2016-09-05 14:45:00

ቅዱስነታቸው በመስከረም 1-2016 ባስተላለፉት መልዕክታቸው ዓለም ለተፈጥሮ ጥበቃ ያደረግ ዘንድ የተምጽኖ ጥሪ አደረጉ ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቆጣጠር በመስከረም 1-2016 የተከበረውን ዓለም ለተፈጥሮ ጥበቃ ያደረግ ዘንድ በማሰብ በተካሄደው ዓለማቀፋዊ የጸሎት ቀንን ምክንያት በማድረግ በተለይም ደግሞ በያዝነው ልዩ የምሕረት ዓመትን እና እርሳቸው እራሳቸው ከ15 ወር በፊት አከባቢ በጻፉት “ላውዳቱ ሲ” የተሰኘውን ሐዋሪያዊ መልዕክታቸው ላይ ተመርኩዘው ያስተላለፉት መልዕክታቸው ዋናው ጭብጥ ሐሳብ “ለጋር መኖሪያ ቤታችን ራሩላት” የሚለው እንደ ነበረ ተገለጸ።

በመቀጠል ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ለተፈጥሮ እንክብካቤ ይደረግ ዘንድ ለማሳሰብ የተካሄደው ዓለማቀፍ የጸሎት ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉትን መልዕክት ጠቅለል ባለ መልኩ እንደ ሚከተለው እናቀረበዋለን።

መስከረም 1-2016.

ለጋራ መኖሪያ ቤታችን እንራራላት

ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ጋር በጋር በመሆን፣ እንዲሁም ከሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት እና የክርስቲያን ማሕበረሰቦች አጋርነት የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ “ለተፈጥሮ እንክብካቤ ይደረግ ዘንድ ዓለማቀፍ የጸሎት ቀን ታከብራለች”። በእዚህ እለት “አማኝ ግለሰቦች እና የማኅበረሰብ ክፍሎች እያንዳንዳቸው ተፈጥሮን የመንከባከብ ጥሪያቸውን በድጋሚ የሚያድሱበትን አጋጣሚ በመጠቀም፣ የእዚህን ድንቅ የሆነ ተፈጥሮ ፈጣሪና እንድንከባከበው በአደራ ያስረከበንን እግዚኣብሔርን እንድናመሰግነው እና በቀጣይነትም ይህንን ተፈጥሮ ለመንከባከብ እንድንችል ይረዳን ዘንድ፣ በተጨማሪም በምንኖርባት ዓለም ላይ ላደረስነው ውድመት ይቅርታን እንድንለምነው” ይህ ቀን አጋጣሚን ፈጥሮልናል።

