2016-10-04 11:15:00

ቅዱስነታቸው በአዘረበጃን ሐዋሪያዊ ግቡኝት ባደረጉበት ወቅት“እምነት እና አገልግሎት”የክርስትያንነት መገለጫ ሊሆኑ ይገባል አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ከመስከረም 20-21/2009 በጆርጂያ ለሁለት ቀን ያህል ጎብኚት ማድረጋቸውን መግለጻችን የሚታወቅ ሲሆን የጆርጂያን ጉብኚት በተሰካ ሁኔታ ካጠናቀቁ ቡኋል የካውካሰስ ሀገራት አባል የሆነችሁን አዘረበጃንን ለመጎብኘት በትላንትናው እለት ማለትም በመስከረም 22/2009 አዘረበጃን መድረሳቸው ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው በመስከረም 22/2009 በጆርጂያ ከሚገኘው ተብሊሲ ዓለማቀፍ የአየር ጣቢያ በሀገሩ የሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 8.00 ላይ ደማቅ አሸኛኘት ተደርጎላቸው የአዘረበጃን ጉብኝታቸውን ለመጀመር ወደ እዚያው ያቀኑ ሲሆን የአንድ ሰዓት ተኩል በረራን ካደረጉ ቡኋላ በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 3.30 በአዘረበጃን በሚገኘው በኩ ኤይዳር አሊዬቪ ዓለማቀፍ የአውሮፕላን ማረፊ ጣቢያ በደረሱበት ወቅት የዘረበጃን የመጀመሪያው ምክትል ጠቅላይ ምኒስትር በሆኑት ያዕቁብ ኤዩቦቪ እና በሌሎች ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ቅዱስነታቸው ከተደርገላቸው አቀባባል ቡኋላ በቀጥታ ያመሩት በሀገሪቷ ወደ ሚገኘው የሳሊዢያን ማህበር ማዕከል ውስጥ በሚገኘው ያለዳም ኋጥያት የተጸነሰች ማሪያም ወደ ተብሎ ወደ ሚጠራው ቤተ ክርስቲያን በማምራት በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 10.30 ላይ መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረግ የጀመሩ ሲሆን በእለቱም ባሰሙት ስብከት በአዘረበጃን የሚገኙ ጥቂት የካቶሊክ ማሕበርሰብ አባላት በታላቅ ስደት ውስጥ በነበረቡት ወቅት ያደረጉትን አስደሳች የሕይወት ምስክርነት “ያስገኘውን ድንቅ” እምርታ በእለቱ  መግለጻቸው ታውቁዋል።

የተከበራችሁ አንባቢዎቻችን ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በአዘረበጃን ያላዳም ኋጥያት የተጸነሰች ማሪያም ቤተ ክርስቲያን ውሽት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ያሰሙት ስብከት ሙሉ ይዘቱ እንደ ሚከተለው ነው።

የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል በክርስቲያን ሕይወት ሊኖሮ ሰለሚገባ ሁለት አስፈላጊ ገጽታዎች ስለሆኑ “እምነት እና አገልግሎት” ያስረዳናል። ከእምነት ጋር በተያያዘ መልኩ  ሁለት የተወሰኑ ጥያቄዎች ለጌታ ቀረበውለታል።

የመጀመሪያው ጥያቄ የቀረበው በነቢዩ ዕንባቆም አማካይነት ሲሆን ይህም እግዚኣብሔር በሰዎች ላይ በሚደረሰው ጥቃት፣ ጥል እና ክርክር አዝኖ ፍትሕ እና ሰላም ዳግም-ይቋቋም ዘንድ ጣልቃ እንዲገባ በማሰብ “እግዛብሔር ሆይ ለርዳታ እየጠራሁ፣ አንተ የማትሰማው እሰክ መቼ ነው!” የሚለው የነቢዩ ልመና ነው። የእግዚአብሔር ምላሽ ግን ቀጥተኛ አልነበረም፣ ድንገተኛ በሆነ መልኩ ችግሩን ለመፍታት አይደለም የፈለገው፣ ኋይልን በመጠቀም እራሱን መግለጽም አልፈለገም። ነገር ግን ተስፋ ሳይቆርጡ በትዕግስ እንዲጠባበቁ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰው በእምነት ይኖር ዘንድ ለማሳየት የእምነትን አስፈላጊነት በማጉላት ይገልጻል። እኛንም እግዚኣብሔር የሚያስተናግደን በተመሳሳይ መልኩ ነው ወዲያውኑ ያለንን ፍላጎቶችን ለማርካት አይደለም፣ ወይም በተደጋጋሚ ዓለም እና ሌሎች ሰዎች ይለወጡ ዘንድም አይደለም።

