2016-07-11 16:13:00

የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት መግለጫ፥ እግዚአብሔርና አገራችንን እናፈቅራለን


የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. የተከበረው የአገራቸው ዝክረ 200ኛው የነጻነት ቀን ምክንያት የሳንታ ፈ ደ ላ ቨራ ክሩስ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት የብፁዓን ጳጳሳቱ ምክር ቤቱ ሊቀ መበር ብፁዕ አቡነ ኾሰ ማሪያ አራንሰዶ ፊርማ የተኖረበት ባስተላለፉት መልእክት፥ 200 ዓመታት እያስቆጠረ ያለው የነጻነት ቀን ስናከብር ማስታወስ ያለብን የእግዚአብሔ ኵላዊ አባትነትና ገዛ አገርን ማፍቀር የሚጋጭ ጉዳይ አለ መሆኑ ነው፡ የአንድ አገር ዜጋ ያንድ መሬት ያንድ ባህልና ቋንቋ ልጅ መሆን ሁላችን በእግዚአብሔር ኵላዊ አባትነት ምክንያት ኵላዊ ወንድማማችነት ለመኖር መጠራታችን አብሮ የሚሄድ እንጂ አንዱ ሌላውን የሚያገል አይለም እንዳሉ ሲር የዚና አገልግሎት አስታወቀ።

እምነት የሚያገል ሳይሆን የግኑኝነት የመከባበርና የውይይት መንገድ ነው

እምነት ከእግዚኣብሔር የተቀበልኩት ጸጋ ነው። ነገር ግን ጸጋው የተቀበልኩት ባንድ አገር ባንድ ባህል ባንዲት ቤተሰብ ውስጥ ነው። እግዚአብሔርን አፈቅረዋለሁኝ አገሬንም እወዳለሁኝ ስለዚህ እምነት አግላይ ሳይሆን የግኑኝነት የመከባበር የውይይት መንገድ ነው። አገር ጸጋ ነች። ጸጋ በመሆንዋን ኃላፊነት ጭምር ነች እንዳሉ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፥ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ማክሪና ሌሎች አበይት የመንግሥት አካላት እንዲሁም ምእመናን የተሳተፉበት በአርጀቲና የቅድስት መንበር ሓዋርያዊ ልኡክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ፓውል ኤሚል ትሸሪግና የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ አውረሊዮ ፖሊ ጭምር የተሳተፉበት እግዚአብሔር ለአርጀቲና ስለ ጸገወው 200ኛ ዓመቱን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9 ቀ ላስቆጠረው የነጻነት ቀን ምክንያት ንሴብሐከ ኦ እግዚእነ የሊጡርጊያ ሥነ ስርዓት በቅድስት ድንግል ማርያም የትስብእት እመቤት ካቴድራል በሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ አልፍረዶ ዘካ ተመርቶ ካረገው የመስጋና ሊጡጊያ በመቀጠል በብፁዓን ጳጳሳት የታጀቡት ብፁዕ ካርዲናል ማሪዮ አውረሊዮ ፖሊ የተመራ መሥዋዕተ ቅዳሴ ማረጉንም አስታወቀ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.