2016-08-18 12:17:00

ቅዱስነታቸው "ምሕረት ሕብረትን የመፍጠሪያ አብይ መሳሪያ ነው" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በነሔሴ 11-2008 ለጠቅላላ አስተምህሮ በጳውሎስ 6ኛ አዳራሽ ለተሰበሰቡት ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ያስተላለፉት አስተምህሮ ምሕረት ሕብረትን የመፍጠሪያ አብይ መሳሪያ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢየሱስ 5000 ሰዎችን በአምስት እንጄራ እና በሁለት ዓሣ በታምር መመገቡን በምያወሳው እና ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 14, 13-21 ላይ በተወሰደው የመጸሐፍ ቅዱስ ቃል ላይ ተመርኩዘው አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ለሚከተሉት ሰዎች ያሳየው ርኋራኄ ስሜታዊ ሳይሆን “በጣም ስለሚወደን እና ሊቀርበን ስለሚፈልግ ያደረገው ታምር ነው” ማለታቸው ተገለጸ።

ኢየሱስ ለሚከተሉት ሰዎች ማሰቡ ይህንን ታምር እንዲፈጽም አነሳስቶታል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ይህንን ታምር ብቻውን መፈጸም ብችልም ቅሉ  “ያላቸውን ጥቂት እንጀራ እና ዓሣ እንዲያሳዩት ደቀ መዛሙርቱን መጠየቁ በዚህ ታምር ደቀ መዛሙርቱን ለማሳተፍ በመፈለጉ ስሆን በእምነት እና በፀሎት ኋይል ለሁሉም እንደ ሚበቃ ለማሳየት በመፈለጉም ጭምር መሆኑን ገልጸው “ማንኛውም ታምር ሊፈጸም የሚችለው በእምነት፣ በርኋራኄ እና በፍቅር በተደረገ ጸሎት መሆኑንም” አክለው ገልጸዋል።

ኢየሱስ ታምራቱን በፈጸመበት ወቅት አይኖቹን ወደ ሰማይ በማቅናት አመስግኖና ባርኮ እንጀራውን ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው ይህም ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር የመጨረሻ እራት በበላበት ወቅት ከፈጸመ ተግባር ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው በመግለጽ አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተመሳሳይም ይህ ተግባር በእየ እለቱ ካህናት መስዋዕተ-ቅዳሴ በምያቀርቡበት ወቅት በተመሳስይ መልኩ የሚተገበር እንደ ሆነም አክለው ገልጸዋል።

ይህም የሚያሳየው አሉ ቅዱስነታቸው ይህ የሚያሳየው የክርስቲያን ማሕበረሰብ በቅዱስ ቁርባን አማካይነት  በተደጋጋሚ እንደ ሚወለድ” ሁነኛ ማሳያ ነው ብለው ከክርስቶስ ጋር ያለን ሕብረት ለወንድሞቻችን እና ለእህቶቻችን ተጨባጭ በሆነ መልኩ የክርስቶስን ምህረትን በተግባር ለመፈጸም መውጣት እንዳለብን የምያሳስበን እና በእዚህ መልክ ብቻ ነው ምዕመናን የምህረት አገልግይ መሆናቸውን ማሳየት የሚችሉት በማለት አክለው ገልጸዋል።

በአስተምህሮዋቸው ማገባደጃ ላይ ቅዱስነታቸው ቤተ ክርስቲያን ለእዚህ ከተቀደሰ አገልግሎት ብቁ ትሆን ዘንድ ምዕመናን ወደ ጌታ እንዲጸልዩ ጋብዘው እያንድ አንዳችን ተጨባጭ የእግዚኣብሔር ምሕረት መገለጫ የሆነውን በግንኙነታችን ወቅት ሁሉ ሕብረት ፈጣሪዎች እንድንሆን ይረዳን ዘንድ መጸለይ እንደ ሚገባ በማሳሰብ አስተምህሮዋቸውን አጠናቀዋል። 

                                                                        








All the contents on this site are copyrighted ©.