በምትኩም እርሱ በቀዳሚነት የምፈልገው የእኔ እና የእናንተን ልብ እንዲሁም የእያንዳንዱን ልብ ለማከም ነው። እግዚአብሔር ዓለምን የሚያድነው ልባችንን በመቀየር ነው፣ ይህም ደግሞ ያለእኛ ትብብር የሚከናወን ነገር አይደለም። እግዚአብሔር ወደ ሕይወታችን ለመግባት ያስችለው ዘንድ የልባችንን በር እንድንከፍት ይፈልጋል። ይህ ለእርሱ ልባችንን የመክፈት እና በእርሱ የመተማመናችን  ሂደት በአጭሩ “ዓለም የሚሸነፈው በእምነታችን ነው” (1ዩሐንስ 5.4) እንደ ሚለው ነው። እግዚአብሔር የተከፈተና ታማኝ ልብ በሚያገኝበት ወቅት አዎን በዚያን ጊዜ ታላቅ ነገሮችን መፈጸም ይችላል።

ነገር ግን ሕይወት ያለው እምነት ማግኘት ቀላል ነገር አይደለም፣ በዚህ ምክንያት የተነሳ ሐዋሪያት ለኢየሱስ “እምነታችንን ጨምርልን”(ሉቃስ 17.5) ብለው የጠየቁትን ጥያቄ መመልከት ተገቢ ነው። ይህም እኛም በየቀኑ ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ የሚጠበቅብን ግሩም ጥያቄ ነው። ነገር ግን የተሰጠው መለኮታዊ መልስ “እምነት ቢኖራችሁ ኖሮ. . .” የሚል ጥያቄን በጥያቄ የመለሰ በመሆኑ አስገራም ነበር። እግዚአብሔር እራሱ ነው እምነት እንዲኖረን የሚጠይቀን። ምክንያቱም ሁል ጊዜም ቢሆን የእግዚአብሔር ስጦታ የሆነው እምነት በእኛ ርሳችን ነው መኮትኮት የሚገባው። ከሰማይ የሚመጣ ምዕታታዊ ኋይል አይደለም፣ ወይም ለአንዴ እና ለጨረሻ ጊዜ የሚሰጠን  “የፈጠራ ችሎታ” አይደለም። ወይም ደግሞ የሕይወት ችግሮቻችንን እንድንፈታ የሚሰጠን ልዩ የሆነ ኋይል አይደለም። የእኛን ፍላጎት ብቻ ለማርካት የሚጠቅም እምነት እርሳችንን ብቻ ማዕከል ያደረገ በመሆኑ እራስ ወዳዶች ያደርገናል። እምነት ጥሩ ከመሆን ወይም ጥሩ ስሜት ከመሰማት፣ በልባችን ውስጥ ሰላምን በሚያመጣው መጽናናት ከሚሉት ጋር በፍጹም መምታታት የለበትም። እምነት ከእግዚኣብሔር ጋር በደስታ እንድንኖር፣ ከእርሱ ጋር ሕብረት እዲኖረን የሚያደርገን እና የሚያስተሳስረን የወርቅ ክር ነው፣ እስከ ሕይወታችን ፍጻሜ የሚቆይ ስጦታ ነው፣ ነገር ግን ፍሬ ማፍራት የሚችለው የየራሳችንን ድርሻ ስንወጣ ብቻ ነው።

