክፍል ተገኝተው ስለ ጉብኚቱ አስፈላጊነት ለጋዜጠኞች ይህንን የመጀመሪያና በታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአንድ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሚደረገው ጉብኚት አስፈላጊነቱን የገለጹት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መኋከል ለሐይማኖት ሕብረት የሚደረገው ውይይት የሚመሩት በዓለም የሉቴራን ፌደረሽን ዋና ጸሐፊ ክቡር ማርቲን ጃንግ እና በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደረውና የክርስቲያን ህብረት እንዲጠናከር የሚሠራው ምክር ቤት ዋና ጸኋፊ የሆኑት ካርዲናል ኩርት ኮክ ጉብኚቱን አስመልክተው ለጋዜጠኞች መግለጫ መስጠታቸውም ታውቁዋል።

የሉቴራ ቤተ ክርስቲያን ከካቶሊክ የተገነጠለችበትን 500ኛ ዓመትን ለመዘከር በማሰብ የተዘጋጀው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ጉብኝት አስፈላጊነት ላይ ማብራሪያ የሰጡት የሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮች ይህ ጉብኝት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መኋከል እየጎለበተ መጥቶ ከእዚያም ቡኋላ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ1999 ጽድቅን የተመለከተ የማይለውጥ የነገረ መለኮት አስተምህሮ ላይ እና እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ2013 ደግሞ በሁለቱ አባያተ ክርስቲያን መኋከል ተሃድሶን በተመለከተ የነበረውን ሁኔታ የሚያስረዳ ታሪክ በጋራ ስምምነት “ከጥላቻ ወደ ሕብረት” (From Conflict to Communion) በሚል አርዕስት ያሳተሙት ሰንድ ለግንኙነታቸው ፈር የቀደደ እንደ ነበረም ተገልጽዋል።

ከተወሰኑ ጊዜያት በፊት ክቡር ጃንግ ይህ በካቶሊኮች እና በሉቴራን አባያተ ክርስቲያና መኋከል የሚታየውን ታሪካዊው ክፍፍል ሊፈታ የማይቻል ጉዳይ ይመስል እነደ ነበር አውስተው ዛሬ ግን ይህ እውነታ ተቀይሮ በእዚህ መከራና መከፋፈል በገጠመው ዓለማችን ስምምነትን መፍጠራችን ትልቅ የሆነ የክርስቲያን ምስክርነትን የሚያሳይ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

“በእዚህ ታሪካዊ የመታሰቢያ ቀን መከናወን የሚጠበቅባቸው ነገሮች ምን መሆን እንዳለባቸው በጥልቀት እየሠራንበት እንገኛለን. . .ለእዚህም ይህ 500ኛ አመት ከመዘከሩ በፊት ዝክሩን ወይም መታሰቢያነቱን በተመለከተ ጠንካራ የሐይማኖት ሕብረት መፍጠራችንን የሚያሳይ ምልክት እንደ ሆነ ይገልጻል በሚል ተስፋ ከአመት በፊት ዝግጅት ማድረግ ጀምረናል ያለው መግለጫው “ይህም ተስፋ የምለመልምበት ምክንያት በመኋከላችን እየተካሄደ በሚገኘው ውይይትና እያደገ በመጣው የመተማመን መንፈስ ምክንያት ነው ያለው መግለጫው በእዚህም ረገድ በመካከላችን አንድነት እንዳይፈጠር እንቅፋት ሆነው የነበሩትን አንድ አንድ መሠረታዊ የሆኑ የየአብያተ ክርስቲያኖቻችንን አስተምህሮዎችን እስከ ማስወገድ፣ እንዲበለጽጉና እንዲበስሉ እስከ ማድረግ ተደርሶ እንደ ነበረና ይህም ወደ ፊት በመጓዝ ‘ከጥላቻ ወደ ህብረት’ እንድንደርስ ረድቶናል ይላላ መግለጫው። ይህን በተመለከተ የደረስንበትን ደረጃ በይፋ ለመግልጽ በማሰብ ነው እንግዲህ በጋራ እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ የምንጸልየው፣ ይህንንም ነው እንግዲህ ለማሕበረሰቦቻችን በትጋት እንዲኖሩበት የምናበረታታው” በማለት የጋራ መግልጨው የጉብኚቱን አስፈላጊነት ገልጹአል።

