2016-10-22 14:35:00

ቅዱስነታቸው "እምነት የህጎችና የደንቦችን ስብስብ ነው ወደ ሚለው ሐሳብ ሊወርድ አይገባውም" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥቅምት 11/2009 ጥሪን የተመለከተ ዓለማቀፍ ጉባሄ በቫቲካን በተካሄደበት ወቅት እንደ ገለጹት እምነት የህጎችና የደንቦችን ስብስብ ነው ወደ ሚለው ሐሳብ ሊወርድ ሳይሆን የሚገባው ነገር ግን በምትኩ ሰዎችን የሚያነቃቃና በወንጌል ምልዕክት የሚገኘውን ደስታ እንዲጎናጸፉ የሚረዳ የሕይወት መንገድ  ነው ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው ይህንን መልዕክት አስተላልፈውት የነበረው በቁጥር በርከት ያሉ ካርዲናሎች፣ አቡናት፣ ካህናትና ከመንፈሳዊ ማሕበራት ለተውጣጡ ሰዎች በሮም በላቲን ቋንቋ “Miserando atque eligendo’ በአማሪኛው ‘በምህረት አየውና መረጠው” በሚለው ኢየሱስ ማቴዎስን በጠራበት ወቅት የተጠቀመበትን ቃል መርዕ አርዕስት አድርጎ በሮም በተካሄደው ጉባሄ ላይ መሆኑም ታውቁዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህን ተመሳሳይ መርዕ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ሳይመአጡ በፊት ይህንን ተመሳሳይ ሐረግ ለወንድሞቻቸው ጳጳሳ የአገልግሎታቸው መርዕ እንዲሆን መርጠውት እንደ ነበረ አስታውሰው ይህ መርዕ ሐሳብ ጌታ በወጣትነት እድሜያቸው በጠራቸው ወቅት እንዲፈጽሙት የሰጣቸው መርሖ መሆኑ ይሰማቸው እንደ ነበረ አስታውቀዋል። የጥሪ ጥያቄዎች በፍጹም ወደ ሐዋርያዊ እቅዶች ወይም ደግሞ ወደ የቁጥር ስሌቶች ህሳቤ ዝቅ ማለት የለባቸውም በማለት ለተሳታፊዎች በጽኖት በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በአንጻሩ ኢየሱስ የኖረበትን መንግድ ለመከተል መማር፣ መናገርና የእግዚኣብሔርን ምሕረት በአከባቢው ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ማሳየቱን ማወቅ ነው ብለዋል።

ይህ ኢየሱስ ያሳየን የሕይወት ምሳሌ በሦስት ግሶች ልናጠቅልላቸው እንችላለን ያሉት ቅዱስነታቸው እነዚህም መውጣት፣ ማየትና መጥራት የሚሉ መሆናቸውን ገልጸዋል። በመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያን ‘አልችል ይሆናል’ በሚል ፍርሃት ውስጥ ሆና ምንም ማምለጫ እንደ ሌለው ከምትሆን ይልቅ የግድ መውጣት ይጠበቅባታል፣ በእንቅስቃሴ ላይ ሊትሆንም ይገባታል፣ ምዕዳሩዋንም ማስፋትም ያስፈልጋታል በማለት በአጽኖት በመግለጽ ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በድፍረትና አግባብ ባለው መልኩ ግቦቻቸውን ዳግም እስካልከለሱ፣ የመዋቅር ለውጥ እስካላደረጉ፣ የአሠራር ዝይቤአቸውን እስካልቀየሩና የስብከተ ወንጌል ዜዴዎቻቸውን እስካልከለሱ ድረስ  ፍሬን የሚያፈራ ጥሪን መስብሰብ አይችሉም ብለዋል።

በሁለተኛ ደረጃ አሉ ቅዱስነታቸው አንድ እረኛ ኢየሱስ በጊዜው የነበሩ ሕዝቡን የተመለከተበትን መንገድ መማር ይኖርበታል ካሉ ቡኋላ እነዚህም ጭፍን የሆነ ታዋቂ ጥላቻን በማስወገድና ሌሎችም የእግዚኣብሔር ፍቅር በሕይወታችው ይሰማቸው ዘንድ ቦታ መስጠት ያስፈልጋል ብለዋል። ቤተ ክርስቲያንና ዓለም የሚያስፈልጉዋቸው በሳልና በጣም ሚዛናዊ የሆኑ ካህናት ናቸው በማለት ንግግራቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው መንፈሳዊ የሆኑ፣ በርኅራኄ የሚወስኑና የሕዝቡን ሕሊና ሙሉ በሙሉ የመቆጣጠር ፍላጎት ሳያሳዩ ሕዝቡን የሚመሩ ካህናት እንደ ሚያስፈልጉ በአጽኖት ገልጸዋል።

በመጨረሻም አሉ ቅዱስነታቸው እረኞች ኢየሱስ ሕዝቡን የጠራበትን መንገድ መማር ይኖርባቸዋል እንጂ አስተሳሰባችውን ሙሉ በሙሉ እንዲለውጡ በማሰብ ረጃጅም የሆኑ አስተምህሮዎችና የተዘጋጁ መልሶችን በመጠቀም  ማስገደድ አይገባም ካሉ ቡኋላ ነገር ግን መሆን የሚገባው ሌሎች ተገቢ የሆኑ ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ በማድረግና ኢየሱስ ወደ ሚመራቸው መንግድ ማሳየት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.