እናም የእኛ ድርሻ ምንድነው? ኢየሱስ የእኛ ድርሻ አገልግሎትን ያቀፈ መሆን እንዳለበት እንድንገነዘብ ይረዳናል። ኢየሱስ በወንጌል የእምነትን ኋያልነት ከገለጸ ቡኋላ አገልግሎት አስፈላጊ መሆኑንም ያስገነዝበናል። እምነት እና ተግባር በፍጹም መነጣጠል የለባቸውም፣ በተቃራኒው እነዚህ ሁለት ነገሮች በጣም የተሳሰሩ እና የተገናኙ ነገሮች ናቸው። ይህንንም ለማስረዳት ለሁላችን አዲስ ያልሆነውን ስለ ውብ ምንጣፍ የተገለጸውን ምልከታን መጠቀም እፈልጋለሁ። ይህ ውብ ምንጣፍ ጥንታዊ የሆነ እና ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው። እያንዳንዳችን ያለን የክርስቲያን ሕይወት ከጥንት ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ነው። ከእግዚኣብሔር ልብ የመነጨ እና በቤተ ክርስቲያን አማካይነት ለእኛ የተሰጠን ስጦታ ነው። ሁላችሁም እንደ ምታውቁት እያንዳንዱ ውብ ምንጣፍ በጥንቃቄ የተሸመነ እና በጥንቃቄ የሚታጠፍ ነው። የተሸመነ እምነት እና በጥንቃቄ የሚደረግ አገልግሎት። እምነት ከአገልግሎት ጋር በሚጣመርበት ወቅት ልባችን ክፍት እና ጠቃሚ ይሆናል መልካም ነገሮችን የማከናወን አድማስን ያሰፋልናል። ኢየሱስ በወንጌል እንደ ሚለን በዚህም መልኩ የሚገለጽ እምነት  ኋያል እና ድንቅ የሆኑ ነገሮች ማከናወን ይችላል። እምንት ይህንን መንገድ ከተከተለ፣ በሳል እና በጥንካሬ የሚያድግ ይሆናል ነገር ግን ይህ ሊሆን የሚችለው ከተግባር ጋር ሲቀናጅ ነው።

ነገር ግን አገልግሎት ምንድነው? ምን አልባት አገልግሎት ለሥራችን ታማኝ ሆነን እና መልካም ተግባራትን ማከናወን ሊመስለን ይችላል። ለኢየሱስ ግን ከእዚህ ይተሻለ ማድረግ ነው። በዛሬው ወንጌል እና በጣም ጥብቅ እና ጽንፈኛ ውል ውስጥ ተደራሽ እንድንሆን ይጠይቀናል፣ ሕይወታችንን ሙሉ በሙሉ እድንከፍት ይጠይቀናል፣ የእራሳችንን ጥቅሞችን ብቻ መሰረት አድርጎ ከመንቀሳቀስም ልንገታ እንደሚጠበቅብን ያሳስበናል። ይህ ነገር ለምንድነው እኛን የሚያስገርመን? እርሱ እኮ እስከ መጨረሻ ድረስ የእኛ አገልጋይ መሆንን መርጡዋል “ልያገለግለን እና ሕይወቱን ሊሰጠን መጣ” (ማርቆስ 10.45)። መስዋዕተ ቅዳሴን ሁል ጊዜ በምናቀርብበት ወቅት ይህንን እውነታ እንመለከታለን። እኛ እርሱን ለማገልገል እና ለመውደድ በምንነሳበት ወቅት ሁሉ ከእኛ ጋር ለመጉዋዝ፣ እኛ ከምንገምተውና ከሚገባን በላይ ልያገለግለንና ሊወደን  ጌታ በመካከላችን ይገኛል። አንደኛ ልጁን ሰጥቶናል። እርሱን እንድንመስልም “ልያገለግለኝ  የሚፈልግ ሁሉ ይከተለኝ” (ዩሐንስ 12.26) በማለት ይጋብዘናል።

ስለዚህም የተጠራናው አገልጋዮች ብቻ ሆነን እንድንሸለም ሳይሆን የእኛ ፍቅር አገልጋይ በመሆን የመጣውን እርሱን እንድንመስል ነው። እንዲሁም የተጠራነው ዛሬ እና ነገ ብቻ እንድናገለግል ሳይሆን ነገር ግን በአገልግሎት እንድንኖር ጭምር ነው። በዚህም የተነሳ አገልግሎት የሕወታችን አንደኛው ክፍል ሊሆን ይገባል፣ እንዲያውም የክርስቲያን የሕይወት መገለጫ ሊሆንም ጭምር ያስፈልጋል፣ እግዚአብሔርን በአምልኮ እና በጸሎት ማገልገል፣ ግልጽ እና ተደረሽ መሆን፣ ባልንጀሮቻችንን ተጨባጭ የሆኑ ተግባራትን በመፈጸም መውደድ፣ በፍቅር ለጋራ ጥቅም መሥራት ያስፈልጋል።