አብያት ክርስቲያናት እና የክርስቲያን ማኅበረሰብ እንዲሁም የሌላ እምነት ተከታዮች ለገጸ-ምድራችን የወደ ፊት እጣ ፋንታ መጠበብ መጀመራቸው አበረታች ነገር ነው። በእርግ ባለፉት አስርተ-ዓመታት የሐይማኖት መሪዎች እና ልዩ ልዩ ተቋማት በምድራችን ላይ እየተከሰት የሚገኘውን ኋላፊነት የጎደለው ብዝበዛ ለብዙኋኑ አጋልጠው እንደ ነበረ ይታወሳል። በእዚህም ረገድ የቁስጥንጥንያው ፓትሪያርክ በርተሌሜዎስ ከእርሳቸው ቀደም ብለው የነበሩትን የፓትሪያርክ ዲሚትሪን ፈለግ በመከተል በተፈጥሮ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ሐሳሳቢ ውድመት ኋጥያት መሆኑን እና ይህም በአከባቢ ላይ እየደረሰ የሚገኘው ውድመት ሞራላዊ እና መንፈሳዊ ሥር መሰረቶችን እንደ ምያቃውስ መገለጻቸው ይታወቃል። ከተፈጥሮ ጋር ያለን ውህደት እዲጨምር እንዲሁም የአደጋው አሳሳቢነትን ለማጉላት በማሰብ በሮማኒያ በሲቢው ከተማ 2007 የተካሄደው ሦስተኛው የአውሮፓ አብያተ-ክራስቲያንት የውይይት ጉባሄ ከመስከረም 1 ጀምሮ ባሉ አምስት ሳምንታት ውስጥ እንዲከበረ በመወሰኑ በተለይም ደግሞ በመስከረም 1 የኦርቶዶክስ አብያተ-ክርስቲያናት አምላክ የፈጠራቸውን ፍጥረታትን የሚያስቡበት ቀን በመሆኑ እና በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እንደ ጎርጎሮሳዊያን የቀን አቅጣጠር በጥቅምት 4 የሚከበረው የቅዱስ ፍራንቸስኮ በዓልን ምክንያት በምድረግ ነው።  ይህ ሦስተኛው የአውሮፓ አብያተ-ክራስቲያንት የውይይት ጉባሄ በቀጥይነትም በተፈጥሮ እንክብካቤ ዙሪያ ብዙ ሐሳቦች እንዲነሱ ምክንያት ሆኖኋል። በእዚህም ሳቢያ በዓለማችን በእዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የተለያዩ ሥራዎች እንዲከናወኑ መንስሄ ከመሆኑም ባሻገር ፍታዊ የሆነ የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም እዲኖር፣ ለድሆች ትኩረት እንዲሰጥ፣ ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍል ኋላፊነት ተሰምቶት በተለይም ደግሞ የተለያዩ ሐይማኖት ተከታይ የሆነው የወጣቱ ትወልድ በአንድነት በእዚህ ጉዳይ ላይ እንዲረባረብ ያነሳሳ ነው። ክርስቲያኖች ይሁኑ ክርስቲያን ያልሆኑ በጎ ፈቃድ ያላቸው ሰዎችም ጭምር የጋራ መጠልያ ቤታችን ለሆነችው ምድራችን ርኅራኄን እንዲያሳዩ እና የጋራ መኖሪ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን መንከባከም ይኖርብናል።

  1. ምድራችን  በልቅሶ ላይ ናት

በእዚህ መልዕክቴ ቀደም ሲል ያደረኩትን ንግግር በድጋሜ በማስታወስ “በእዚህ ምድር ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በመክራ ውስጥ የሚገኙ ድሆችን እና በአከባቢ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን በድጋሜ ማስታወስ እፈልጋለሁኝ”። እግዚኣብሔር የተትረፈረፈ የአትክልት ሥፍራን ሰጠን ነገር ግን እኛ ወደ ባድማነት እና የትርኪሚርኪ መጣያ፣ ወደ ተበከለ የቆሻሻ መጣያ ሥፍራነት ቀየርናት”። በምድራችን ስነ-ምዕዳር እና የተመጋጋቢነት ሂደት ላይ ኋላፊነት በጎደለው መልኩ እና በእራስ ወዳድነት መንፈስ እየደረሰ የሚገኘውን ውድመት በግድየለሽነት ስሜት ወይም በዝምታ መመልከት አይኖርብንም። “ምክንያቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ዝርያዎች እየጠፉ በሚመጡበት ወቅት በመኖራቸው ምክንያት እነርሱን በማየት ለፈጣሪ የምንሰጠው ምስጋና እየቀነሰ ስለ ሚመጣ እና ይህንን የማድረግ መብትም ስለሌለን ጭምር ነው።

የሰው ልጆች በምያደርጉ እንቅስቃሴ ምክንያት የአለም ሙቀት መጨመሩ ይቀጥላል፣ ባሳለፍነው 2015 የነበረው የዓለማችን ሙቀት እስካሁን ከተመዘገቡት ሁሉ በጣም የላቀ ሲሆን በ2016ም  ይህ ነገር በቀጣይነት እንደ ሚከሰት እሙን ነው። ይህም ጉዳይ በዓለማችን ድርቅ፣ ጎርፍ፣ እሳት እና ያልተለመደ የአየር ንብረት ለውጥ እዲኖር እያደረገ ይገኛል። የአለም የአየር ንብረት ለውጥ ለስደተኞች ፍሰት ቀውስ ከፍተኛ የሆነ ድርሻ አበርክቱኋል። በዓለም ውስጥ የሚኖሩ ድሆች ኋላፊነት በማይሰማቸው ሰዎች አማካይነት ድህነት ከደቀንባቸው መከራ ባሻገር በአለም የአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ከድጥ ወደ ማጡ እየወረዱ ይገኛሉ።

