2016-08-01 16:41:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ ከኢየሱስ ጋር አብራችሁ ዓለምን ለውጡ


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ል.ጳ. ፍራንቸስኮ ክራኮቪያ በሚገኘው በምህረት አደባባይ በፓላንድ ሰዓት አቀጣጠር ከጧቱ ስምንት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ እንደደረሱም ሁለት ሚሊዮን በላይ በሚገመቱት ወጣቶች አቀባበል ተደርጎላቸው እየተዘዋሩ ለሁሉምሩ ሰላምታን አቅርበው ልክ ዘጠኝ ሰዓት ከአርባ ወደ መንበረ ታቦት ደርሰው የክራኩፍ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ድዝዊች የእንኳን ደህና መጡ መልእክት አስደምጠው እንዳብቁ መስዋዕተ ቅዳሴ መርተ

      የዕለቱ ከነቢይ ሆሴዕ ምዕ. 6 ከቁጥር 1-6

       ከኤፈሶን ምዕ. 2 ከቁጥር 4-10

       ከሉቃስ ወንጌል ምዕ. 19 ከቁጥር 1-10

የተወሰዱት ምንባባት በማስደገፍ በለገሱት ስብከት፥

በእግዚአብሔር እመኑ ዓለም ትለውጣላችሁ። ኢየሱስ የእናንተ ደጋፊ ነው። በወደቃችሁበት ሥፍራ ተገኝቶ ያነሳችኋል። ምንም’ኳ መድከም ቢኖርም ያፈቅራችኋል። ፍቅር ይርቅ መባባልና ምሕረትም ነው፡

ኢየሱስ ከቀራጮች እለቃ ከሆነው ዘከዎስ ጋር ተገናኘ። በዚህ ግኑኝነት ላይ በማተኮርም ቅዱስ አባታችን፥ ዘኬዎስ አጭር በዚህ ምክንያትም በሕዝብ መሃከል የነበረውን ኢየሱስ ለማየት የተሳነው ነበር። እኛም ኢየሱስን ለማየት ብቃት የሌለን ሆነን ሊሰማን ይችል ይሆናል። እያንዳንዱ ገዛ እራሱ አሳንሶ የሚመለከት ሊሆን ይችላል። ይኽ ደግሞ ያለን መንፈሳዊነት መለያ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችን ማስተዋል ይኖርብናል። የእርሱ ልጆች መሆናችን የማንገነዘብና የእርሱ እይታ በእኛ ላይ የማንቀበል ከሆን የተከዙ ሆነን እንቀራለን።

እግዚአብሔር እንደ እኛነታችን ያፈቅረናል። ይኽ እግዚአብሔር በእኛ ላይ ያለው ፍቅር ያለን እንከን ሓጢኣትም ጨርሶ የሚሽረው አይሆንም። ወንጌል እንደሚያረጋግጥልንም ማናችንም ለእርሱ እሩቅ ወይንም ያልበቃን አይደለንም። ሁላችን አስፈላጊዎች ነን። ስለዚህ እግዚአብሔር እንዳንተነትህ ላይ ይታመናል። ያለህ ልብስ ሃብት ወዘተ ግድ የማይለው። አንተን ነው የሚያፈቅረው። በእርሱ ዓይን  እያንዳንዳችሁ ሊገመት የማይቻል አቢይ ክብር አለው።

ኢየሱስ የሚሻው ወደ ላቀው ታተኩሩ ዘንድ ነው፡ ስለዚህ ለትካዜ ምርኮኞች አትሁኑ

ወደ በለጠውና ከፍ ወዳለው ከማተኮር ይልቅ ታች ታች ወደ ሆነው ስናጎነብስ እርሱ ይደግፈናል። እርሱ ለማፍቅረችን ታማኝ ነው። እንዳውም እኛን ከማፍቀር የሚያግደው ምንም ነገር የለም። የእኛ የእናንተ ደጋፊ ነው። በእኛ ውስጥ ተዘግተን በትካዜ ተውጠን በደረሰብን ግፍና በደል ላይ በማተኮር ባለፈው ጊዜ ውስጥ ታጥረን ብንቀርም እርሱ በተስፋ ዘወትር ይጠባበቀናል። በተከዘ ሕይወት መማረክ ለመንፈሳዊ ብቃታ የተገባ አይደለም። ትካዜ ሁሉን የሚያደነዝዝ የሚበክል በርን እንዲዘጋ የሚያደርግ የሕይወት ሕያውነትን የሚቀናቀን ተህዋስ ነው። እግዚአብሔር ግን በማፍቀራችን ላይ የጸና ነው። ከወደቅንበት ዳግም እንደምንነሳ ያምናል። ጨልመንና አልቦ ሐሴት ለመሆናችን እጁን የማይሰጥ አምላክ ነው። ዳግም እንደምንነሳም ከእኛ በላይ እርሱ በእኛ ላይ የታመነ ነው።

