2016-09-24 11:03:00

ቅዱስነታቸው "ስግብግብነት፣ እብሪት እና ኩራት" የሰውን ልጅ የሚያበላሹ ነገሮች ናቸው አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 22/2016 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት ከመንፈስ ቅዱስ ከሚመጣ ጉጉት እና ከአደፈ ሕሊና ከሚመጣው ጉጉት መካከል ንጽጽርን በማድረግ ስብከታቸውን ጀምረው እብሪት ሕይወታችንን ጭንብል በማልበስ ያልሆነውን ነገር እንደ ሆንን እንዲሰማን ያደርጋል ማለታቸው ተገለጸ።

ዛሬ የተነበበልን ቅዱስ ወንጌል (ሉቃ. 9.7-9) ንጉሥ ሂሮድስ ግራ መጋባቱን ወይም በከፍተኛ ሥጋት ውስጥ መግባቱን አሳይቶናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም መጥመቁ ዩሐንስን አስገድሎት ስለነበረ እና አሁን ደግሞ በኢየሱስ መምጣት ስጋት ስለተሰማው መሆኑን ገልጸዋል።

ሂሮድስ ልክ እንደ አባቱ ታላቁ ሂሮድስ፣ ሰባሰጎልች መጥተው በጎበኙት ወቅት የተሰማውን  አይነት ጉጉት ነበር የተሰማው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም ላይ ተመስርተው በነብሳችን ውስጥ ሁለት ዓይነት ጉጉቶች አሉ “ነብሳችን መልካም ነገር እስክትሠራ ድረስ እረፍት የሚነሳት ከመንፈስ ቅዱስ የሚመነጭ መልካም ጉጉት” የመጀምሪያው መሆኑን ገልጸው መጥፎ ጉጉት ደግሞ “ከአደፈ ሕሊና እንደ ሚመነጭ” ጠቁመው ሁሉቱም ሂሮድሶች (ማለትም አባት እና ልጅ) ጉጉታቸውን ለመፍታት የተጠቀሙበት ዘዴ መግደል እና በገደሉት ሰው “ሬሳቸው ላይ መረማመድ” እንደ ነበረ ገጸዋል።

እንደዚህ ዓይነት ክፋትን የሚሠሩ ሰዎች ያደፈ ሕሊና ነው ያላቸው፣ በስላም መኖር አይችሉም ምክንያቱም እነርሱ በቀጣይነት እንዲሁም በችኮላ በዚህ ክፋት ውስጥ እየኖሩ ስለሆነ ስላም ይርቃቸዋል. . . .እነዚህ ሰዎች ክፋትን ፈጽመዋል፣ ማንኛውም አይነት ክፉት ሥረመሰረቱ ተመሳሳይ ነው ስግብግብነት፣ እብሪት እና ኩራት ናቸው። እነዚህ ሦስት ነገሮች ሕሊናችን ሰላሙን እንዳያገኝ ያደርጉታል። እነዚህ ሦስቱ ነገሮች መንፈስ ቅዱስ  ጤናማ ወደ ሆነ መቅበጥበጥ እንዳያስገባን በማገድ በጉጉትና በፍርሃት እንድንኖር ያደርጉናል። ስለዚህም  ስግብግብነት፣ እብሪት እና ኩራት የክፍት ሥርመሰረት ናቸው።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት በእለቱ የተነበበው የመጀመሪያ ምንባብ የተወሰደው ከመፅሐፈ መክብብ መሆኑን እና የሚያወሳውም ስለ ክንቱነት መሆኑን በማውሳት እንደ ገለጹት፣

