2016-10-26 15:00:00

ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር መንግሥት የሚያድገው በማዋቅሮች ላይ ተመሥርቶ ሳይሆን አባላቱ በሚያሳዩት መልካምነት ነው አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በታላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 15/2009 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት የእግዚኣብሔር መንግሥት የሚያድገው አባላቱ በሚያሳዩት መልካምነት ላይ ተመሥርቶ መሆኑን ገልጸው ስለዚህም ክርስቲያኖች በመዋቅሮችና በድርጅቶች የውስጠ ደንብ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ እንደ ሌለባቸው ማሳሰባቸው ተገለጸ።

 

በእለቱ በተነበበው የወንጌል ቃል (ሉቃስ 13. 18-21) ላይ ተመርኩዘውና የእግዚኣብሔር መንግሥት በምን እንደ ሚመሰል በሚጠቅሰው ምንባብ ላይ መሠረት አድርገው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር መንግሥት በአንድ ውስን በሆነ መዋቅር ላይ የተመሰረተ ሳይሆን ነገር ግን በየጊዜው እየተቀየረና ለማደግ የሚረዳው ምን መሆን እንዳለበት የገለጸ የሚሄድ ነው ካሉ ቡኋላ የእግዚኣብሔር ቃል ዝንብሎ ለጥናት ይሆን ዘንድ የተሰጠን ህግ ሳይሆን ነገር ግን ከሕይወታችን ጋር ተቆራኝቶ ወደ ፊት ሊጓዝ የሚገባ ነገር መሆኑን በአጽኖት ገልጸዋል።

“የእግዚአብሔር መንግሥት ምንድነው?” በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከታቸውን የቀተሉት ቅዱስነታቸው ይሁንና የእግዚኣብሔር መንግሥት በጣም ጥሩ የተባለ መዋቅር ያለው፣ ጥሩ አደረጃጀት ያለው፣ ምርጥ የድርጅት የውስጥ መዋቅር ያለው፣ ሁሉም ነገር ያለው ቢሆን እና ሰዎች ወደ እዚህ መዋቅር የማይገቡበት ከሆነ የእግዚኣብሔር መንግሥት ልንለው አንችልም” በማለት በጽኖት የገለጹት ቅዱስነታቸው በሕግ ውስጥ የምናገኛቸው የማይለወጡ፣ ግትር የሆኑና የመሳሰሉት ነገሮች  ይህን የመሰለ አደረጃጀት በእግዚኣብሔር መንግሥት ውስጥ ሊከሰት አይችልም ካሉ ቡኋላ ሕግ ወደ ፊት መጓዝ የሚችል መሆን ይኖርበታል፣ የእግዚኣብሔር መንግሥት ወደ ፊት የሚጓዝ ነው እንጂ ዝም ብሎ ተገትሮ የቆመ ነገር አይደልም በማለት ገልጸው የእግዚኣብሔር መንግሥት በእየጊዜው ራሱን እያደሰ የሚሄድ መሆኑንም አብራርተዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንዳሳሰቡት ወደ ፊት መጓዝን ትተውና ግትር በሆነ ህግ ላይ ብቻ የተመሰረተ ባሕሪ ያለን ሰዎች መሆን እንደ ማይገባ አሳስበዋል። “ጌታ የእግዚኣብሔር መንግሥት እያደገና ለሁሉም መልካም ምግብና መልካም መኖሪያ ይሆን ዘንድ ለማስቻል ከእኛ የሚፈልገው ምን ዓይነት ባህሪ ነው? በማለት ጥያቄን በማንሳት ስብከተቻውን ቀጥለው ለእዚህም ትክክለኛው መልስ የገራምነትን ባህሪ መላበስ መሆኑን ገልጸው ምክንያቱም የእግዚኣብሔር መንግሥት ልያድግ የሚችለው በገራምነት እና በመንፈስ ቅዱስ እገዛ መሆኑንም አበክረው ገልጸዋል። ዱቄት ዱቄትነቱን ትቶ ወደ ዳቦነት የሚቀየረው በእርሾ አማክይነት መሆኑን በማውሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ለእርሾ ጥንካሬ ዱቄቱ በገራምነት ራሱን ስላስገዛና ከእርሾ ጋር በገራምነት መዋሀድ ስለፈለገ መሆኑን ገልጸዋል። ራሳችንን ከሌላ ነገር ጋር ማዋዐድ ስቃይን የሚፈጥር ጉዳይ ነው አይደል? በማለት ጥያቄን አንስተው አዎን! የእግዚኣብሔርም መንግሥት እንዲሁ ነው፣ የሚያድገውም በዚሁ መንገድ ነው ከዚያም እንጀረው ለሁሉም የተዘጋጀ ይሆናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ልክ ዱቄት ለእርሾ በገራምነት እንደ ሚታዘዝና አንድ ዘር ሞቶና ማንነቱን ካጣ ቡኋላ ወደ ትልቅ ነገር እንደ ሚቀየር ሁሉ የእግዚኣብሔር መንግሥት በተመሳሳይ መልኩ “ወደ ተስፋ” እና ወደ “ሙልኋት” የሚጓዝ መንገድ ነው ብለዋል።

የእግዚኣብሔር መንግሥት በእየለቱ እራሱን ይፈጥራል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔር መንግሥት የሚያድገው ልክ አንዲት የእርሾ ቅንጣት ዘር ልጡን እንደ ሚለውጥና ኩፍ እንደ ሚያደርግ ሁሉ እኛም ለመንፈስ ቅዱስ ራሳችንን ማስገዛት ስንችል ነው ካሉ ቡኋላ ክርስቲያኖች ወደ ፊት መጓዝ የማይችሉ ከሆነ ግትሮች ይሆናሉ ይህም ግትርነት ወላጅ አልባ ልጆች ያደርጋቸአል ብለዋል።

“ግትር የሆነ ሰው አለቃ እንጂ አባት የለውም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የእግዚኣብሔር መንግሥት ልክ አንድ እናት እራሷን ለልጆቹዋ አስላፋ በመስጠት የጌታን ምሳሌ በመከተል ለልጆቹዋ  ምግብና መጠሊያ እንደ ምታቀርብ እናት የእግዚኣብሔር መንግሥትም እንዲሁ የሚያሳድግና ለም ነው ብለዋል። ዛሬ መንፈስ ቅድሱ የገራምነትን ባህሪ እኒያጎናጽፈን የምንለምንበት ቀን ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ብዙን ጊዜ ለስሜቶቻችንና ለውሳኔዎቻችን ገራምነትን አናሳይም ካሉ ቡኋላ ‘ነገር ግን የፈለግነውን እንሠራላን. . .’ የእግዚኣብሔር መንግሥት በዚህ ዓይነት ሁኔታ አያድግም ለመንፈስ ቅዱስ በምናሳየው ገራምንት ብቻ ነው ልያሳድገንና ልክ እንደ እርሾ ልጡን እንደ ሚያቦካው እና እንደ ሚቀይረው እኛም ልንለውት የምንችለው ለመንፈስ ቅዱስ በግራምነት እራሳችንን ስናስገዛ ብቻ ነው ካሉ ቡኋላ እግዚኣብሔር የገራማነት ጸጋ ይሰጠን ዘንድ ተመኝተው ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.