እውነተኛ ሕይወት የሚሰጠው ኢየሱስ ነው፡ በማንኛው መንገድ ይጨበጭ ብቻ ለሚባለው የስኬታማነት ሱስኝነት እምቢ

ሌላው ዜከዎስ ሊወጣው የሚገባው መሰናክል የሚያሰልል ሐፍረት ነው። ሐፍረት የሚሸነፈው በፍቅር ብቻ ነው።  አንድ ሰው ፍቅር ሲይዘው ከዚህ በፊት አድርጎት አማያወቀውና የማድረጉ ብቃቱ አለኝ ብሎ የማይገምተው ነገር ይፈጽማል። በኢየሱስ ፊት ኢየሱስ ጋር ስትገናኝ እጅን አጥፎ በነበርክበት ተቀምጦ መቅረት የሚቻል አይደለም። ለዚህ ሕይወት ለሚሰጠው ጌታ በአንድ አጭር መልእክት ምላሽ ለመስጠት አይቻልም።

የወተደዳችሁ ወጣቶች፥ ሁሉመናችሁ በተለይ ደግሞ ደካማነታችሁ ድካማችሁ ሃጢኣታችሁ በንስሐ ይዛችሁለት ወደ እርሱ ለመቅረብ አፍትርፍ ሊያሳፍራችሁ አይገባም። በምህረቱና በሰላሙ ያስገርማችኋል። በለጋስነት ትመልሱለትና ትከተሉትም ዘንድ አትፍሩ። መንፈሳችሁ ይደንዝዝ ዘንድ እትፍቀዱ፥ እይታችሁ መልካም ወደ ሆነው መስዋዕትነትንም የሚጠይቅ ቢሆንም ፍቅር ላይ አኑሩ። በመልካምም ይሁን በክፉ ስኬታማነት ብቻ ለሚለው አደንዛዥ እጸዋት እምቢ በሉ፡ ከዚህ ሱስ ተቆጠቡ።

ጥላቻን እምቢ ለሚለው አዲስ ሰብአዊነት ላይ እምነት ይኑራችሁ ባላችሁበት አትራመዱ

ዘኬዎስ የሚጋፈጠው ሦስተኛው እንቀፋት፥ የሚያጉረመርም ሕዝብ ነው። ሊያላግጡበትና እግዚአብሔር ከእርሱ ሩቅ እንደሆነ ሊያሳምኑት የሚሳለቁበት ስብስብ ሕዝብ። በእግዚአብሔር አስተዋይና ትሁት በሆነው የምሕረቱ ኃይል ላይ እምነቱ ይኑራችሁ፡ ሌሎች ስለእናንተ የሚያጉረመሩመት ነገር ሊያስፈራችሁ አይገባም፡ አትፍሩ።

ምሕረት የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው ምሕረትን ያገኛሉና፡ በሕዝቦች መካከል ጥላቻን እምቢ የምትሉ በአገሮች የድንበር ወሰን የማትምለክቱ አለ ምንም የበላይነት የበታችነትን የጥላቻ መንፈስ የግል ባህላችሁና መለያችሁን የምታቅቡ በአዲስ እና በታደሰ ሰብአዊነት እምታምኑ በመሆናችሁ አላሚያን በማለት በመሳለቅ ለሚያቀርቡባችሁ ቅድመ ፍርዲ አትፍሩ። ፈገግታ በተላበሰና እጆቹን በሚዘረጋ ሕይወታችሁ እትፍሩ። እናንተ የተስፋ አብሳሪያን በመሆናችሁ ለብቸኛው ሰብአዊ ቤተሰብ ቡራኬ ናችሁ።