ክርስቲያኖችንም ቢሆን ከእዚህ የአገልግሎት ጎዳና የሚያስወጡን እና ሕይወታችንን ትርጉም አልባ እንዲሆን የሚያደርጉ የተለያዩ ፈተናዎች አሉ። በእዚህም ረገድ ሁለት ነገሮችን እናገኛለን። የመጀመሪያው ልባችንን በለብታ እንዲያድግ ስናደርገው ነው። ለብ ያለ ልብ በስንፋና የተዋጠ እና የፍቅር እሳትን የሚያዳፍን ነው። ለብ ያለ ሰው እሱ ወይም እሷ የራሱን ምቾት ለማርካት ብቻ ይኖራል ወይም ትኖራለች፣ በዚህም ማንም አይጠግብም፣ የእንዲህ ዓይነት ክርስቲያን ሕይወት ቀስ በቀስ በሁለት ነገሮች መኋል የተወጠረ ሕይወት ሆኖ ሕይወቱ ይጠናቀቃል። ለብ ያለ ሰው ለእግዚኣብሔር እና ለሌሎች የተወሰነ የጊዜ እና የአገልግሎት ኮታን በመስጠት ልባቸውን ሙሉ በሙሉ ሳይሰጡ ልባቸውን በቁጠባ የሚጠቀሙ ሰዎች ናቸው። ስለዚህም እርሷ ወይም እርሱ በሕይወት ውስጥ ብዙ ውጊያ አይገጥማቸውም በአንጻሩም እንደ ቀዘቀዘ እና ለመጠጣት አስቸጋሪ እንደ ሆነ አንድ ብርጭቆ ጥሩ ሻይ ይሆናሉ ማለት ነው። ከእናንተ በፊት በእምነት ጎዳና ያለፉትን ሰዎች በምታዩበት ወቅት ሁሉ እርግጠኛ ነኝ ልባችሁ ልብ እንዲል የምትፈቅዱ አይመስለኝም። መላው ቤተ ክርስቲያን ለእናንተ ልዩ ፍቅር በማሳየት ረገድ የማበረታቻ ቃላትን ያቀቡላችኋል። እናንተ በእግዚኣብሔር እይታ ውስጥ ውድ የሆናችሁ ትንሽ መንጋዎች ናችሁ።

ለብ ያልን ሰዎች በመሆናችን የተነሳ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን እንደ አለቃ እራሳችንን በምንቆጥርበት ወቅት እና እራሳችን ለሌሎች አገልግሎት የምናውለው ጥቅምን ለማግኘት ወይም ሌላውን ሰው ለመምሰል ከመጠን በላይ በሆነ መልኩ በምናሳየው ነገር የሚፈጠር ሁለተኛ ፈተና አለ። በእንዲህ ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ አገልግሎት ዘዴ እንጂ ዋናው የመጨረሻው ግብ አይሆንም ምክንያቱም ግቡ ክብር መጎናጸፍ ስለሆነ፣ ቀጥሎም ስልጣን እና ትልቅ ሰው ለመሆን የመፈለግ አባዜ።  “በእናንተ መካከል ግን እንዲህ አይሁን” በማለት ኢየሱስ ሁላችንንም ያሳስበናል “ነገር ግን ከእናንተ መኋከል ታላቅ ለመሆን የሚፈልግ ሰው የሁሉም አገልጋይ ይሁን” (ማቴዎስ 20.26)። በዚህ መንገድ ብቻ ነው ቤተ ክርስቲያን የምታድገው እና የምታጌጠው። ስለ ምንጣፍ ያለንን ምስል በድጋሜ በምንመለከትበት ወቅትና ለእዚህ ለእናንተ መልካም ማሕበረሰብ በምንመነዝርበት ወቅት ከእናንተ እያንዳንዱ ዕጹብ ድንቅ የሐር ፈትል ይሆናል። በአንድነት በምትሸመኑበት ወቅት ግን በተለያዩ መልካም ነገሮች እንደ ተሸመነ ውብ ምንጣፍ ትሆናላችሁ፣ ለብቻችሁ ግን ምንም ጥቅም ሊኖራችሁ አይችልም። ስለዚህ ሁል ጊዜም በትህትና ልገሳ እና አንድ በመሆን ሕብረታችሁን በመጠበቅ ኑሩ፣ ለዚህም ከልዩነቶች ሕብረትን የሚፈጥረው ጌታ ይጠብቃችኋል።

ያለአዳም ኋጥያት የተጸነሰች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በማላጅነዋ፣ በኋይሏም ታግዘን በተለይም ደግሞ የእምነት ሥራቸው እና አገልግሎታቸው በመኋከላችሁ የሚገኘው የቅድስት እማሆይ ትሬዛ ዘ ካልካታ አማላጅነትም ይድረሳችሁ። በዛሬው መልዕክት ውስጥ የተጠቀሰውን የእርሳቸውን ቃል እንዲህ አጠቃልዬ ልንገራችሁ “የእምነት ፍሬ ፍቅር ነው፣ የፍቅር ፍሬ አገልግሎት ነው፣ የአገልግሎት ፍሬ ሰላም ነው”።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.