2016-07-11 16:04:00

ቅዱስ አባታችን፥ ነፍሴ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ፒዮቫነሊ ቤተ ክርስቲያንን በጽናት ያፈቀሩ


እ.ኤ.አ. ከ 1983 እስከ 2001 ዓ.ም. በኢጣሊያ የፊረንዘ ከተማ ሊቀ ጳጳስ በመሆን ያገለገሉት ብፁዕ ካርዲናል ሲልቫኖ ፒዮቫነሊ በ 92 ዓ.ም. ዕድሚያቸው እ.ኤ.አ. ሐምሌ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመ ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የብፁዕ ካርዲናል ፒዮቫነሊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት እንደተነገራቸው ለፊረንዘ ሊቀ ጳጳሳት ለብፁዕ ካርዲናል ጁዘፐ በቶሪ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የተለግራም መልእክት፥ ብፁዕ ካዲናል ፒዮቫነሊ ባደረባቸው ህመም ምክንያት ለረዥም ዓመታት ገዛ እራሳቸውን ለጌታ ፈቃድ በመተው ያንተ ፈቃድ ይሁን በሚል በታማኝ እምነት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ሲለዩ ልባችን በሃዘን የተነካ ቢሆንም ቅሉ በሁሉም የሕይወት ደረጃና ሁነት እሜን ብሎ ለሚኖር ሕይወት አብነት ሆነዋል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅርቡ ለብፁዕ ካርዲናል ፒዮቫነሊ ስልክ በመደወል ቅርበታቸውና ጸሎታቸውን እንዳረጋገጡላቸው ጠቅሶ፥ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የቴለራም መልእክት፥ ለነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ፒዮቫነሊ ቤተሰቦችና ቤተዘመድ እንዲሁም ለፊረንዘ ሰበካ ባጋጠማቸው ሓዘን ቅርብ መሆናቸ ገልጠው በጵጵስና ወንድም ለሆኑት ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ፒዮቫነሊ የሰጡት ሐዋርያዊ አገልግሎትና እግብር ላይ ያዋሉት ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ስናስታውስ ወንጌልን በሐሴትና በተስፋ እንዳገለገሉና ቤተ ክርስቲያንን በጽናት እንዳፈቀሩ እንገነዘባለን እንዳሉ አስታውቀዋል።

የኢጣሊያ መራሔ መንግስት ማተዮ ረንዚ በበኩላቸውም የብፁዕ ካርዲናል ፒዮቫነሊ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት ዜናው እንደደረሳቸው ለፊረንዘ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል በቶሪ ባስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የቴለግራም መልእክት ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ፒዮቫነሊ ለፊረንዘ ከተማ መንፈሳዊ አብነትና ለከተማይቱ ሕዝብ መንፈሳዊነት ማመሳከሪያ እንደነበሩ ገልጠው የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን ይፋ ማድረጋቸው የመራሔ መንግሥት የዜናና ኅትመት ቢሮ ያስራጭው መግለጫ የጠቀሰው የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ነፍሰ ኄር ካርዲናል ፒዮቫነሊ ካንዲት ላባደር ቤተሰብ በሮማ ከተማ የተወለዱ እ.ኤ.አ. በ 1947 ዓ.ም. የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን አጠናቀው ማዕርገ ክህነት እንደተቀበሉም በፊረንዘ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲና ኤሊያ ዳላ ኮስታ የእግዚአብሔር አሳቢነትና ተግባር መሥራች ለሆኑት ለአባ ጁሊዮ ፋቺበኒ የቅርብ ረዳት ሆነው እንዲያገለግሉ ተመድበው በፊረንዘ ከተማ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ የተደቀነውን ውስብስብ ሁነትና ተጋርጦ ሁሉ ለመወጣት ሕዝብን በማገልገል ላይ እያሉ በ 1948 ዓ.ም. የፊረንዘ ከተማ የንኡስ የዘርአ ክህነት ተማሪ አለቃ ለነበሩት ለአባ ኤንሪኮ ባርቶለቲ ረዳት በመሆን የሰጡት የ12 ዓመት አገልግሎት ለመላ ሕይወታቸው አቢይና ጥልቅ ተመክሮ ጥሎ ያለፈ መሆኑና እ.ኤ.አ. በ1979 ዓ.ም.  በፊረንዘ ሰበካ የሊቀ ጳጳሳት የቅርብ ሐዋራያዊ መንበር ውስጥ ተምድበው እንዲያገለግሉ በፊረንዘ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት በብፁዕ ካርዲናል ጆቫኒ በነሊ ተሰይመው በማገልገል ላይ እያሉ በ 1982 ዓ.ም. ረዳት ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ ተሹመው  እንዳገለገሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ጠቁሞ፥ እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 1983 ዓ.ም. የፊረንዘ ከተማ ሊቀ ጳጳስ እንዲሆኑ በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ተሰይመው ሲያበቁ ከሁለት ዓመት በኋላ ግንቦት 25 ቀን  በሮማ የባልጸጋይቱ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርሲቲያን ስዩም ጳጳስ ሆነው የፊረንዘ ሰባካ ካርዲናል ተብለው መሾማቸው ያስታውሳል።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም በብፁዕ ካርዲናል ፒዮቫነሊ ዕረፍት ምክንያት ካርዲናሎች ጉባኤ አባላት ብዛት ወደ 212 እነርሱም በሕገ ቀኖና መሠርት 112 የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የመምረጥ መብት ያላቸውና በእድሜ መግፋ ምክንያት የመምረጥ መብት የሌላቸው 100 አባላት የንዳሉት የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.