2016-08-05 16:06:00

የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ዋና አስተዳዳሪ መግለጫ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአሲዚ ስላካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስመልከ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ዋና አስተዳዳሪ ግረግ ቡርከ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የቅዱስነታቸው የአሲዚው መንፈሳዊ ንግደት ምሕረት ላይ ያነጣጠረ የአጭር ሰዓት ሐዋርያዊ ዑደት ቢሆንም መልእክቱ እጅግ ጥልቅና ሰፊ ነበር። በተለይ ደግሞ ቅዱስነታቸው ከግል ጸሎትና ከለገሱት አስተንትኖ ውጭ በሚያደርጉት የመንፈሳዊ ዝክረ ነገር ውስጥ ያልተካተተ ወደ ማናዘዣው ስፍራ በመሄድ ለአንድ ሰዓት የሚሆን እዛው ተቀምጠው አንዲት አካለ ጉዳተኛ በእድሜ የገፉት እናት፡ እንድ ካህን ሁለት የቃኝ ወጣቶች ማሕበር አባላት የሚገኙባቸው በጠላላ 19 ሰዎችን አናዘዋል። የሐርያዊ ጉብኝቱ ማእከልም እርሱ ነው፡ ካህናት ጳጳሳት በማናዘዣ ሥፍራ እንዲገኙና የእግዚአብሔር ምሕረት መስካሪያን እንዲሆኑ አደራ የሚል ነው፡ የአብ ምሕረት ማስፋፋት።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እዛው ከተገኙት የፐሩጃ የምስልምና ሃማኖት ተከታዮች መንፈሳዊ መሪ ኢማም ጋር ሰላምታን ተለዋውጠው አጭር የሐሳብ ልውውጥም አድርገዋል። ይኽ ግኑኝነትም የአሲዚ መንፈስ የሚያንጸባርቀው እርሱም ግኑኝነትና ውይይት የሚልም እሴት የሚያጎላ ነው።

ቅዱስ አባታችን ቃለ ወንጌልና የቅዱስ ፍራንቸስኮ የቅድስና ታሪክ መሠረት በማድረግ የምሕረት ትርጉሙ በጥልቀት በሰጡት አስተንትኖ ገልጠዉታ። ምሕረት በሰዎች መካከል ምሕረት በሕዝቦች መካከል ምሕረት በአገሮች መካከል ስለዚህ ምሕረት የመልክዓ ምድር ሥነ ፖሊቲካዊ  የአቀማመጥ መንግሥታት ጭምር የሚል ነው።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሚገልጡት ምሕረት ኵላዊነት ባህርይ ያለው ነው፡ ለዓለም ሁሉ አለ ምንም የሃይማኖት የባህል የቋንቋ እንዲሁም ፖለቲካዊ ርእየት ልዩነት የሚመለከት ሲሆን የዓለማዊነት ትስስር ገጽታ ያለው ነው። በዚህ በአሲዚ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ንግደት ምሕረት መሐሪነት ይቅር ባይነት ላይ በማተኰር ምሕረትና መሐሪነት የማይነጣጠሉ ተደጋግፈው በቁርኝት እንደሚሄዱ በቅድስተ ማሪያም ዘመላእክት ቤተ መቅደስና ከቤተ መቅደሱም ውጭ ደጋግመው ያሰመሩበት ሐሳብ ነው። እግዚአብሔር በቅድምያ ምሮናል ምሕረቱን ለግሶልናል፡ ይኸንን ለመኖር መጠራታችንም በስፋት ገልጠዉታል መማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.