2016-10-20 17:01:00

የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 20 ቀን እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. በመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ውስጥ የሚታቀፈው በኤውሮጳ የሚገኙት የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ የካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በፖርቱጋል ፋጢማ ከተማ ለጉባኤ መጠራቱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታውቋል።

ይኽ በፖልርቱጋል በሚገኘው በፋጢማ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ የሚካሄደው ይፋዊ ዓመታዊ ምሉእ ጉባኤ ዋናው የማወያያ ርእሰ ያደረገው ጉባኤ ከምስራቅ ሥርዓት ተከታይ አገሮች ተሰደው በምዕራብ አገሮች የሚኖሩት ካቶሊካውያን ምእመናን ሐዋርያዊ እንክብካቤ ላይ እይታው በማኖር በፋጢማ እንዲካሄድ የጋበዙትም የሊስቦና ፓትሪያርክ የፖርቱጋል ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ማኑኤል ክለመንት መሆናቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ በማያያዝ በፋጢማ የማርያም መገለጽ እ.ኤ.አ. 2017 ዓ.ም. ዝክረ መቶኛው ዓመት የሚከናወን በመሆኑም ለጉባኤ መንፈሳዊ ድምቀት የሚያሰጠው መሆኑ ጠቅሰው እነዚህ በኤውሮጳ ከሚገኙት ከ 15 የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ ጳጳሳት በጋራ የምስራቅ ስርዓት ተከታይ ካቶሊክ ምእመን ከሚገኙባቸ ከፈረንሳይ ከጀርመን ከፖልርቱጋል ከእንግሊዝ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የተወጣጡ ተወካዮች በማሳተፍ የሚካሄድ መሆኑ አስታውቋል።

በተለያዩ የኤውሮጳ አገሮች የሚገኙት የምስራቅ ሥርዓት ከሚከተሉት አገሮች ተሰደው በምዕራብ አግሮች መኖር የጀመሩት ካቶሊካውያን ምእመናን መንፈሳዊ እንክብካቤና እንዲሁም የምስራቅ ኤውሮፓ ክልል አገሮች ከአምባገነን መንግሥታት ነጻ መጣት ጋር ተያይዞ የክልሉ ዜጎች ወደ ተቀሩት ምዕራብ አገሮች መሰደድና እነዚህ ስደተኞችም ከምስራቅ ተከታይ ካቶሊክ አቢያተ ክርስቲያን ከመጡ ከ 20 ዓመት በኋላ የሆናቸው ወደ ሁለተኛው ትውልድ የደረሱ ሆነው ምንም’ኳ የላቲን ሥርዓት የሚከተሉ አቢያተ ክርስቲያን ዘንድ የሚታቀፉ ቢሆንም ነገር ግን የምስራቅ ሥርዓት ከሚከተሉት አገሮች ተሰደው በሚኖሩበት የምዕራብ አገሮች በምሉ የምስራቅ ሥርዓት ሕገ ቀኖና ሥር መንፈሳዊ እንክብካቤ እንዲያገኝ ተደርጓል። እነዚህ በምዕራብ አገሮች የጸኑት የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ አቢያተ ክርስቲያን በተስተናገዱበት አገር በሚገኘው የብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሥር ጭምር በመታቀፍ ሙሉ ዜግነት አግኝተው ተጣማሪ የህብረተሰቡ ክፍል ለመሆን በቅቷል።

በዚህ በፋጢማ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ በሚካሄደው ምሉእ ዓመታዊ ጉባኤ በሰብሳቢነት የሚገኙት የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን የሚንከባከበው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ሊዮናርዶ ሳንድሪ ከተጋባእያኑ ጋር በመሆን ጉባኤው የሚያነሳቸው ዘርፈ ብዙ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ርእስ ዙሪያ ሃሳብ ለሃሳብ በመለዋወጥ የእነዚህ አቢያተ ክርስቲያን የኤኮኖሚ ጉዳይ በተመለከተም ፕሮፈሰሮ ዥዋው ሉይስ ሰሳር ዳስ ነቨስ የሚያቀርቡት ንግግር ተደምጦ በተያያዘ መልኩም በምዕራብ አገሮች የተስተናገዱት የምስራቅ አቢያተ ክርስቲያን ተከታይ ምእመናን በሚያቀርቡት ምስክርነት በተስተናገዱበት አገር በምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና ከተሰደዱበት አገር ከምትገኘው የምስራቅ ሥርዓት ከምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለው ግኑኝነት በጥልቀት ይስተነተናል።

በዚህ የጉባኤው የእያንዳንዱ ቀነ ውሎው በመስዋዕተ ቅዳሴ የሚጀመርና የመላ ኤውሮጳ አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ምክርቤቶች ኅብረት ያዘጋቸው የኤውሮጳ የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ አቢያተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ የኢጣሊያ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር በኢጣሊያ የጄኖቫ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ባኛስኮ ባላቸው የመላ ኤውሮጳ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤቶች ኅብረት ሊቀ መንበርነት ሐዋርያዊ ሥልጣን በመጀመሪያው ቀነ ጉባኤ ተሳታፊ እንደሚሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገልጠው፡ ጉባኤው እሁድ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. የመላ ኡክራይንና ክየቭ የግሪክ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አቢይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕነታቸው ስቪያቶስላቭ ሸቭቹክ በቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በሚመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴና በቤተ መቅደሱ ባለው የምኅህረት ቅዱስ በር የማለፍ መንፈሳዊ ዑደት ሥነ ሥርዓት እንደሚጠናቀቅ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.