እብሪት እንድናብጥ ያደርገናል። ይህም እብሪት ከሳሙና እንደ ሚወጣ አረፋ ረጅም ሕይወት የለውም። እብሪት እውነተኛ ነገርን አያጎናጽፈንም። ሁሉንም ጥረቱን ለመጨናንቅ ያዋለ ሰው ምን ዓይነት ትርፍ ሊያገኝ ይችላል? ለመታየት ይሰጋል፣ ያስመስላል፣ ያልሆነውን ለመሆን ይሞክራል። ይህ ደግሞ እብሪት ነው። በቀላሉ ቋንቋ እብሪት እውነተኛ ሕይወታችንን ይሸፍናል። ይህም ደግሞ ነብሳችንን ያሳምማታል። ምክንያቱም በመጨረሻ ትክክለኛ ሕይወታቸውን ሸፍነው በሚቀርቡበት ጊዜ ወይም ሌላን በሚመስሉበት ወቅት ሁሉ . . . የሚሰሩት ሥራ ሁሉ ለማስመሰል ነው. . . እነዚህ ምን ያገኛሉ? እብሪት ልክ እንደ አጥንት በሽታ ነብስን ይቦረቡራል. . . አጥንት በበሽታ በሚጠቃበት ወቅት አጥንቱ ከውጭ ሲመለከቱት ደህና ይመስላል ነገር ግን ውስጡ ተበላሽቱዋል። እብሪት እኛን የሚያጨበረብረን እንዲሁ ነው ብለዋል።

እብሪት ነብሳችንን እረፍት የሚነሳ ነገር መሆኑን በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቅዱስ በርናዶስ ስለከንቱነት የተናገራቸውን ቃላትን ተጠቅመው “በመጨረሻ የምትሆነውን አስብ፣ የምትሆነውም የትሎች ምግብ ነው” በማለት ጠቅሰው ይህንንም የቅዱስ በርናዶስ ጥቅስ ተከትለው ‘ሕይወታችንን የምንቀባባው ነገር ሁሉ ውሸት ነው፣ ምክንያቱም ትሎች በልተው ስለ ሚጨርሱን እብሪት ምን አይነት ብርታት አለው? ብለው ጥያቄን አቅርበው በኩራት ተመርተን ወደ ውድቀት እናመራለን ይህም ስህተቶቻችንን እንዳናይ ይከለክለናል “ሁሉንም ነገር ይሸፋፍናል፣ ስለዚህም ሁሉም ነገር ሽፍን ይሆናል” ብለዋል።

ያልሆኑትን ሆኖው የሚገኙ ብዙ ሰዎችን እናውቃለን፣ ‘እንዴት ያለ ጥሩ ሰው ነው። በየእሁዱ ቅዳሴን ያስቀድሳል” ቤተ ክርስቲያንን በገንዘብ ይደግፋል። ነገር ግን እንደ አጥንት በሽታ ሙስና ውስጣቸውን መጥምጦ የጨረሳቸው ቢሆንም ቅሉ የሚታዩት ግን እንደ መልካም ሰው ነው። እንዲህ አይነት ሰዎችም አሉ…ቅዱስ ሊባሉ የሚችሉም ብዙ ሰዎችም ይኖራሉ። ምንድነው እርሱ ይህንን አይነት ተግባር እንድንፈጽም የምያደርገን”? እንደ መልከ መልካም ስዕል ሆነን እንድንታይ ነገር ግን እውነትው የተገላቢጦሽ እንዲሆን የሚያደርገን ዋንኛው ነገር እብሪት ነው። ታዲያ ጥንካሬያችን፣ ደህንነታችን እና እንዲሁም መሸሸግያችን የት ነው? ብለው ይህም በመዝሙረ ዳዊት እንደምናነበው “ጌታ ሆይ ከትውልድ እስከ ትወልድ አንተ መሸሸግያችን ነህ’ እንዳለው ሁሉና እንዲሁም በወንጌል ውስጥ ኢየሱስ ‘እኔ መንገድ፣ እውነትና ሕይወት ነኝ’ ያለው የእብሪትን የፊት ማስዋቢያነት ለመግለጽ ሳይሆን ከእነዚህ የክፋት ምንጮች ከሆኑት ስግብግብነት፣ እብሪት እና ኩራት ተወግደን በተልይም ደግሞ ክፉ ከሚያደርገንን እብሪት ነፃ እንድንሆን አምላክ ይርዳን’ ብለው የእለቱ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.