2016-07-22 16:35:00

ኵባ፥ በክራኮቪያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለመሳተፍ ለማይችሉ ወጣቶች አማራጭ ብሔራዊ የወጣቶች ቀን


በክራኮቪያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በኤኮኖሚና ፖለቲካዊ ምክንያት ለመሳተፍ የማይችሉ የኵባ ወጣቶች ለዚያ ለክራኮቪያው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀንና ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቅርብ ለመሆን ታልሞ በኵባ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከዚያ የክራኮቪያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጋር የሚያዋህዳቸውና ያንን መንፈስ ለመኖር የሚያስችላቸው ብሔራዊ የወጣቶች ቀን ማዘጋጀቷ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ሊዛ ዘንጋሪኒ ሲር የዜና አገልግሎት ያሰራጨው ዜና ጠቅሰው ያመለክታሉ።

ይኸንን እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 28 ቀን እስከ ሐምሌ 31 ቀን 2016 ዓ.ም. ሊካሄድ ተወስኖ ያለው የኩባ ብሔራዊ የወጣቶች ቀን ምክንያት በማድረግም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለኩባ ወጣቶች መልእክት ያስተላለፉም ሲሆን። የኵባ ወጣቶች በሪዮ ተካሂዶ በነበረው ዓለም አቀፍ የውጣቶች ቀን በመገኘት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ወጣቱ ከዚህ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ፍጻሜ በኋላ ወደ አካባቢው ተመልሶ የኃሴት ምስክር እንዲሆንና አበይት ነገራት ከማለም እንዳይቦዝን፡ ዘወትር ዕለታዊ ኑሮ በመጋፈጥ የበለጠውን ለመጨበጥ ጥረት በማድረግ ከኢየሱስ ጋር እንዲጓዙ በማለት ሰጥተዉት የነበረው የአደራ ቃል መሠረት በማድረግ በሃቫና ያዘጋጁት ብሔራዊ የወጣቶች ቀን መሆኑ ቀደም በማድረግ ለቅዱስነታቸው አስተላልፈዉት በነበረው መእክት አስታውቀው እንደነበር ሲር የዜና አግልግሎ ያሰራጨው ዜና ጠቅሰው ያመለከቱት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ዘንጋሪኒ አያይዘው፥ የሃቫናው የኵባ ወጣቶች ቀን በክራኮቪያ የሚካሄደው 31ኛው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መርሐ ግብር የሚከተልና “ምኅረትን የሚያደጉ ምኅረትን ስለሚያገኙ ደስ ይበላቸው” (ማቴ, 5,7) የሚለውን መርሕ ቃሉን የሚከተል ሲሆን። የሃቫናው ብሔራዊ የወጣቶች ቀን በአገሪቱ የሚታጠር ሳይሆን ያንን የክራኮቪያው ዓለም አቀፍ የወጣቶ ቀን መንፈስ ለመኖር ታልሞ የሚካሄድ ነው ብለው አያይዘውም በዚህ በኵባ በሚካሄደው ብሔራዊ የወጣቶች ቀን 1,400 ወጣቶች እንደሚሳተፉም ያመለክታሉ።

የዚህ የኵባው ብሔራዊ የወጣቶች ቀን ትምህርተ ክርስቶስ ፍኖተ መስቀል በቅዱስ የምኅረት በር የመግባትና ውይይት ያካተተ ሲሆን በኤኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ ችግሮች ምክንያት በክራኮቪያ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የማይሳተፉ ቢሆንም ቅሉ ይኽ ውስንነት ያንን የክራኮቪያ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን መንፈስ እንዳንኖሩ የሚዳርጋቸው እንዳልሆነ የኩባ ወጣቶች በአገራቸው የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ባዘጋጀችላቸው ብሔራዊ ዓቀፍ የወጣቶች ቀን በመሳተፍ ሊመሰክሩት በመዘጀት ላይ ናቸው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.