2016-09-23 16:42:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ከመስከረም 19 ቀን እስከ መስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በተጠራው ዓለም አቀፍ የመሪዎች ጉባኤ የቅድስት መንበር ልኡካንን በመምራት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን በመሳተፍ ንግግር ያስደመጡ ሲሆን። ከዚህ ውጭም ከመሪዎች ጉባኤ በተያያዘ መልኩ በተከናወኑት አበይት ጉባኤ ተገኝተው ንግግር አሰምቷል።

ብፁዕነታቸው በዚህ ስደተኞችና ተፈናቃዮች ርእስ ዙሪያ በመከረው በዓለም አቀፍ የመሪዎች ጉባኤ ባስደመጡት ንግግር፥ ከጠቀሱዋቸው ነጥቦች ውስት በዓለማችን ለተለያዩ ጸረ ረቂቀ ነፍሳት በመባል የሚታወቀው መድኃኒትና ለተዛማጅ በሽታዎች ፍወሳ የሚሰጡት መድኃኒቶች የሚቋቋሙ ሰዎች ብዛት እጅግ በሚያስደነግጥ ሁኔታ ከፍ እያለ መምጣቱ የሚለውን የጠቀሱት የቫቲካን ርዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ በማስከተል፥ ብዙ ተሀዋስያን የጸረ ተህዋስ መድኃኒት የሚቋቋሙ በመሆናቸው ታማሚው ሰው በቀላሉ አደጋ ተጋልጦ ይገኛል። ስለዚህ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይኸንን እግምት ውስጥ በማስገባት በጤና እንክብካቤና ባስቀድሞ የመከላከል መርሃ ግብር ላይ በመጠመድ ለዚህ ዓላማ አቅሙንና በቂ መዋዕለ ንዋይ እንዲያውል ጥሪ በማቅረብ ህክምና ማግኘተ አንዱ የሰብአዊ መብትና ክብር የሚያመለክተው  ነው፡ ስለዚህ የሁሉም የጤና እንክብካቤ አገልግሎት የማግኘት መብት አለ ምንም ቅድመ ሁኔታና አድልዎ ሊከበር ይገባዋል እንዳሉ ገልጧል።

ብፁዕነታችው ቅድስት መንበር በቀላሉ ለአደጋ የሚጋለጡት ዜጎች ድጋፍ እንዲቀርብላቸው ዘወትር የምታቀርበው የቃልና ተግባራዊ ጥሪ አስታውሰው ባስደመጡት ንግግር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባሕ በሚል ርእስ ዙሪያ የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ዋቢ ያደረጉ መሆናቸው ዶኒኒ ገልጠው፥ ሕክምና የማግኘት አገልግሎ የሁሉም መብት ነው፡ ስለዚህ የሕክምና አገልግሎት ለሁሉም ማዳረስ ግዴታና ኃላፊነት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በላይ የሁሉም ሰው ልጅ ሰብአዊ መበትና ክብር የሚመለከት መሆኑ ሊስተዋል ይገባዋል፡ በድኽነት ለተጠቁት በድኾች አገሮች የሰው ልጅ ሕክምና የማግኘት መብትና ክብሩ እንዲጠበቅ የማድረጉ ኃላፊነት ዓለም አቀፋዊና ብሔራዊ አቀፍ ጉዳይ መሆኑም ያብራሩ ሲሆን፡ ሌላው የዳሰሱት ነጥብ አለ አግባብ መድኃኒት የመጠቀሙ ተግባር ልሙድ እየሆነ በሰው ላይ የሚያስከትለው የጤና መቃወስ  በእርሻው መስክ ሳይቀር አለ አግባብ መድኃኒት የመጠቀሙ ሂደትም በሰውና በተፈጥሮ ላይ አቢይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑና ይኸንን ጉዳይ ምኅዳር መንከባከብ ከሚለው ኃላፊት ጋር በማያያዝ ሰፊ ትንተና ሰጥተውበታል ብለዋል።

ሌላው ስደተኛውና ተፈናቃዩ መደገፍና ማስተናገድ አስፈላጊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለስደትና ለመፈናቀል የሚዳርጉት ምክንያቶች መፍትሔ እንዲያኙ የማድረጉ ጥረት ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባውና ስደተኛው ላለ ማስተናገድ የሚቀርቡት ምክንያቶች ስደተኛው መቀበልና ማክበር ከሚለው አመክንዮ አይበልጥም። ስለዚህ ላለ መቀበል ምንም ምክንያት ሊኖር አይችልም እንዳሉ ዶኒኒ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.