2016-07-27 16:00:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመንፈሳዊ ፍርያማነት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ከመነሳታቸው አንድ ቀን ቀደም በማድረግ አት ፖንቲፈክስ በተሰየመው ማኅበራዊ መረብት ዘንድ ባለው የግል አድራሻቸው አማካኝነት “ውድ ወጣቶች ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በመንፈሳዊ ፍርያማነት እጅግ ሃብታም ይሆን ዘን በጸሎት አሃድነት ይኑረን፡ ነገ ያገናኘን” የሚል መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን። በዚህ እየተኖረ ባለው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ወቅት የሚከበረው 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የምኅረት መንፈስ የሚያንጸባርቅ መሆኑም ሲገለጥ። ይኽ 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለምታስተናግደው የፖላንድ ከተማ ክራኮቪያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ስታኒስላው ድዚዊች እ.ኤ.አ. ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መክፈቻ መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ያ ወደ ዓለም የምኅረት ነበልባል ማድረስ የሚል የዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ያስጀመሩት “ምሕረትን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፡ ምሕረትን ያገኛሉና” (ማቴ. 5,7) የሚል ቃለ ወንጌል መርህ ያደረገው የክራኮቪያው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መከፈቻ የቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የግል ጸሓፊ በመሆን ያገለገሉት በአሁኑ ወቅት የክራኮቪያ ሊቀ ጳጳሳት በመሆን እያገለገሉ ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ድዝዊች መሥዋዕተ ቅዳሴ ከማሳረጋቸው ቀደም ተብሎ የምሕረት ችቦ ያስቀደመ ከዚያ ቅድስት ፋውስታ ኮዋልስካ የምሕረት መንፈሳዊነት የኖረችበትና የመሰከረችበትን ቅዱስ ታሪክ ከሚያስታሰው ከላጋውኒኪ ክልል የተነሣ የክራኮቪያ ከተማ ምእከል ወደ ሆነው የብሎኒያ የአታክት ሥፍራ የደረሰ መንፍሳዊ ንግደት መካሄዱ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አክለው፥ በተደረገው መንፍሳዊ ንግደት በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሕይወት አቢይ ትርጉም ባላቸው ሥፍራዎች እርሱም ከቅዱስ ፍሎሪያኖ ቤተ ክርስቲያን ወጣት ካህን ሆነው ባገለገሉበት እንዲሁም እ.ኤ.አ. ከ 1963 እስከ 1978 ዓ.ም. በዋውል ኮረብታ በሚገኘው የክራኮቪያ ርእሰ ሰባካ እረኛ እያሉ ያገለገሉባት ካቴድራል ፍኖት በማድረግ  መከናወኑ ጠቅሰው፡ የተከናወነው መንፍሳዊው ንግደት የዓለም አቀፍ ወጣቶች ቀን ትእምርት የሆኑትን አቢይ ቅዱስ መስቀልና የቅድስት ድንግል ማርያም መድኅነ ዘሮማውያን ጭምር ያስከተለ ነበር ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቀደም በማድረግ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ለፖላንድ ወጣቶችና በአገሪቱ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አስተላልፈዉት በነበረው የድምጸ ርእየት መልእክት፥ ከኤውሮጳ ካፍሪካ ከአመሪካዎች ከእስያና ከኦቻይና የተወጣጡ ወጣቶች ጉዞአቸውን ወደ ክራኮቪያ አቅንቷል። ጉዞው የእምነትና የወንድማማችነት ንግደት እንዲሆን ወጣቱ ለተነሱባቸው አገሮችና  ወደ ክራኮቪያ የሚደርጉት ጉዞ ሁሉ እባርካለሁ በማለት  ቡራኬየን አስተላልፈው፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያንን “ምህረትን የሚያደርጉ ምሕረትን ስለሚያገኙ ደስ ይበላቸው (ማቴ. 5,7) የሚለውን ቃሉ በሕይወታችሁ ለማጣጣም የሚያበቃችሁ ጸጋው ይስጣችሁ ብለው፥ ለዓለም የውህደት ትእምርትና ምስክርነት ለማቅረብ ያንን የተለያዩ አሕዛብ ባህሎች ቋንቋና ዘውገ በጠቅላላ ኅብረ ቅንስል የሚያጸና የምኅረት አካል በሆነው በኢየሱስ ስም የምታሳዩት አንድነት የውህደት ውበት የሚመሰክር የአሃድነት ትእምርት ነው ከእናንተ ጋር ለመገናኘት ትልቅ ጉጉት አለኝ በዓሉ የምኅረት አሃድነትናና ኅቡር ቅንስል ትእምርት ነው ያሉትን ሓሳብ ይኸው ወጣቶች እ.ኤ.አ. ከ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምረው እየመሰከሩት ነው።  የመለኰታዊ ምሕረት ርእሰ ከተማ የሆነቸው ክራኮቪያ የወጣቶች ኢዮቤልዩ እየኖርች ነው ያሉት ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቱ በአገረ ፖላንድ የሚገኙት የመገናኛ ብዙኃን ለዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀንና እዛው ልክ ከዓስር ዓመት በከተማይቱ የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እንዲሁም ልክ 14 ዓመት እያስቆጠረ ካለው ቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በከተማይቱ አካሂደዉት ከነበረው ሐዋርያዊ ጉብኝት በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በፖላንድ የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ላይ በማተኮር ከወዲሁ ብዙ ዘገባ እያጠናቀሩ ናቸው ብለው።

ይኽ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ 15ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ዋና ዓላማው ካደረገበት ከዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ቀጥሎ በፖላንድ ከምትገኘው 1050 ዓመቷን እያስቆጠረች ካለቸው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር የሚገናኙበትና በዚያ የጽሞና ጸሎት የሚያሳርጉበት የመቅሰፍት ሰፈር አውሽዊዝና ቢርከናው የሚያካሂዱት ሐዋርያዊ የጸሎት ጉብኝት ጭምር ያካተተ መሆኑ ጂሶቲ ገልጠው በስቃይ ፊት ለማንባት እንችል ዘንድ ክፋት ስቃይ ተላምዶ ከመኖር የሚያላቀን እግዚአብሔር የማንባት ጸጋውን  ይሰጠን ዘንድ በማለት ያቀረቡት ጥሪ የሚኖር ሓዋርያዊ ጉብኝት ጭምር መሆኑ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.