2016-08-23 12:13:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "የሰው ሕይወት ከፍ ያለ ወጋ ያለው በጣም አስፈላጊ ነገር ነው" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በነሐሴ 15-2008 ባሰሙት ስብከት “ሕይወት የቪዲዮ ጨዋታ ወይም እንደ አንድ ተከታታይ ፊልም የሆነ ነገር ሳይሆን፣ የእኛ ሕይወት ከፍ ያለ ወጋ ያለው በጣም አስፈላጊ ነገር በመሆኑ የሕይወታችን ግብ የሆነውን የዘላለም ሕይወትን ለማግኘት መጣር አስፈላጊ ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

 

በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ ሳምንታዊ አስተምህሮ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት ቃለ ወንጌል ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በእለቱ ማለትም እንደ የጎርጎሮሳዊያን የሥርዓተ-ሉጥርጊያ አቆጣጠር መሰረት ከሉቃስ ወንጌል ከምዕራፍ 13፣22-30 በተነበበው የወንጌል ቃል ላይ በመመርኮዝ አንድ ሰው ኢየሱስን “አቤቱ የሚድኑ ጥቂቶች ሰዎች ናቸውን?” የሚለውን ጥያቄ በማውሳት “የሚድኑ ስንት ሰዎች መሆናቸውን ማወቅ ብዙ የምያሳስብ ነገር አይደለም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በጣም አስፈላጊ ነገር ሊሆን የሚገባው ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን መንገድ ማወቅ ነው” ብለዋል።

ወደ ዘላለም ሕይወት የምያስገባው በር መሰረቱን ያደረገው በክርስቶስ ላይ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንን በር ማለፍ የሚቻለው ትዕቢትን፣ ጅንንነትን እና እንዲሁም ኋጥያትን በማስወገድ በምትኩ ፍቅርን ለሁሉም በመለገስ በእግዚአብሔር ምሕረት ስንታቀፍ ብቻ መሆኑን አበክረው ገልጸዋል።

“ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ የዛሬው ወንጌል የዘላለም ሕይወት  ጭብጥ ላይ ያተኮረ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም በሚሄድበት ወቅት “አቤቱ የሚድኑ ጥቂቶች ሰዎች ናቸውን?” ብሎ መጠየቁን በድጋሚ በማውሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ለቀረበለት ጥያቄ በቀጥታ መልስ አልሰጠም ነበር ብለው ኢየሱስም መዳን የሚፈልጉ ሰዎች “በጠባቡዋ በር ለመግባት ተጣጣሩ፣ በዚህች በር ለመግባት የሚፈልጉ ብዙዎች ናቸው፣ ነገር ግን መግባት አይችሉም እላችኋለሁ” ብሎ መመለሱን ጠቅሰው ኢየሱስ የበርን ምሳሌ ተጠቅሞ ለአድማጮቹ መግለጽ የፈለገው፣ በጣም አስፈላጊው ነገር በዚህች ጠባብ በር ስንት ሰዎች እንደ ሚገቡ ማወቅ ሳይሆን፣ በጣም አስፈላጊው ነገር ስንት ስዎች እንደ ሚድኑ ማወቅ መሆኑን ለማስገንዘብ ፈልጎ መሆኑን ገልጸው አስፈላጊው ነገር የቁጥሩን ብዛት ማወቁ ሳይሆን ሁሉም ሰው ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደው በር የተኛው መሆኑን ለይቶ ማወቁ ነው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸው በመቀጠል እንዳሳሰቡት በትክክለኛው የሕይወት መንገድ ላይ ለመራመድ በቅድምያ በጠባቡዋ በር ማለፍ ያስፈልጋል ብለው “ይህችህ ጠባብ በር ምን ትመስላለች? በሩስ ማነው?” በማለት ጥያቄ ሊነሳ እንደ ምችል ጠቁመው በዩሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 10,9 ላይ እንደ ተጠቀሰው ኢየሱስ እራሱ “በሩ እኔ ነኝ” ብሎ በመናገሩ ጠባቡ በር ኢየሱስ እራሱ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ኅብረት ይኖረን ዘንድ እና በፍቅሩ እና በከለላው እንድንታቀፍ ይመራናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህ በር ለምን ጠባብ ሆነ?” ብለን መጠየቅ በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው በሩ ጠባብ የሆነበት ምክንያት ብዙ ሰዎች እንዳያልፉበት ተፈልጎ ሳይሆን ቅሉ፣ ፍርሃታችንን እና ኩራትን በማስወገድ በምትኩም ትህትናን በመላበስ እና ልባችን በእርሱ እንዲታመን በማድረግ ኋጥያተኞች መሆናችንን እንድንገነዘብ የእርሱን ምሕረት ለማግኘት እንድንጓጓ በመፈለጉ መሆኑን ገልጸዋል።

