2016-08-18 11:25:00

በኋያላን እና በጉልበተኞች አስገዳጅነት ሰባዊ ላልሆን አስገዳጅ ሥራ የተጋለጡ ሴቶች ብዙ መሆናቸውን ቅዱስነታቸው አስታወቁ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ እንደ አውሮፓዊያን የስርዓተ ሉጢርጊያ አቆጣጠር በኔሐሴ 9-2008 የተከበረውን እመቤታች ቅድስት ድንግል ማሪያም ወደ ሰማይ በነፍስና በሥጋ ያርገችበትን ዕለት በሚዘከርበት የፍልሰታ ዓመታዊ በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ ይህንን ታላቅ ዓመታዊ በዓል ለመታደም  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን፣ “እንኳን አደረሳችሁ” በማለት ንግግራቸውን የጀምሩት ቅዱስነታቸው የማሪያም ዕርገት የሁላችንንም የወደ ፊት እጣ ፋንታ የሚጠቁም ታላቅ ሚስጢር መሆኑን ባስተላለፍነው የዜና እወጃችን እንደ ገለጽን የሚታውስ ስሆን የማሪያምን የእርገት በዓል አስመልክተው ካሰሙት ቃለ እግዚአብሔርጋ በማያያዝ በአሁኑ ጊዜ በዓለማችን የሚታየውን እና እርሳቸው “በጣም አስከፊ ዘመናዊ ባርነት” ብለው የጉዳዩን አሳስቢነት በአጽኖት የገለጹትን በከፍተኛ የሕይወት ጫና ውስጥ እና በስቃይ ውስጥ የሚገኙትን ሴቶች እህቶቻችንን ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው እንደ ነበር ይታወሳል።

ቅዱስነታቸ በስብከታቸው በኋያላን እና በጉልበተኞች አስገዳጅነት ሰባዊ ላልሆን አስገዳጅ ሥራ የተጋለጡ ሴቶች ብዙ እንደ ሆኑ፣ አካላቸው እና መንፈሳቸው በግዳጅ በወንዶች እንዲበዘበዝ እየተዳረገ መሆኑን አበክረው መግለጻቸውን ሰኞ እለት ባስተላለፍነው የዜና እወጃችን እንደ ዘገብን ይታወሳል።

ይህንን ስብከተ ወንጌል እና በሴቶች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ዘመናዊ ባርነት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ትኩረት ስጥተው በአጽኖት መግለጻቸውን በጣም እንዳስደሰታቸው “ካዛ ሩት” በሚባል የሚታወቀው ና በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴት ልጆችን የሚረዳ የመጠልያ ጣቢያ አላፊ የሆኑት ሲስተር ሪታ ጃሬታ በተለያየ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙትን ሴቶችን ለማሰብ በተዘጋጀው የጸሎት ስነ-ስርዓት ላይ መግለጻቸው ታወቀ።

ቅዱስነታቸው በስብከተ ወንጌላቸው የተናገርዋቸው ቃላት በጥልቀት ገብተው ልብን እና ሕይወትን የመንካት ጉልበት ነበራቸው ያሉት ሲስተር ሪታ ምክንያቱም በሴቶች ላይ እየተፈጸመ ይሚገኘውን ግፍ የሚረዳ አንድ እረኛ፣ አንድ አባት አንድ ጳጳስ መኖሩ እና አሁንም በእዚህ ችግር ውስጥ ለሚኖሩ ሴቶች አለኝታነትን የሚያሳይ መልዕክት በመሆኑ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት መልዕክት ጥንካራ እና አጋርነትን የሚያሳይ ነበር በማለት ምስክርነታቸውን የቀጠሉት ሲስተር ሪታ በተለይም ደግሞ ኋልፊነት የጎደላቸው ሰዎች ስግብግብነታቸው  አስወግደው ኋላፊነት የሚሰማቸው ሰዎች ይሆኑ ዘንድ ያቀረቡት ጥሪ  ለችግሩ አዲስ የግንኙነት መስመር የቀየሰ መሆኑን ያሳዩበት እንደ ነበር ገልጸዋል።

ይህ በካዜርታ ጠቅላይ ግዛት የሚገኘው ካዛ ዲ ሪታ የተሰኘው እና በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ተቀብሎ የሚያስተናግደው ማዕከል ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተለይም ከሳሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት የመጡ ሴት ስደተኞችን ተቀብሎ አስፈላጊውን እርዳታ እና እንክብካቤን የሚለግስ ማዕከል እንደ ሆነ አያይዘው የገለጹት የማዕከሉ ኋላፊ ሲስተር ሪታ በማዕከሉ የሚገኙ አንድ አንድ ሴቶች ለአቅመ ሔዋን እንኳን ያልደረሱ መሆናቸውን ገልጸው ከእነዚህም አብዛኞቹ ናይጄራዊያን መሆናቸውን አመልክተው በማዕከሉም አስፈላጊ እገዛ እየተደርገላቸው እና ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እንዲመለሱ የተቻለውን ያህል ጥረት እያደረጉ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.