2016-09-26 16:51:00

ኰሎምቢያ የሰላም ስምምነት ሰነድ ፍርርም


በኰሎምቢያ ለ 52 ዓመት አገሪቱን ያደማው በመንግሥት የመከላከያ ኃይልና ፋርክ በመባል በሚጠራው የትጥቅ ትልግ የሚያረማምደው ማርክሳዊ  የኰሎምቢያ አቢዮታዊ ግንባር መካከል እ.ኤ.አ. መስከረም 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በተደረሰው የሰላም ስምምነት ፍርርም እልባት ሊያገኝ ነው ተባለ።

ይኽ እ.ኤ.አ. ከ 1964ዓ.ም. ጀምሮ ይካሄድ በነበረው ግጭት ሳቢያ 220 ሺሕ የአገሪቱ ዜጎች ለሞት ሌሎች 45 ሺሕ መጥፋት ምክንያትና እንዲሁም 7 ሚሊዮን ሕዝብ ለመፈናቀል ላቅመ አዳም ያልደረሱ ወጣት ሕፃናት ለሽምጥ ተዋጊነት አደጋ ያጋለጠው ጦርነት እልባት እንዲያገኝ አቢይ ሚና ከተጫወቱት አገሮች ውስጥ ቫቲካን የሚጠቀስ ሲሆን። ቅድስት መንበር እ.ኤ.አ. ሰኔ 23 ቀን 2016 የሰላም ስምምነት እንዲደረስ በኩባ ገላጋይነት ተደርጎ የነበረው የሰላም ውይይትና የተደረሰው የቶክስ አቁም ስምምነት በመደገፍ ቀጥሎም ሙሉ የሰላም ስምምነት እውን እንዲሆን ካለ መታከት ጥረት ማድረጓ የሚታወስ ሲሆን፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. በ 2017 ዓ.ም. ኮሎምቢያን ለመጎብኘ ፍላጎቱ እንዳላቸው ይፋ አድገው እንደነበርም ጠቅሶ፥ በካርታጀና ደ ኢንዲያስ ከተማ የሰላም የስምምነት ሰነድ ፍርርም በተካሄደው ሥነ ስርዓት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ዋና ጸሐፊ ጆን ከርይ የኤውሮጳ አገሮች ኅብረት የውጭ ፖለቲካ ተጠሪ ሞገሪኒ የዓለም ባንክ ቤት ሊቀ መንበር ኡም ዮንግ ኪም የመክሲኮ የጓተማላ የሆንዱራስ ኤል ሳልቫዶር ኮስታ ሪካ ፓናማ ኩባ ቨነዝዋላ የረፓብሊካዊት ዶመኒካን ኤኳዶር የፐሩ የቺለና የፓራጉዋይ መራሕያን መንግስታት እንዲሁም የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን መገኘታቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ካጠናቀሩ ዘገባ ለመረዳ ተችሏል።

ከተደረሰው የሰላም ስምምነት በኋላ የኰሎምቢያ መንግሥት የሚጋፈጠው ተግዳሮት ቢኖር የአብዮታዊው ታጣቂ ኃይል ግንባር አባላት ወደ ሰላማዊ ኑሮ ለመመለስ የማድረጉ ሂደት በተያያዘ መልኩም  ብዙኃኑ የአገሪቱ ዜጋ በተደረሰው የሰላም ስምምነት ላይ አመኔታ የሌለው በመሆኑ የሰላም ስምምነት  ሙሉ በሙሉ ገቢራዊ እንዲሆን የኵሎምቢያ ሕዝብ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚሰጠው የድምጽ ውሳኔ ተከትሎ ሕዝብን የማሳመን ጉዳይ ተጨማሪ አቢይ ተግዳሮት  መሆኑ ኢዛበላ ፒሮ ባጠናቀሩት ዘገባ ያመለክታሉ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.