2016-09-16 16:14:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ የላቲን ሥርዓት ሕገ ቀኖናና የምስራቅ ሥርዓት ሕገ ቀኖና ለተወሃደ ስምምነት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባላቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሥልጣን መሠረት በኩላዊት ቤተ ክርስቲያን የላቲን ሥርዓት ሕገ ቀኖና የምስራቅ ሥርዓት ሕገ ቀኖና የተወሃደ ስምምነ የሚያሰጥ በተለይ ደግሞ ሕገ ቀኖናዊ ውህደት በሚል ሐዋርያዊ መልእክት ሥር እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2016 ዓ.ም. የደነገጉት ሕግ እ.ኤ.አ. መስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ መብቃቱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ ገለጡ።

ይኽ አዲሱ በሐዋርያዊ መልእክት ሥር ቅዱስ አባታችን ያስተላለፉት ውሳኔ፥ ምሥጢረ ክህነት ምሥጢረ ተክሊል ምሥጢረ ጥምቀት ዙሪያ በተደጋጋሚ ይቀርብላቸው የነበረውን ሃሳብና አስተያየ ብሎም ጥያቄ ሁሉ በማሰባሰብ በቅዱሳት ምሥጢራት ዙሪያ ብዙውን ጊዜ ለየት ባለ መልኩ ምሥጢረ ክህነት ጉዳይ ላይ በልዩ በማተኮር ኢደንባዊ ቅብኣ ክህነት ማእከል በማድረግ ይኽ አይነቱ አወዛጋቢ ጉዳይ መፍትሔ እንዲያገኝ አልመው የደነገጉት ሕግ ሲሆን። ሁለቱ ሥርዓቶች ለተወሃደ ስምምነት የሚያደርስ መሆኑም የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አኵይሊኖ አያዘው፥ በላቲን ሥርዓት በሚከተሉት ሰበካዎች ግዛት ሥር የምስራቅ ሥርዓት የሚከተሉት ምእመናን በብዛት የሚገኙ በመሆናቸውም የምዕራቡ ዓለም በብዛት የላቲን ሥርዓት የሚከተል ቢሆንም በተለያየ መክንያት ከምስራቁ ዓለም ወደ ምዕራቡ ዓለም የሚገባው ዜጋ ብዛት ግምት በመስጠት እነዚህ የምሥራቅ ሥርዓት ከምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሚመጡት የሚቀበሉት ቅዱሳት ምሥጢራት በላቲን ሥርዓ የምትከተለው ቤተ ክርስቲያንም ቢሆንም የምስራቅ ሥርዓት ተከታይ ምእመና መሆናቸው ለተቀበሉት ቅዱሳት ምሥጢራት ማረጋገጫ በሚሰጠው አመሳካሪ ወረቅት ዘንድ ሊሰፍር እንደሚገባው ያስገነዝባሉ። ስለዚህ ይህ ደግሞ የላቲን ሥርዓት ሕገ ቀኖናና የምሥራቅ ሥርዓት ሕገ ቀኖና የተወሃደ ስምምነት እንዲኖረው የሚያደርግ መሆኑ ያመለታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.