የኢየሱስ እይታ በእኛ ላይ ከማንኛው ዓይነት እንከንና ሐጢኣት እጅግ የላቀ ነው። ሰውን እንጂ ሐጢአትንንና እንከንን አይመለከትም። ከዚህ በፊት በተፈጸመው ሐጢኣት አይገታም የበለጠ መጻኢ ላይ ትኩረቱን የሚያኖር ነው። በዝግነት ፊት እጁን ሳይሰጥ የአሃድነት የሱታፌ መንገድን ይሻል፡ ውጫዊው ሳይሆን ልብን የሚመለከት ጌታ ነው፡ ስለዚህ ንጹሕ ልብ አቅቦ ለመገኘት ቅንነትና ፍትሕ እንዲነግስ ከመታገል አትቦዝኑ አደራ።

በውጫዊነት አትማረኩ ብልጭ ብሎ በሚጠፋው ላይ እትቅሩ፡ ያውጫዊነት ላይ የሚያነጣጥረው የዓለማዊነት ሊጡርጊያ ተጋገጡት፡ ውጫዊነት ላይ ባተኰረው እውነተኛ ውበት ተምሳይ መንፈስ በሆነው ላይ አትጣበቁ። ካለ መታከት መልካም ለማየትና ለማስተላለፍ በሚችለው ልብ ላይ የተረጋገጠ ጥብቅ ግኑኝነት ይኑራችሁ። ያንን ከእግዚአብሔር በነጻ የተቀበላችሁት በነጻነት ለሌሎች አካፍሉት ምክንያቱን ይኸንን መልካምነት የሚጠብቁ ብዙ ናቸውና።

በእግዚአብሔር ላይ ታመኑ፡ በዚህ በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ያያችሁትን ወደ ቤታችሁ ይዛችሁ ተጓዙ

ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አሁን ነው የሚጀመረው ከዚህ ወደ ቤታችሁ ስትሄዱ ይዛችሁት የምትሄዱት ገጠመኝ ነው። ይኽ ደግሞ ኢየሱስ የሚሻው ጉዳይ ነው። ከሌሎች ጋር መገናኘት። ከሁሉም ከውይይትና ከግኑኝነት የላቀው እውነተኛው ግኑኝነት ጸሎት ነው። ቃሉን በእለታዊ ሕይወታችሁ ሊናገራችሁ ይፈልጋል። ወንጌል የእናንተ ያንተና የአንቺ ነው። የመንገዳችሁ የሕይወታችሁ ብሶል ወንጌል ነው፡

የእግዚአብሔር ተዘክሮ ላይ እምንት ይኑራችሁ። የእርሱ ተዘክሮ ያ የእያንዳንዳችን ውሂበ ዘገባ የሚታቀብበት ቤተ መዝገብ ሳይሆን የሚያስብ ርህሩህ ልብ የእያንዳንዳችን ክፋትና ሐጢኣይት ለመሻር ዝግጁ የሆነ ልብ ነው። ይኸንን ታማኝ የእግዚአብሔር ተዘክሮ ለመምሰል እንሞክር። ተዘክሮ ያንን የተቀበልነው መልካም ሁሉ የምናቅብበትና የማናካፍልበት ተጨባጭ ሂደት ነው።

እ.ኤ.አ. በ 2019 ዓ.ም. የሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መስዋዕተ ቅዳሴ አሳርገወ እንዳበቁ እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመምራታቸው ቀደም በማድረግ ባስደመጡት አስተንትኖ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ከሰማየ ሰማይ ሆነው ይኸ በትውል አገራቸው የተካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሐሴት እንደተከታተሉት እርግጠኛ ነኝ። የእግዚአብሔር አሳቢነት ዘወትር እፊታችን ሆኖ ይመራናል። ያ እ.ኤ.አ. በ 1985 ዓ.ም. በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግምዊ ትንቢት ያስጀመረው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በ 2019 ዓ.ም.  በአገረ ፓናማ እንዲካሄድ ወስነዋል። በማርያም አማላጅነት በቤተ ክርስቲያንን በዓለም የወጣቶች ጉዞ እንዲያበራና እንዲጠብቅ መንፈስ ቅዱስን እንለምነው ምክንያቱም የእግዚአብሔር ምህረት ሐዋርያትና ምስክርኖች ናችሁና ብለው ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ደግመው ሐዋርያያዊ ቡራኬ መስጠታቸው ጂሶቲ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.