2016-08-10 16:45:00

ተወላጅ የአገሬ ሕዝቦች ቀን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ ታስቦ የዋለው ተወላጅ የአገሬ ሕዝቦች ቀን ምክንያት ትዊተር በተሰየመው ማኅበራዊ ድረ ገጽ ባለው @Pontifex ኣት ፖንቲፈክስ አድራሻቸው አማካኝነት “ለአደጋ ተጋልጦ የሚገኘው ተወላጅ የአገሬ ህዝብ መለያና ህልውናቸውም ሳይቀር ከተጋለጠበት አደጋ ተላቆ በሚገባ እንዲከበርላቸው ስንል እንጠይቃለን” የሚል መልእክት አስተላልፈዋ። በተለይ ደግሞ በዚህ ዓለም አቀፍ የሪዮ 2016 ዓ.ም. የኦሎምፒክ ስፖርት እየተካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት የላቲን አመሪካ ቀደምት ተወላጅ አገሬዎች ሁኔታ ማእከል ሆኖ የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበና ዓለም አቀፍ የቀደምት ተወላጅ አገሬዎች ሰብአዊ መብትና ክብር ተሟጓች "Survival International" የተሰየመው ዓለም አቀፍ ማኅበር በብራዚል በቀደምት የአገሬ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ጅምላዊ ቅትለት ያብቃለት በሚል ርእስ ሥር ቀደምት የአገሬ ተወላጆች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ እንዲረጋገጥ የጥሪ ዘመቻ ማነቃቃቱ የዓለም አቀፍ የቀደምት ተወላጅ አገሬዎች ሰብአዊ መብትና ክብር ተሟጓች ማኅበር ቅርንጫፍ በኢጣሊያ ተጠሪ አሊቸ ፋራኖ ከቫቲካን ረዲዮጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቋል።

ይህ ዓለም አቀፍ ማኅበር በሪዮ የሚካሄደው የ 2016 ዓ.ም. የኦሎምፒክ ስፖርት ውድድር የቀደምት አገሬ ተወላጆች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ዓለም አቀፋዊ ግንዛቤ አግኝቶ ሁሉም ስለዚሁ ጉዳይ በየፊናው የተቻለውን ለማድረግ ጥሪ ለማቅረብ ጥሩ አጋጣሚ መሆኑ ግምት በመሰጠም ዘመቻውን አስጀምሯል። በቅድሚያ በብራዚል የጉራኒ መሬት ንጥቂያና በዚያ ክልል የሚገኙትን ቀደምት የአገሬ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ዓመጽ የጓራኒ ተወላጆች መሬታቸው እየተነጠቁ የጎዳና ተዳዳሪ ሆኖ ለመኖ አደጋ ተጋልጧል። ስለዚህ የብራዚል መንግሥት የዚህ ዓይነቱ በቀደምት ተወላጅ ዜጎች የሚሰነዘረው ዘርፈ ብዙ ጥቃት ለህልውናቸው አደጋ መሆኑ ተገንዝቦ ሰብአዊ መብታቸውና ክብራቸው ለማስጠበቅ እንዲቆም ጥሪ እየቀረበ ነው ብለዋል።

በብራዚል የአማዞን ክልል የሚገኙት የካዋሂቫ ጎሳ የሆኑት ቀደምት ተወላጆች በዓለም ለከፋ አደጋ ከተጋለጡት ቀደምት ተወላጆች በቅድሚያ የሚጠቀሱ መሆናቸው ከገለጡ በኋላ እነዚህ ጎሳዎች እየተገፉ መኖር ከጀመሩ ብዙ ዓመታት አስቆጥሯል። በደን ሃብት እጅግ ክቡር የሆነውን ክልላቸው ለእንጨት አምራች ኢንዳስትሪዎች መስህብ በመሆኑ እነዚህ ኢንዳስትሪዎች ጭካኔ በተሞላው አሠራር የክክሉን የደን ሃብት ምንጠራ ተግባራችው አለ ምንም ከልካይ ሕግ እያፋጠኑ ይገኛሉ። ይኸንን እውነታ ለአገሪቱ የሕግና ፍትህ ሚኒስትር በማቅረብ የደን ሃብት ምንጠራ የሚካሄድባቸው የክልሎች መልክኣ ምድር የተኖረበት ሰነድ በማቅረብ ይኽ ደግሞ በአገሪቱ መንግሥት ጸድቆ ገቢራዊ እንዲሆን የህዝብ ፊርማ የማሰባሰቡ ጥሪ መተላለፉ አስታውቀው ሆኖም ውሳኔው ሕግ ሆኖ እስካልጸደቀ ድረስ የካዋሂቫ ጎሶች ህልውና ለመከላለክ ያስቸግራል ብለዋል።

በመላ ዓለም በቀደምት የአገሬ ተወላጆች ላይ እድገትና ሥልጣኔ በሚል አነጋገር የዘረኝነት ጥቃት ጅምላዊ ቅትለት ሲፈጸም ይታያል እድገትና ስልጣኔ የሚባለው እቀድ ቀደምት የአገሬ ተወላጆች የሚደግፍ ሳይሆን የእንርሱ መሬት የሚያቀርበው የተፈጥሮ ሃብት ለመበዝበዝ ያለመ ተግባር ነው ካሉ በኋላ የእነዚህ ሕዝቦች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ የመላ ዓለም መንግሥታ ቀዳሚ መርሐ ግብር በማድረግ መንቀሳቀስ ይኖርባቸዋል ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.