2016-09-08 13:36:00

ቅዱስነታቸው "በእያንዳንዱ ቀን ሰላምን ለማረጋገጥ የምናከናውናቸው ጥቃቅን ተግባራት ለአለም ሰላም ከፈተኛ አስተዋጾ አለው" አሉ


በእያንዳንዱ ቀን በምናከናውናቸው ተግባራት ውስጥ ሰላምን ለመፍጠር የምናደርጋቸው ጥቃቅን ተግባራት በዓለም ደረጃ ሰላም እንዲረጋገጥ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ ይህንን ለማከናወን የሚያስችለንን ጥበብ እንዲሰጠን እግዚአብሔርን መጠየቅ እንደ ሚገባ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 8-2016 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከታቸው መናገራቸው ተገለጸ።

“ሰላም በአለማቀፍ ደረጃ በሚደረጉ ታላላቅ ስምምነቶች ብቻ ሊረጋገጥ አይችልም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሰላም በትናንሽ ለምሳሌም እንደ ልባችን በመሳስሉ ስፍራዎች የሚፈጠር ወይም ደግሞ ዮሴፍ ተኝቶ በነበረበት ወቅት የእግዚአብሔር መልዐክ  አማኑኤል ወይም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው” የተባለውን ለአለም ልታበረክት ተዘጋጅታ የነበረች እጮኛውን ማሪያም እንዳይተው በሕልሙ እንደተገለጠለት ዓይነት ግልጸት ከእግዚአብሔር የሚሰጥ ስጦታ መሆኑን ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ መግቢያ ላይ በተደረገው የመግቢያ ጸሎት ላይ “ሁላችንም በአንድነት እና በሰላም እናድግ ዘንድ” በሚለው ቃል ላይ ተመርኩዘው እና “ሰላም” በሚለው ቃል ላይ አጽኖት ሰጥተው በቀጠሉት ስብከታቸው “ማደግ” የሚለው ቃል ቅዱስነታቸው አጽኖት ሰጥተው ሰላም በሕይወት ሂደት ውስጥ የሚፈጠር ስጦታ በመሆኑ ሁላችንም ይህ ሰላም ያድግ ዘንድ በየቀኑ አስተዋጾ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለዋል።

“የቅዱሳንም ሆነ የኋጥያተኞች መንገድ እንደ ሚያሳየን ይህንን የሰላም ስጦታ የግድ መቀበል እንዳለብን እና የሕይወታችን መንገድ እንዲሆን በመድረግ፣ በውስጣችን እንዲገባ እንዲሁም በአለማችን ውስጥ እንዲንሰራፋ ማድረግ ይጠበቅብናል ብለው ሰላም አንዱን ቀን ዘለን በሌላው ቀን የምንፈጽመው ተግባር ሳይሆን በየቀኑ ሊተገበር የሚገባው ስጦታ ነው” ማለታቸውም ታወቁዋል። “ስለዚህም” አሉ ቅዱስነታቸው “ስለዚህም ሰላም በሰው ልጆች መዳፍ ውስጥ የሚገኝ ስጦታ ነው፣ እኛ የሰው ልጆች ነን በእየ እለቱ በተግባሮቻችን የሰላም እርምጃዎችን ማድረግ የሚጠበቅብን፣ ተግባሮቻችን ከተሰጠን ስጦታ ጋር በማቀናጀት ሰላምን ማስፈን አለብን” ብለዋል።

“ነገር ግን እንዴት ነው ይህንን ግብ መምታት የምንችለው?” ብለው ጥያቄን በማንሳት ሰብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእለቱ ስርዓተ ቅድሴ እየተከብረ የሚገኘው የማሪያም ውልደትን አስመልክተው እንደ ገለጹት “ትንሽነት” የሚል አጉዋጊ ቃል እንዳለ ገልጸው ቤተልሔም በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ ትንሽ የሆንች ሀገር እንደ ነበረች ዋቢ በማድረግ. . .”ሰላም በእጃችን መዳፍ ውስጥ የሚገኝ እና በየቀኑ በምናከናውናቸው ጥቃቅን ተግባራት ልንከውነው የምንችለው ስጦታ ነው” ብለው “ታላላቅ ተግባራትን በመፈጸም እና አለማቀፋዊ የሆኑ ስምምነቶችን በመፈጸም ብቻ የሚገኝ ነገር ሳይሆነ በየቀኑ በምናከናውናቸው ጥቃቅን ተግባራት ነው ሰላምን ልናረጋግጥ የምንችለው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በመቀጠል “ግሩም የሆኑ ቃላትን በመጠቀም ስለሰላም ልታወራ ትችላለህ፣ እንዲሁም ስላምን የተመለከተ ትልቅ ሊባል የሚችል ጉባሄ ልታደርግ ትችል ይሆናል፣ ነገር ግን ትንሽ በሆነችው ልብህ ውስጥ፣ በቤተስብህ ውስጥ፣ በአቅራቢያህ፣ በሥራ ቦታ  ሰላም ከሌለ በአለም ውስጥም ሰላም ሊኖረ አልችልም” ብለዋል።

“በእየ እለቱ በምናከናውናቸው ጥቃቅን ተግባራት አማካይነት በአድማስ ላይ የሚገኙትን የሰው ልጆችን ሁሉ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሰላምን ማስፈን እንድንችል ጥበቡን እንዲሰጠን” እግዚአብሔርን መለመን ይገባናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በተለይም ደግሞ” አሉ ቅዱስነታቸው “በተለይም ደግሞ እኛ እየኖርንበት በምንገኘው የአሁኑ ዘምን በጦርነት ውስጥ እየኖርን እና ሁሉም ለሰላም ጥሪ” በምያደርጉበት በአሁኑ ወቅት እራሳችንን መጠየቅ የሚገባን ጥያቄ “ልብህ ዛሬ እንዴት ነው? ሰላም አለው ወይ? ሰላም ከሌለው ደግሞ በቅድሚያ ስለ ሰላም ከመናገርህ በፊት ልብህ ሰላም እንዲጎናጸፍ እንዴት አስችለዋለው? ቤተሰቦችህ ዛሬ እንዴት ናቸው? ሰላም አላቸው ወይ? ቤተሰቦችህን፣ ካህናቶችህን፣ ማህበርህን በሰላም መምራት የማትችል ከሆነ . . . እንዴት ነው እርሱ ስለ አለም ሰላም ማውራት የሚቻለው?” ብለን መጠየቅ ይኖርብናል ካሉ ቡኋላ  “የእኔ ልብ ዛሬ እንዴት ነው? ሰላም አለው ወይ? የእያንዳንዳችን ቤተሰቦች እንዴት ናቸው? ሰላም አላቸው ወይ? የሚሉትን ጥያቄዎች ዛሬ ለእናንተ ማንሳት እፈልጋለሁ እነዚህን ጥያቄዎች ካልመለስን በአለም ውስጥ ሰላምን ማምጣት አንችልም” ካሉ ቡኋላ የእለቱን ስብከተ ወንጌል አጠናቀዋል።

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.