2016-10-20 10:05:00

ቅዱስነታቸው "መልካም እረኛ ኢየሱስን የሚከተል ሰው ነው እንጂ ስልጣን፣ ገንዘብ ወይም በጎጠኛነት የሚያምን ሰው" አይደልም አሉ


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በጥቅምት 8/2009 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት መልካም እረኛ ሊባል የሚችል ሰው ኢየሱስን የሚከተል ሰው እንጂ ስልጣን፣ ገንዘብ ወይም በጎጠኛነት የሚያምን ሰው አይደልም ብለዋል።

በእለቱ በተነበበው ሁለተኛው የሐዋሪያው የጳውሎስ መልዕክት ወደ ጢሞቲዎስ 4.10-17 በተወሰደው የመጀመሪያ ምንባብ ላይ ተመርኩዘውና ጳውሎስና ሌሎችን ሐዋሪያት በሐዋሪያዊ ተግባሮቻቸው ወቅት የገጠማቸውን ተግዳሮቶችን ዋቢ በማድረግ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ሐዋሪያው ጳውሎስ በመጨረሻው የሕይወቱ ማብቂያ ላይ ያለማንም እጋዢ በመቅረቱ እና ሁሉንም ነገር በማጣቱ ልክ እንደ አንድ ለማኝ ሰው ለመለምን ቋምጦት ነበር ብለዋል።

“በብቸኝነት፣ በችግር፣ በሁሉም ችላ በመባሉ በጣም ተናዶ ነበር፣ ይህ ሰው የጌታን ቃል የሰማና ጥሪውንም የተቀበለ ጀግናው ጳውሎስ ነበር” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሐዋሪያው ጳውሎስ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመጓዝ ብዙ የተሰቃየና ወንጌልን በመስበክ ሂደት ውስጥ መከራን ያየ፣ ጌታ አሕዛብ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እንዲገቡ መፍቀዱን ሌሎች ሐዋሪያት እንዲማሩ ያደረገ፣ ጸሎቱ ሰባቱ ሰማያት ድረስ የዘለቀና ማንም ሰው ሰምቶ የማያውቀውን የክርስቶስን ድምጽ የሰማ ታላቁ ጳውሎስ አሁን ደግሞ በሮም ብትንሽ የእስር ቤት ውስጥ ተቀምጦ በፈራጆቹና በርሱ ሐዋሪያት መኋከል የተከፈተውን ክርክር እና ትግል በማዳመጥ ላይ ይገኛል” ካሉ ቡኋላ ይህም የታላቁ የጳውሎስ ሕይወትን ፍጻሜ ምን እንደ ሆነ ያሳያል ቅያሜ ወይም ደግሞ ምሬት ሳይሆን ይሰማው የነበረው ነገር ግን ውስጣዊ ባዶነት ነበር የተሰማው ብለዋል።

ሐዋርያው ጴጥሮስ እና መጥምቁ ዩሐንስም ተመሳሳይ ገጠመኞችን ማሳለፋቸውን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠለት ቅዱስነታቸው እነርሱም በመጨረሻ የሕይወት ዘመናቸው ተመሳሳይ ስቃይ ግጥሞዋቸው እንደ ነበርና “ተንኮለኛ በሆንችው ወጣት ዳንሰኛና አመንዝራ የነበረችሁ ሴት በፈጸመችሁ የበቀል ሴራ” መጥመቁ ዩሐንስ አንገቱን ተቀልቶ እንደ ነበረ አስታውሰው በቅርቡም እንኳን ዓለማቀፍ ሐዋሪያዊ እንቅስቃሴዎች እንዲስፋፉ ያደረገው ማክሲሚላን ኮልቤ በእስር ላይ እያለ መሞቱንም በማጣቀሻነት ጨምረው ገልጸዋል።

አንድ ሐዋሪያ ታማኝ በሚሆንበት ወቅት እርሱ ወይም እርሷ ተመሳሳይ እጣፋንታቸው በኢየሱስም ላይ የደረሰው መከራ እንደ ሚጠብቃቸው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል በማለት በአጽኖት በመናገር ስብከታቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው ይህ ሁሉ በሚሆንበት ወቅት ኢየሱስ ብቻችውን አይተዋቸውም በቅርበት ከእነርሱ ጋር በመሆን ጥንካሬውን ይሰጣቸዋል ብለዋል። ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ይህ የወንጌል ሕግ ነው የስንዴ ቅንጣት በመሬት ላይ ወዳቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራላች፣ ከሞተች ግን ብዙ ፍሬን ታፈራለች” እንደሚል ከገልጹ ቡኋላ በመጀመሪያዎች ምዕተ ዓመታት የነበሩ የነገረ መለኮት መምህራን የሰማዕታት ደም ለክርስቲያኖች ዘር ነው ብለው መጻፋቸውንም አስታውሰዋል።