ካቶሊኮች ይህንን የተሃድሶ የመታሰቢያ በዓል በምን ዓይነት መንፈስ ማክበር ይኖርባቸዋል ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ ካርዲናል ኮክ በመለሱበት ወቅት ሦስት መሠረታዊ የሆኑ ፍሬ ሐሳቦችንም ጠቅሰዋል። ይህ የመታሰቢያ በዓል በጋራ መከበሩ ወይም መዘከሩ በቀዳሚነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልጸው በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ለ50 ዓመታት ያህል በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መኋከል የጋራ ምስክርነት የመጭው ጊዜ ተስፋ ነው በሚል ሕሳቤ ስያደርጉ ለነበረው ውይይት መሠረት የጣለ መሆኑ የሚታሰብበት እለት ሲሆን በመጨረሻም በተሃድሶ ምክንያት በተፈጠረው ቅራኔ ምክንያት በ16ኛው እና በ17ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓ አሰቃቂ ወደ ሆነ ግጭት ውስጥ በገባችበት ወቅት በተፈጠረው “የደም ባሕር” በመጸጸት እንደ ሚዘከር ገልጸዋል።

ሉተር ላይ ተደርጎ የነበረው ውግዘት ይነሳል ወይ? ተብሎ ለተነሳላቸው ጥያቄ ካርዲናል ኮክ ሲመልሱ ይህንን ጉዳይ በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያ የምታከናውነው ነገር አይደለም ካሉ ቡኋላ ነገር ግን አሁን ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሉተርን በተመለከተ ብዙ መልካም ገጽታዎቹን እያነሱ እንደ ሚገኙና ሉተር ለጋራ የክርስትና እምነታችን ያባረከተውን መልካም ነገር እየመረመሩ እንደ ሚገኙ ገልጸኋል።

“የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውግዘቱን ልታነሳ ወይም ልትሰርዝ አትችልም” ያሉት ካርዲናል ኮክ ምክንያቱም ተወግዞ የነበረው ሰው ከእዚህ ምድር በሞት በተለየበት ወቅት ውግዘቱም በእዚያው ስላበቃ ነው ብለዋል። ነገር ግን በሌላ በኩል ስለ ሉተር ማለት የምንችለው ነገር አሉ ካርዲናል ኮክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ እርሱ የሚናገሩት ብዙ መልካም ነገሮች እንዳሉ ማሰብ መልካም ነው ብለውና ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ጀርመንን በጎበኙበት ወቅት የተናገሩትን ቃል በመጥቀስ ከሉተር ብዙ ነገሮችን መማር እንደ ሚቻልም ጠቁመዋል። በመቀጠልም አሉ ካርዲናል ኮክ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ለነበሩ በነዲክቶስ 16ኛ ለሉተር ዋንኛው አሳሳቢ ጉዳይ የነበረው እግዚኣብሔርን በተመለከተ የነበረው ጥያቄ መሆኑን ገልጸው እንደ ነበረ ጠቅሰው በእርግጠኛነትም ለሉተር አንገብጋቢ የነበሩት እግዚኣብሔርን በተመለከተ የነበረው ጥያቄና የኢየሱስ ማዕከላዊነትን የተመለከተ ምልከታዎች በሕይወቱ ውስጥ ቁልፍ የሆኑ አሳሳቢ ጉዳዮችና የሉተር ተግባራት ዋነኛው ትኩረት እንደ ነበሩ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃን ጳጳስ በነዲክቶስ 16ኛ በሚገባ እንደ ምያውቁም ካርዲናል ኮክ ገልጸው ይህም ጉዳይ  ለእኔ ባጣም አስፈሊ ጉዳይ ነው፣ ስለ ሉተር ማለት የምንችለው ይህንኑ ነው፣ በነገረ መለኮት ትምህርትም ስለ ሉተር የተማርነውም ይህንኑ ነው ብለዋል።

የሁለቱ አብያተ ክርስቲያን ተወካዮች በመገለጫቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት ምንም እንኳን በቤተ ክርስቲያንና በቅዱስ ቍርባን አገልግሎት ዙሪያ ሥነ-መለኮታዊ ልዩነት በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ቢኖርም በሲዊድን ሊካሄደ በታቀደው ጉብኝት ወቅት እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ አዳዲስ ግብዐቶች እንደ ሚገኙና ምን አልባትም በመንበረ ታቦት ዙሪያ በጋራ የሚቀርቡበት አጋጣሚ ሊፈጠር እንደ ሚችል ጨምረው ገልጸዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.