 የተመጣጠን የስነ-ምዕዳር ሂደት እንደ ምያሳየው የሰው ልጆ ከተፈጥሮ ጋር ጥብቅ የሆነ ግንኙነት እንዳለው ነው። ስለእዚህም ተፈጥሮን መበደል ማለት የሰው ልጆችን መበደል ማለት ነው። በተመሳሳይ መልኩ እያንዳንዱ ፍጥረት የራሱ የሆነ ተፈጥሮኋዊ እሴቶች አሉት ይህም ሊከበር ይገባዋል። “ምድራችን እና ድሆች እያሰሙ የሚገኙትን ለቅሶ ችላ አንበል” ተገቢ እና ወቅታዊ ምላሽ እንዲገኝ የተቻለንን ሁሉ ማድረግ ይኖርብናል።

2. . . .እኛ ኋጥያትን ስለ ሠራን

እግዚአብሔር ለእኛ ምድርን የሰጠን ተመጣጣኝ በሆነ መልኩ “እንድናለማት እና እንድንከባከባት ነው” ዘፍ 2,15። ከመጠን በላይ መጠቀም እና በጣም አንሰተኛ በሚባል መልኩ መንከባከብ ኋጥያት ነው።

ወንድሜ ፓትሪያርክ በርቴሌመዎስ ብርታት በተሞላው መልኩ በተፈጥሮ ላይ እየፈጸምነው የምንገኘውን ኋጥያት ተንብየው ነበር።  አሁን በጋራ የመኖሪያ ቤታችን ላይ እየተከሰተ ካለው እውነታ በመነሳት እና ይህንን ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመትን ምክንያት በማድረግ በተለይም ደግሞ በምስጢረ ንስኋ አማካይነት “ውስጣዊ የሆነ ለውጥ ማምጣት ይኖርባናል። በእዚህ ልዩ የምሕረት ዓመት በተፈጥሮ ላይ ያደረስነውን ጥፋት ተገንዝበን ይቅርታን የምንጠይቅበት ሊሆን ይገባል። እንዲሁም ይህንን ሁኔታ ለመለወጥ ተጨባጭ እርምጃዎችን መውሰድ እንድያስችልን እስቲ ራሳችንን እንመልከት ምክንያቱም ለስነ-ምዕዳር የምናደርገው አስተዋጾን በግልጽ በማወቅ  ለራሳችን፣ ለጎረቤቶቻችን፣ ለተፈጥሮ እና ለፈጣሪ ማሳየት የሚገባንን ኋላፊነት ማወቅ ያስፈልጋል።

3. ሕሊናችንን መመርመር እና መጸጸት

ለእዚህ ችግር ቀዳሚ የሆነ መፍትሄን ለማምጣት እንዲያስችለን በቅድሚያ “ማመስገን እንድንችል፣ ዓለማችን የእግዚአብሔር ስጦታ መሆኑዋን መረዳት እንድንችል እንዲሁም በጽሞና የእርሱን መልካምነትን በመላበስ በመልካም ሥራችን እራሳችንን መስዋዕት ማድረግ እንድንችል፣ በቅድሚያ እራስን መመርመር ያስፈልጋል። ጠንከር ያለ የሕሊና ምርመራ ካደረግን ቡኋላ በፈጣሪ፣ በፍጥረት፣ እንዲሁም በወንድም እና ሕህቶቻችን ላይ ባደረስነው ጥፋት ተጸጽተን ንስኋ መግባት ያስፈልጋል። “ንስኋን አስመልክቶ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ  እንዳስቀመጠው እውነት ነጻ ያወጣችኋል” “እግዚአብሔር ከኋጥያታችን በላይ ነው” ስለሆነም በተፈጥሮ ላይ ላደረስነው በደል ይቅር ይለናል”።

