2016-07-20 16:59:00

ቨነዝዋላ፥ ቤተ ክርስቲያን ከሚሰቃየው ሕዝብ ጎን


በአሁኑ ወቅት በቨነዝዋላ ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊ ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አለ መረጋጋት ተከትሎ እየተዛመተ ያለው የምግብና የመድሃኒት እጥረት መፍትሔ እንዲያገኝ በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ባለፉት ቀናት ባካሄደው ጠቅላይ ጉባኤ አማካኝነት ለአገሪቱ መንግሥት ጥሪ ማስተላለፉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አልቫሮ ቫርጋስ ማርቲኖ ካጠናቀረው ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

በቨነዝዋላ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በማስደገፍ የቨነዝዋላ ርእሰ ከተማ ካራካስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኾርገ ኡሩሳ ሳቪኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት በሚያካሂዳቸው ጠቅላይ ጉባኤዎች አማክኝነት የአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ጭምር ይመለከታል የሚታዩት ችግሮች ሁሉ በጥልቀት በመወያየት መንስኤው ለይቶ በመተንተን መፍትሔ ይሆናል የሚለውን ሃሳብ ለሚመለከተው አካል በተለያየ መልኩ በሐዋርይዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት ጭምር ይፋ ያደርጋል። ስለዚህ በአሁኑ ወቅት ያለው ውጥረት መንግሥት መፍትሔ በማፈላለጉ ሂደት ተግቶ የሕዝብ ሰብአዊ መብትና ክብር ይዋስ ዘንድ ብፁዓን ጳጳሳቱ ባካሄዱት ጠቅላይ ጉባኤ አማካኝነት ጥሪ እንዳቀረበም ገልጠዋል፡

ብፁዓን ጳጳሳቱ በቅድሚያ ርእስ የሚያደርገው የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይና ሂደት የሚመለከት ቢሆንም ቅሉ የሕዝብ ችግር የቤተ ክርስቲያኒቱ ችግር በመሆኑም ጭምር ከሚሰቃየው ጎን በመሆን ድምጽ ለሌለው ድምጽ በመሆን ፍትሕና የሕግ ሉኣላዊነት እንዲረጋገጥ ጥሪ ታቀርባለች፡  ካሉ በኋላ መንግሥት በተለያየ ወቅት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮም ሆኑ የቨነዝዋላ ብፁዓን ጳጳሳት የሚያቀርቡት ጥሪ የሚያዳምጥ አይመስልም። የመንግሥት ተልእኮ በማክበር የአገሪቱን የሕዝብ ችግር ለሚመለከተው አካል ቤተ ክርስቲያን አቤት በማለት መፍትሔ እንዲገኝለትም በማበረታታት መፍትሔ ይሆናል የምትለው ሃሳብ ታቀርባለች። ሆኖም መንግሥት ለማዳመጥ ፈቃደኛ ባለ መሆኑ ችግሩ እየከረረ መጥቷል። የምግብ እጥረት የመድሃኒት እጥረት ወደ ከፋ ደረጃ እያዘገመ ነው። ከተለያዩ የመንግሥት ያልሆኑት የተራድኦ ማኅበራት የቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራት የመድሃኒትና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለማፋጠን ብዙ ጥረት እየተደረገና ያሰባሰቡት እርዳታ ወድ ቨነዝዋላ ለመላክ ዝግጁ ናቸው ነገር ግን መንግሥት የምግብም ሆነ የመድሃኒት እጥረት የለም የሚል ተጨባጩን ማሕበራዊና ኤኮኖሚያዊ ጉዳይ የሚክድ በመሆኑ ድጋፉንም ጭምር አያስፈልግም ይላል፡  እንዲህ አይነቱ የመንግሥት መልስ ዓላማው ምን መሆኑ ግራ የሚያጋባ ነው፡ አልፎ አልፎም ጸረ ቤተ ክርስቲያን የሆነ ተግባር ይታያል። ቤተ ክርስትያን የፖለቲካ ድርጅት አይደለችም ጸረ መንግሥትም ሆነ የመንግሥት ደጋፊም አይደለችም ግድ የሚላት የሕዝብ ጉዳይ ነው ካሉ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ዝም ለማሰኘት ብዙ ጥረት ሚደረግም የሕዝብ የድኻው የተናቀው የሚሰቃየው ሕዝብ ድምጽ ከመሆን መቼም ቢሆን አትቦዝንም ጥሪዋም ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.