2016-07-06 15:02:00

ደቡብ ሱዳን፡ ብፁዕ አቡነ ሂቦሮ፥ ጥላቻ የሚያስፋፋ ተግባር ይገታ


የፖለቲካ ሰልፎች እርስ በእራስቸው የሚወቃቀሱበት አንዱ ሌላውን በማጥላላት የሚነዛው ጥላቻን የሚቀሰቀስ ንግግር አገር ለሰላም ከመምራት ይልቅ አገር የሚያዋልት ለመከፋፈል የሚዳርግ ተግባር መሆኑ በደቡብ ሱዳን የቶምቡራ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤድዋርድ ሂቦሮ ባለፉት ቀናት በአንድ የአገራቸው የራዲዮ ጣቢያ ባስተናገደው ውይይት በመሳተፍ በማብራራት አንዱ ደቡብ ሱዳን ለግጭትና ለዓመጽ የሚዳርጋት ጉዳይ ቢኖር የፖለቲካ አካላት ገዛእ ራሳቸውን ለማገናኘት የሚጠቀሙበት ሌላው የሚያጥላላና ጥላቻ የሚቀሰቅስ ንግግርና የሚጠቀሙባችው ቃላቶች ናቸው በማለትም ምላስ ከሚተኮሰው ጥያት በላይ ለከፋ ጉዳት የምያጋልጥ ነው እንዳሉ የቫቲካን ርዲዮ ጋዜጠኛ ኢዛቤላ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።

እምቢ ለመከፋፈል፡ በጋራ የጋራ ጥቅም መሻት

መከፋፈልን ከሚዘራው ልሳን ይልቅ ግንባታ ንዴትና ቁጣ ከሚወልደው ልሳን ይልቅ ሰላማዊ ግኑኝነት አመጽ አልቦ ፖለቲካዊ ተነጻጽሮ ከሚያነቃቃ ልሳን ይልቅ የጋራ ጥቅም በጋራ መሻት በሰላም መንገድ የሚመራ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ሂቦሮ ማብራራታቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘውም፥

እ.ኤ.አ. ሰነ ወር 2016 ዓ.ም. ማብቂያ በደቡብ ሱዳን ዋው ክልል በሱዳን ህዝባዊ ነጻነት ግንባር ታጣቂ ኃይሎችና በሌሎች ታጣቂ ኃይሎች መካከል ግጭት መካሄዱና አርባ ሰዎችም ለሞት መዳረጋቸው የክልሉ የዜና ምንጮች ጠቅሰው ከገለጡ በኋላ ብፁዕ አቡነ ሂቦሮ ይኽ ሁሉ የሚታየው ውጥረትና ግጭት የውይይት ባህል ካለ ማጎልበትና ውይይት ሲጎድል መወያየት የሚገባቸው ተጠያቂ አካላት ተፋጠነው ጠበንጃየ ለማለት ከሚቃጣው ግፊት የሚወልደው ነው እንዳሉ ገልጠዋል።

የተረጋጋች አገር ለማቆም የሚያበቃ መንገድ ማበጀት

ብፁዕ አቡነ ሂቦሮ በሱዳን የሚገኙት አቢያተ ክርስትያናት ሁሉም ሃይማኖቶች የመንግሥትና ፍትሃ ተቋማት የውይይት ባህል እንዲበለጽግ በመደገፍ ማንኛውም መራሂ አካል ምን አይነት አገር እንደሚሻ በማስተንተን ይኸንን ሃሳቡን በሰላማዊና የተረጋጋች አገር ለማቅናት የሚደግፍ መንገድ በማበጀት ለሕዝብ ማስተዋወቅ ይኖርበታል እንዳሉ ፒሮ ገልጠው ይኽ በእንዲህ እንዳለም ደቡብ ሱዳን እ.ኤ.አ. ሐምሌ 9 ቀን 2011 ዓ.ም. ነጻነቷን የተቀዳጀችበት ዕለት ለማክበር በመዘጋጀት ላይ ስትሆን ሆኖም ባለፉት ዓመታትም በአገሪቱ ውስጥ በርእሰ ብሔር ኪር የመንግሥት ወታደሮችና በምክትል ርእሰ ብሔር ማቻር ደጋፊያን መካከል ርእሰ ብሔር ኪር ላይ የተጣለው መንፈቅለ መንግስት ክሽፈት ተከትሎ ከ 2013 ዓ.ም. ጀምሮ የተቀጣጠለው ግጭት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በርእሰ ብሔር ኪርና በምክትል ርእሰ ብሔር ማቻራ መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት  ሊቃጭ መቻሉንም በማስታወስ ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.