4. አካሄዳችንን ማስተካከል

ሕሊናን መመርመር፣መጸጸት እንዲሁም ኋጥያታችን በምሕረት ለተሞላው እግዚአብሔር መናዘዝ ወደ አንድ መሻሻልን ማምጣት ወደ ምያስችለን አንድ ዓላም ይመራናል። ይህም ዓላማ ተፈጥሮን ማክበር ወደ ምያስችለን ተጨባጭ ሐሳብ እና ተግባር ሊተረጎም ይገባል። ለምሳሌም “ፕላሲቲክ ነክ የሆኑ ነገሮችን መጠቀም አቁመን በምትኩም ወረቀት ነክ ነገሮችን መጠቀም፣ የውሃ አጠቃቀማችንን በቁጠባ ማድረግ፣ ህይወት ያላቸው ፍጥረቶች ሁሉ እንክብካቤ ማሳየት፣ በካይነት የሌላቸውን የመጓጓዣ አገልግሎቶችን መጠቀም፣ ዛፎችን መትከል. . . ወዘተ የመሳሰሉትን ተግባራት መፈጸም ያስፈጋል።

5. አዲስ የምሕረት ተግባር

“የምሕረትን ተግባር ከማከናወን በተሻለ ሁኔታ ከእግዚአብሔር ጋር የምያዋህደን የተሻለ ነገር የለም፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ኋጥያታችንን ይቅር የሚለን እና ፀጋውን የሚሰጠን እኛም ይህንን የምሕረት ተግባር በስሙ ማከናወን እንድንችል ነው”።

የክርስቲያን ሕይወት ባህል ሰባት አካላዊ እና መንፈሳዊ የምሕረት ተግባራትን መፈጸም እንዳለብን ያስተምረናል። “ብዙን ጊዜ የምሕረት ተግባራት ከግለሰቦች ጋር በተያያዘ ሁኔታ የሚፈጸሙ ለምሳሌ ለታመሙት ሆስፒታል፣ ለተራቡት ምግብ ቤት፣ ቤት ለሌላቸው መኖሪያ ቤት፣ ለተማሪዎች ትምህርት ቤት. . . ወዘተ ብቻ መስሎን ሊታይን ይችላል። ነገር ግን የምሕረት ተግባራትን በጥቅሉ ብንመለከት የምሕረት ተግባራት ዋናው ትኩረት የሰው ነፍስ እና ሰውን ያማከሉ ነገሮች ብቻ እንደ ሆኑ ያመለክታል።

ያለምንም ጥርጥር “የሰው ልጅ ሕይወት እና ይህንንም ያማከሉ ነገሮች ሁሉ” የጋራ መኖሪያችን የሆነውን ቤታችን እንድንከባከብ አደራ ይሉናል ማለት ነው። ስለ የጋራ መኖሪያ ቤታችን መንከባከብ የእዚህ የምሕረት ተግባራ አንደኛው አካል ነው።

6. በመጨረሻም እንጸልይ

ምንም እንኳን ኋጥያተኞች ብንሆንም እና በብዙ መከራዎች ውስጥ እያለፍን ቢሆንም ቅሉ ተስፋ መቁረጥ አይገባንም ምክንያቱም ፈጣሪያችን መቼም ቢሆን ብቻችንን አይተወንም እና ነው። መቼም ቢሆን ፈጣሪያችን መሆኑን አያቆምም ምክንያቱም እርሱ ከምድራችን ጋር የተዋኋደ እና የእርሱ ፍቅር ሁል ጊዜም ቢሆን ወደ ፊት እንድንጓዝ የሚደግፈን በመሆኑ ጭምር ነው።

እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባናል. . . “የድሆች አምላክ የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ የተረሳችሁን እና የተጣለችሁን በእንተ ፊት ግን በጣም ውድ የሆነችውን ምድራችንን መታደግ እንድንችል እርዳን። የፍቅር አምላክ ሆይ በእዚህ ምድር ላይ ለሚገኙ ፍጥረቶች ሁሉ ያንተን ፍቅርን ማሳየት የምንችልበትን ቦታ እና ምንገዱን አሳየን። የምሕረት አምላክ ሆይ ያንተን ምሕረት የተጎናጸፍነውን ምሕረርት የጋራ የመኖሪያ ቤታችን በሆነችው ምድራችን ውስጥ መተግበር እንድንችል እርዳን። የእግዚአብሔር ሥም የተመሰገን ይሆን።

                                          አሜን”!!    

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.