2016-09-14 16:32:00

የካቶሊካዊትና የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፍ ቅይጡ የጋራው የቲዮሎጊያዊ ድርገት 14ኛው ክፍለ ምሉእ ጉባኤ


ለአንድ ሳምንት በኢጣሊያ አብርዞ ክፍለ ሃገር የተለያዩ የአቢያተ ክርስቲያን አሃድነት ርእሰ ከተማ እንድትሆን የሚያደርጋት ጳጳሳዊ ዓለም አቀፍ የካቶሊካዊትና የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቅይጥ የቲዮሎጊያዊ ውይይት ድርገት 14ኛው ክፍለ ምሉእ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 15 ቀን እስከ መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደምታስተናግድ ቅይጡ የቲዮሎጊያዊ የጋራው ውይይት ድርገት የሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የጠቀሱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ አስታወቁ።

ይኽ ዓለም አቀፍ የካቶሊካዊትና የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የጋራው ቅይጡ የቲዮሎጊያዊ ውይይት ድርገት እ.ኤ.አ. ህዳር 30 ቀን 1979 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ፋናርን ጎብኝተው የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ዲሚትሪዮስ ቀዳማዊ ጋር በተገናኙበት ወቅት በጋራ ያቋቋሙት ድርገት ሲሆን፡ ድርገቱ የመጀመሪያው የጋራውን ጉባኤውን እ.ኤ.አ. በ 1980 ዓ.ም.  በግሪካዊቷ ደሴት ፓትሞስና ሮዲ ማከናወኑ ያስታወሱት ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘው፥ ከዚያ እሩቅ ዓመት ወዲህ የጋራው ድርገት ባካሄዳቸው የጋራ ጉባኤዎች ፍጻሜ በኋላ አምስት ሰነዶች እርሱም፥ እ.ኤ.አ. በ 1982 የቤተ ክርስትያን ትእምርታዊ ምስጢርና ቅዱስ ቁርባን ቅዱስ ሚሥጢር በቅድስት ሥላሴ ብርሃን በሚል ርእስ ሥር በጀርመን ሞናኮ ከተማ ቀጥሎም በኢጣሊያ ባሪ ከተማ ባካሄደው የጋራው ውይይት ቀጥሎ እምነት ቅዱሳት ሚሥጢራትና የቤተ ክርስቲያን አሃድነት እ.ኤ.አ. በ 1987 ዓ.ም.። በፊንላንድ ቫልሞ ከተማ እ.ኤ.አ. በ 1988 ዓ.ም. የቅዱሳት ምስጢራት ሥርዓት የቤተ ክርስቲያን መዋቅሮች በቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሚሥጢራዊነት በሚል ርእስ ሥር የተደረሰውና ብሎም እ.ኤ.አ. በ 1993 ዓ.ም. በሊባኖስ ባላማንድ ከተማ አሃድነት፡ የቀድሞው የአንድነት ዘዴና ወቅታዊው የምሉእ አሃድነት ተስፋ በሚል ርእስ ሥር በመጨረሻም እ.ኤ.አ. በ 2007 ዓ.ም. በኢጣሊያ ራቨና ከተማ የሥነ ቤተ ክርስቲያንና የሕገ ቀኖና ምሥጢራዊ ክትያ በቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ምሥጢራዊ በሚል ርእስ ሥር የተደረሱትን የጋራ የስምምነት ሰነዶችን በማስታወስ፡ ይኽ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 5 ቀን እስከ መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም.  በኢጣሊያ የአብሩዞ ክፍለ ሃገር በሚገኘው የኪየቲና ቫስቶ ሰበካዎች ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ብሩኖ ፎርተ ባቀረቡት ጥሪ መሠረት በሰበካቸው ኪየቲ ከተማ የጋራው ጉባኤ እንደሚካሄድ የጋራው ድርገት ጉባኤው ለምታስተናግደው ከተማ ኪየቲ ሊቀ ጳጳሳት ዓለም የአቀፍ የካቶሊካዊትና የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቅይጡ የጋራው የቲዮሎጊያ ድርገት አባል ብፁዕ አቡነ ፎርተ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰው አስታውቀዋል።

የሚካሄደው ጉባኤ በጋራው ድርገት ተኗኗሪ ሊቀ መናብርት የክርስቲያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽና ለቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ልኡክ በተልመሶስ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ጆብ ገትኻ የሚመራ ሲሆን፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከብፁዕ አቡነ ፎርተ በተጨማሪ ብፁዕ ካርዲናል ኮኽና ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጆብ ገትኻ መሳተፋቸው ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ ገልጠው፡ ይኽ በእንዲህ እንዳለም ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ገትኻ በቅርቡ በእድሜ መግፋት ምክንያት የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በዚህ የጋራው የቲዮሎጊያ ዓለም አቀፋዊ ድርገት በተኗኗሪ የሊቀ መንበርነት ሥልጣን ሲያገልግሉ ለነበሩት ታዋቂ የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የቲዮሎጊያ ሊቅ መጥሮፖሊታ ዮአኒስ ዚዙላስን እንዲተኩ በቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ የተሾሙ መሆናቸው ፒሮ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.