ወደ ዘላለም ሕይወት የምያስገባው በር የጠበበበት ምክንያት “ያበጠው ትዕቢታችን እንዲፈነዳ ለማድረግ በማሰብ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚአብሔር የምህረት በር ሁሌም ጠባብ የሆነ እና ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን ወለል ብሎ ለሁሉም የተከፈተ መሆኑን ገልጸው እግዚአብሔር ለማንም ሳያዳላ ሁሉንም ያለምንም ልዩነት ለመቀበል ዝግጁ እንደ ሆነ ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በመቀጠል እንዳሳሰቡት “እግዚአብሔር የሚሰጠን የዘላለም ሕይወት የሚመነጨው ማንኛውንም እንቅፋት በማስወገድ፣ ከፍ አድርጎን ብርሃኑን እና ሰላሙን ከሚሰጠን ከማያልቀው የምሕረት ፀጋው እንደ ሚመነጭ አውስተው መርሳት የሌለባችሁ ነገር ብኖር ወደ ሕይወት የሚወስደው በር ጠባብ ነገር ግን ሁሌም ክፍት መሆን ማወቅ እንዳለብን ጨምረው ገልጸዋል።

ኢየሱስ ዛሬም ቢሆን የሕይወት ጋሬጣዎችን አስወግደን እርቅን በማስፈን ደስተኛ የሆን ሙሉ ሕይወት እንድንኖር ይጋብዘናል በማለት በስብከታቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው ምንም ዓይነት ኋጥያት ብንሠራም እንኳን ሁል ጊዜ በንስሓ ወደ እርሱ እንድንመለስ እና በእርሱ ምሕረት እንድንታቀፍ እንደ ሚጠባበቀን ገልጸው ሙላኋት ያለው ሕይወት የሚገኘው በእርሱ ብቻ መሆኑን ተገንዝበን የሰማይ በር የሆነችው እመቤታችን ማሪያም በአማላጅነቱዋ ወደ ንስሓ በመመለስ የእርሱ መንግሥት ተካፋዮች እንድንሆን ትረዳን ዘንድ መማጸን እንደ ሚገባ አሳስበው የሰማይ ንግሥት ሆይ የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ደግመው እና ቡራኬን መለገሳቸው ታውቁዋል።

ይህ በእዚህ እንዳለ በነሐሴ 14-2008 በቱርክ በአንድ አጥፍቶ ጠፊ በሰርግ ስነ-ስርዓት ላይ በተፈጸመው እና ብዙኋኑ 18 ዓመት በታች የሆኑትን የ54 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የሽብር ጥቃት እጅግ ማዘናቸውን ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በእለቱ ዝግጅታ ማጠቃለያ ላይ መግለጻቸው የታወቀ ሲሆን “በደጋው ሕይወታቸውን ላጡ እና ለተጎዱ ሰዎች መጸለይ እንደ ሚገባ ገልጸው ሰላም ይሰፍን ጸንድ መጸለይ እንደ ሚገባ ማሳሰባቸው ጨምሮ ተገልጽኋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.