“በዚህ መልኩ ኢየሱስን በመመስከር ሂደት ውስጥ እንደ ሰማዕት መሞት፣ የስንዴ ቅንጣት በመሬት ወድቆ ከሞተ ቡኋላ ሌላው እንዲበቅል የሚያደርግና ክርስቲያኖች ምድርን እንዲሞሉአት ይሚረዳ አዲስ ዘርን የሚፈጥር ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው አንድ እረኛ ይህንን በመሰለ መልኩ በሚኖርበት ወቅት መራር ሕይወት ውስጥ እንደ ገባ መቁጠር የለበትም፣ ምን አላባት ብቸኝነት ይሰማው ይሆናል ነገር ግን በእርግጠኛነት ክርስቶስ ከእርሱ ጎን መቆሙን ልያምን ይገባዋል ብለዋል።

አንድ እረኛ በሕይወት ዘመኑ ከነገሮች ለምሳሌም ከሥልጣን፣ ከገንዘብና ከጎጠኝነት እንዲሁም ከመሳሰሉ ነገሮች ጋር ተቆራኝቶ በአንጻሩም ምዕመናን ችላ በሚልበት ወቅት. . . .  እርሱም በሚሞትበት ወቅት ብቻውን አይሆንም ምን አልባት እርሱ ከሞተ ቡኋላ ያለውን ንብረቱን ለመወረስ የሚጠባበቁ ሰዎች በአጠገቡ ይኖራሉ ካሉ ቡኋላ ከሰማዕታት ጎን ግን ሁል ጊዜም የሚኖርው ክርስቶስ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት በአረጋዊያን መጦሪያ ውስጥ የሚገኙ ብዙ ካህናት ምንም እንኳን በሕመም እየተሰቃዩ ቢሆንም እንኳን ይህንን ሕመማቸውን ተቋቁመው በጸሎት ከጌታ ጋር ቅርበትን ፍጥረው እንድሚገኙ ገልጸው “አንድ አንዴ የአረጋዊያን መጦሪያ ቤቶችን ለመጎብኘት በሚሄድበት ወቅት በሕይወታቸው ዘመን መልካም እረኛ በመሆን ለምዕመናኖቻቸው ከፍተኛ እገዛ ያደረጉትን ካህናትን መገናኘታቸውን ገልጸው፣ በሽተኞች ናቸው፣ አንድአንዱም አካላቸው የሰለለ ነው፣ አንድአንዶቹም በተሽከርካሪ ወንበር ላይ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ናቸው በዚሁ ሁሉ ስቃያቸው ውስጥ አስደሳች የሆነ ፈገግታ በፊታቸው ላይ ይታያል ይህም የሚሆንበት ምክንያት ጌታ በቅርበት ከእነርሱ ጋር መሆኑ ስለሚሰማቸው ነው ብለዋል።

በደስታ አይኖቻቸውን እያቁለጨልጩ ‘እንዴት ናት ቤተ ክርስቲያናችን? ሀገረ ስብከቱስ እንዴት ነው? የጥሪ ጉዳይስ እንዴት እየሄደ ነው?” በማለት እንደ ሚጠይቁ በመግልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ጥያቄ ማንሳታቸው ተግቢ ነው ምክንያቱም እንደ አባት ሕይወታቸውን ለሌሎች የሰውበት ጉዳይ በመሆኑ ጥያቄያቸውን ተገቢ ያደርገዋል ካሉ ቡኋላ ቀደም ሲል በስብከታቸው መጀመሪያ ላይ ጠቅሰውት ወደ ነበረው የሐዋሪያው ጳውሎስ ሕይወት በድጋሚ ተመልሰው ብቻውን በመሆን ይሰቃይ ነበር፣ የንዴት ሰላባም ሆነ፣ ከጌታ በቀር በሁሉም እንደ ተረሳ ያውቅ ነበር ‘ጌታ ኢየሱስ ብቻ ነበር ከአጠገቡ የነበረው! ማንኛውም መልካም እረኛ በእዚህ ጉዳይ እርግጠኛ መሆን ይኖርበታል በኢየሱ መንገድ ከተጓዘ ጌታም በመከራው ወቅት ሁሉ ከርሱ ጋር እሰክ መጨረሻው ይጓዛል ብለዋል።

በሕይወታቸው መጨረሻ ላይ ለሚገኙና ጌታ ሕይወታቸውን ወደ እርሱ እንዲወስድ በመጠባበቅ ላይ ላሉት እረኞች መጸለይ ይገባል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጌታ ብርታትን፣ መጽናናቱንና እርግጠኛነትን  ይሰጣቸው ዘንድ ምንም እንኳን በህመም የሚሰቃዩና ብቸኝነት የሚሰማቸው ቢሆኑም ጌታ ከእነርሱ ጋር መሆኑንና ለእነርሱ ቅርብ እንደሆነ ይረዱ ዘንድ መጸልይ ተገቢ እንደ ሆነ አሳስበው ጌታ ጥንካሬን ይሰጣቸው ዘንድ ምኞታቸው መሆኑን ከገለጹ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.