2016-07-13 16:18:00

ቅዱስ አባታችን የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ለሚከታተለው ጽሕፈት ቤት አዲስ አባላት ሾሙ


እ.ኤ.አ. ሐምሌ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ተንከባካቢ ጽሕፈት ቤት አባላት እንዲሆኑ በሊባኖስ የአንጽዮኪያ የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ካርዲናል በቻራ ቡትሮስ ራይ፡ በኬንያ የናይሮቢ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆን ንዠው፡ በምያንማር የያንጎን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ቻርለስ ሙንግ ቦ፡ የምስራቅ ስርዓት

የሚከተሉት አቢያተ ክርስቲያን ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ለዮናርዶ ሳንድሪ፡ የካህናት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል በኒያሚኖ ስተላ፡ በአየር ላንድ የዱብሊን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዲያርሙይድ ማርቲን፡  በሊትዋኒያ የቪልኒዩስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ጂንታራስ ጉሩሳስ፡ በኢጣሊያ የአልባኖ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሰመራሮ፡ በፈረንሳይ የፖንቶይሰ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ስታኒስላስ ላላነ፡ በስፐይን የጉኣዲክስ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጂነስ ራሞን ጋርሲያ በልትራን፡ በፖርቶጋሉ የሊስቦና ረዳት ጳጳስ የኤልቫስ ሰበካ ሱዩመ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኑኖ ብራስ ዳ ሲልቫ ማርቲንስ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የኃይማኖት ነጻነት በሚከታተለው ድርገት ሥር አማካሪ ዶክተር ኪም ዳኔሊስ፡  በጀርመን ሙዩኒክ የኢየሱሳውያን የፍልስፍና መንበረ ጥበብ የሥነ መገናኛ ብዙኃን ሥነ ምግባር መምህር ማርኩስ ሻኽተር፡ በመክሲኮና በስፐይን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ለሚከታተለው ድረገት አማካሪ የሥነ መገናኛ ብዙኃንና የሥነ አእምሮ ሊቅ ለቲሲያ ሶበሮን ማይነሮን መሾማቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቅ።








All the contents on this site are copyrighted ©.