2016-10-13 16:26:00

የኬንያ ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት የሰላም ጥሪ


እ.ኤ.አ. ነሐሴ 2017 በኬንያ ሊካሄድ ስለ ተወሰነው ሕዝባዊ ምርጫ በማስደገፍና እንዲህም የምረጡኝ ምርጫ ውደራ ከወዲሁ የአምጽና የግጭት ምክንያት እንዳይሆን የሚል በተለያየ ምልኩ እየተደመጠ ያለው ስጋት ምክንያት በማድረግ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ካቶሊክ ምእመናን ስለ ሰላምና መረጋጋት እንዲጸልይ በየንየሪ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፒተር ካኢሮ በኵል ምእመና ስለ ሰላምና መረጋጋት ጸሎት እንዲያቀርብ ጥሪ አስስተላልፏል።

ነጻና የሕግ ሉኣላዊነት የሚረጋገ

ጥበት እንጂ የጎሳ ልዩነት የሚያስከተል እንዳይሆን

እ.ኤ.አ. ጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በሱቡኪያ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ብሔራዊ የጸሎት ቀን ታስቦ በዋለበት ዕለት ምክንያት ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ብፁዕ አቡነ ካይሮ ከዚህ ቀደም በአገሪቷ ታይቶ የነበረው ለብዙ ሞትና መቁሰል ለንብረት ውድመት ምክንያት የሆነው ዘውጋዊነትና ብሔርተኝነት መሰረት ያደረገው ዓመጽና ግጭት ዳግም እይዳይታ ምእመናንን ከወዲሁ በማስጠንቀቅ የዚያ ዓይነቱ ስህተት ሁሉ እንዲቃወመው በማሳሰብ ሊካሄድ ተወስኖ ያለው ሕዝባዊ ምርጫ ነጻና ሥርዓት ጠበቅ እንዲሆን ሁሉም ሊጸልይና ተመራጭ የፖለቲካ ሰልፍ መሪዎች ኬንያን በዘርና በጎሳ ሊከፋፍል ወደ ሚችል ፈተና እንዳይመሩ ሊጠነቀቁ ይገባል ብለው፡ የምረጡኝ ውደራውም ሆነ መራጩ ዘውጋዊነትን ሳይሆን ለመላ አገርና ሕዝብ የሚበጅ መርሃ ግብር ላይ ትኵረት እንዲያደርጉ ማሳሰባቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳ ተችሏል።

በሕዝባዊ ምርጫ ሂደት ሕዝብን ማነጽ

የኒየሪ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ካይሮ ሁሉም የኬንያ ሰበካዎች ቁምስናዎች ሕዝብን በሕዝባዊ ምርጫ ሂደት ዙሪያ እንዲያንጹና ይኽም ቅን አገርና ሕዝብን የሚበጅ አለ ምንም ዘውጋዊ መመዘኛ አድር ባይነትና ግላዊ ጥቅማ ጥቅም ብቁ አካል ለመምረጥ እንዲችሉ ለማድረግ ለመደገፍ ታልሞ የሚፈጸም እንዲሆን እደራ ብለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እስከ 20 ህዳር የሚዘለቅ እንዲኖር ያወጁት እየተኖረ ያለው የምሕረት ዓመት ምክንያት ማኅበረ ክርስቲያን ግብረ ምሕረት እንዲፈጽሙ ያቀረቡት ጥሪ ዋቢ በማድረግ ማሕበረ ክርስቲያን በቤተሰብና ባጠቃላይ በመላ አገር የሰላም መሣሪያ ሆነው እንዲገኙ ማሳሰባቸአው ፒሮ አስታውቋል።  








All the contents on this site are copyrighted ©.