2016-09-16 16:31:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፥ ለቅዱስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን ያስደመጡት ስብከት


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን በዚህ በምሕረት ዓመት ምክንይት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት የተጠራው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን ኢዮቤዩ ቀን እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ ተጀምሯል።

ብፁዕ ካርዲናል በጠቅላላ በ 106 የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡካን ታጅበ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚካ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባስደመጡት ስብከት፥ በቅድሚያ ይኸንን ቀን ለጠሩትን የምኅረት ዓመት ያወጁትን ቅዱስ አባታችንን እናመሰግናለን ብለው ሁሉም ስለ ቅዱስ አባታችን እንዲጸልዩ አደራ ማለታቸውንም የቅድስት መንበ የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የማርያም ሕማማት የምታስብበት ዕለት መሆኑንም ዘክረው። ይኽ የማርያም ህማማት በዓል ናፖሊዮን በቤተ ክርስቲያንና በቅዱስ ጴጥሮ ላይ ያወረደው ስቃይና ግፍ ማእከል በማድረግ የደነገጉት ር.ሊ.ጳ. ፒዮስ ሰባተኛ መሆናቸው በማስታወስ ዝክረ በዓሉ ከቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ጥብቅ ግኑኝነት ያለው መሆኑንም ማብራራታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ብፁዕነታቸው እ.ኤ.አ. በ2017 ዓ.ም. ዝክረ አንድ መቶኛው ዓመት ግልጸተ ማርያም ዘፋጢማ እንደሚከበርና በዚያ ቅዱስ ሥፍራ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መንፈሳዊ ንግደት ለመፈጸም ጥልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጠው፡ በዓሉ ስለ እምነታችን የደም ሰማዕትነችን ለመቀበል ዝግጁነታቸው የምናስተውልበት ዕለት ነው ብለው፡ ትናንትናና ዛሬም ነገም ቤተ ክርስቲያንና የቅድስ ጴጥሮስ ተከታይን የሚገልጥ ክቡር መለያ ሰማዕትነ ነው፡ ከዚህ ጋር በማያያዝም እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 1981 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳማዊ ላይ ብዙ ዓመታት ቀደም ብሎም እ.ኤ.አ. ህዳር 27 ቀን 1970 ዓ.ም. በጳውሎስ ስድስተኛ ላይ የተጣለው ጥቃት ዘክረው። … የክርስቶስ ህማማት ዛሬም እተቀጠለ ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስቲያን ስቃየ ክርስቶስ መለያዋ ነው። ለክርስቶስ ባላት ታማኝነት ታዛዥነና ለሐቅ ትሰቃይ ዘንድ ግድ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. መስከረም 14 ቀን 2016 ዓ.ም. በፈረንሳይ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በአሸባሪው እስላማዊ አገር ተከታዮች እጅ የተገደሉት አባ ዣከስ ሃመል ለማሰብ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ቤተ ክርስቲያናችን  የሰማዕታት ቤተ ክርስቲያን ነች እንዳሉት ነውን ቤተ ክርስቲያን የሰማዕታት ቤት ነች እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና የኅትመ ክፍል መግለጫ ያስታውሳል።

በተለያዩ የዓለማችን ክልሎች የሰማዕትነትን ሕይወት ዕለታዊ ኑሮአቸው ሆኖ ለስደት ለመከራ ለእንግልት የሚጋለጡትን እናስታውስ። ስለዚህ የሊቃነ ጳጳሳቱ የሐዋርዊ ልኡክነት ጥሪ በመስቀል ሥር የሚኖር ነ። መስቀል ማግለል ሳይሆን መስቀልን ለመመስከር ልክ እንደ ማርያም ጥሪያችንና አገልግሎታችን መስቀል ሥር ተኩኖ የሚኖር ነው፡  እንደ ማርያም በኢየሱስ ሕማማትን መሳትፍ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ጠቁሞ፡ ከዚሁ ጋር በማያያዝም የእመ ወድንግለ ጽሙረ መንፈሳዊነት ያለው ውበትና መሰረታዊ አስፈላጊነት ለይተው ጥልቅ ትርጉሙንም በማብራራት፡ ትንሽም ይሁን አቢይ የምንላቸውን ዕለታዊ መስቀሎቻችን ለእግዚአብሔር የተገባ መስዋዕት ሆኖ እንዲቀርብ በመስቅል ሥር መሆን ያስፈልጋ። በዚህ ዓለም የሰዎች ዕለታዊ መስቀል የክርስቶስ መስቀል ህልው ነው። አሁንም ክርስቶስ በተለያዩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ሕይወት ስቃይና መከራ ስቅላቱ እየቀጠለ ነው፡ በድኻው በተጠማው በሚሰቃየው የሚገለጠው ስቁል ኢየሱስ ነው። በፍቅርና በምህረት በርህራሄና በወንድሞቻችን እህቶቻችን ስቃይ መሳተፍ እንጂ ከሚሰቃየው መሸሽ ጥሪያችን አይደለም። በመስቀል ላይ ክብርና ምስጋና እንዲሁም ደስታ ይገኛል ይኽ ነው ክርስትና ማለት። ስለዚህ በመስቀል ሥር መሆን ያስፈልጋል በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመ ክፍል መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.