2016-08-03 16:47:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሴቶች ለድቁና ማዕርግ ጉዳይ የሚያጠና ልዩ ድርገት አቋቋሙ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ከመላ ዓለም የውፉያን ደናግል ማኅበር ጠቅላይ አለቆች አገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አድራሽ ተቀብለው ከአለቆቹ ለቀረበላቸው መልስ በመስጠት አስተምህሮ በለገሱበት  ወቅት የሴቶች ለዱቁና ማዕርግ ጉዳይ የሚያጠራ ልዩ ድርገት ለማቋቋም ፍላጎት እንዳላቸው ገልጥዉት የነብረው ሃሳብ ይኸው የዓንቀጸ እምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ምኅበር

ዋና ጸሓፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ልዊስ ፍራንሲስኮ ላዳሪኣ ፈረር የድርገቱ ሊቀ መንበር አድርገው በመሾም ሌሎች 12 አነርሱም ጳጳሳዊ የቅዱስ መጽሓፍ ጉዳይ ተንከባካቢ ድርገት አባል ክብርት ኣናቴ ኑሪያ ካዱች በናገስ፡ በላ ሳፒየንዛ መንበረ ጥበብና በጳጳሳዊ ኣጎስቲኒያኑም መንበረ ጥበብ መምህር ፕሮፈሰር ፍራንቸስካ ኮኪኒ፡ የቲዮሎጊያ ሊቅ የሶፊያ መንበረ ጥበብ ሊቀ መንበር ዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ ድርገት አባል ክቡር አባ ፒየትሮ ኮዳ፡ የስነ ቤተ ክርስቲያን አበው አጎስቲኒያኑም ተቋም ሊቀ መንበር የሥነ አበው መምሀር ክብሩ አባ ሮበርት ዶዳሮ፡ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል ማድሪድ በሚገኘው ጳጳሳዊ ኮሚላስ መንበረ ጥበብ የሥነ ቤተ ክርስቲያን መምህር ክብሩ ኣባ ሳንቲያጎ ማድሪጋል ተራዛስ፡ የጳጳሳዊ አንቶኒያኑም መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪት ክብርት እናቴ ማርይ መሎን፡ በቦን ከተማ በሚገኘው መንበረ ጥበብ የቲዮሎጊያ መምህር የነበሩት የዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ ድርገት አባል ክብሩ ኣካርል ሃይንዝ መንከ፡ በጳጳሳዊ የሳሊዚያን መንበረ ጥበብ የሥነ ቤተ ክርስቲያን መምህር ክብሩ አባ ኢማብለ ሙሶኒ፡ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በብራሰልስ በቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ መምህር የዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ ድርገት አባል ክቡር አባ በርናርድ ፖቲየር፡ ቪየና በሚገኘው የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ የሥነ ቲዮሎጊያ መንፈሳዊነት መምህር የዓለም አቀፍ የቲዮሎጊያ ሊቅ ማሪያነ ሹልሰር፡ በጳጳሳዊ ግረጎሪያና መንበረ ጥበብ የሥነ መሰረተ ቲዮሎጊያ መምህር ፕሮፈሰር ሚከሊና ተናቸ እንዲሁም በኒው ዮርክ በሚገኘው ሆፍስትራ መንበረ ጥበብ መምህር ፕሮፈሰር ፍይሊስ ዛጎኖን በአባልነት የሚያቅፍ በማድረግ ቅዉማንዳደረጉት የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍም መግለጫ አስታወቀ።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.