2016-09-14 16:42:00

ኬንያ፥ በአፍሪቃ ሰላም ለማነቃቃት


በኬንያ በሚገኘው የካቶሊክ ተቋም ታንጋዛ ዩኒቨርሲቲና በጀርመን አኸን ከተማ ዋና መቀመጫው የሆነው ሚሲዮ የተሰየመው የግብረ ሠናይ ማኅበር በጋራ በአፍሪቃ ሰላም የሚያነቃቃ አንድ ዓለም አቀፋዊ የሰላም አጥኚ ቡድን እንዲመለመል ያለመ ዓዋደ ጉባኤ በኬንያ ርእሰ ከተማ ናይሮቢ ሃይማኖቶችና አመጽ በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ መካሄዱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ሲር የዜና አገልግሎት ጠቀስ ዘገባቸው ይጠቁማሉ።

የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ግጭትና አመጽ እንዲወገድ የሚያደርግ መሣሪያ ነው

ሰላም ለመሻትና ሰላም ለማረጋገጥ ያለመ  የአንድ ክልል አመጽ መለያው መንስኤውና ባህርዩን በመለየት በጥልቀት አንብቦ መጽሓፍ ቅዱሳዊ ስነ ምግባራዊና ባህላዊ ህየሳ በመስጠት ከወቅታዊው ሁነት ጋር በማገናዘብ በአመጽ ተወናያን አካላት መካከል እርቅ እንዲተገበር ለመደገፍ የሚል ዓላማ ያለው ሰላም የሚያነቃቃ ዓለም አቀፋዊ የሰላም አጥኚ ማኅብር መሆኑ በናይሮቢ የካቶሊክ ተቋም ታንጋዛ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ወንጌላዊ ልኡክነትና የሥነ ምስልም ጉዳይ ለሚመለከተው ዘርፈ ትምህርት ኃላፊ አባ ፈሊክስ ፊሪ መግለጣቸው ሲር የዜና አገልግሎት የሰጠው ምንጭ በማስደገፍ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አስታውቋል።

የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የሰላም አጥኚዎች ማኅበር ማቋቋም ካለው አስፈላጊነት ጋር በማያይዝም ሃይማኖትና አመጽ በመጽሓፍ ቅዱሳዊ ትንተና በመላ አፍሪቃና በአፍሪቃ ማኅበረ ክርስቲያን ሥነ ምግባራዊ እይታ፡ የግጭትና የጦርነት ማሕበራዊና ኤኮኖሚያዊ መንስኤ፡ ማኅበራዊ ግፉዓን በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ዓመጽና የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ግጭትና ጦርነት ሰላማዊ ማስገኛ በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይትና የሃሳብ ልውውጥ መካሄዱ ሲር የዜና አገልግሎት የሰጠው የዜና ምንጭ የተጠቀሱት ፒሮ ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.