2016-07-01 16:35:00

ቤተ ክርስቲያንና የአቢያተ ክርስቲያን እንቅስቃሴዎች


እ.ኤ.አ. ሰኔ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የክርስቲያኖች አንድነት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮኽ የፍትህና የሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ቱርክሶን የሚያሳትፈው በጋራ ለኤውሮጳ በሚል ርእስ ሥር በሞናኮ ዘባቪየራ ሊካኤድ የተጠራው የሁሉም አቢያተ ክርስቲያን ማኅበርሰብና የክርስትያን እንቅስቃሴዎች የሁሉም አቢያተ ክርስቲያን ምሉእ ውህደት የሚል ይኸንን ውህድነት የሚኖርበት አራተኛው ዓውደ ጉባኤ መጀመሩ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሲቲ አያይዘው፥ ይኽ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው ዓውደ ጉባኤ  ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮና የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በጠለመዎስ ቀዳማዊ በድምጸ ራእይ የሚሸኝ በቀጥታ የሚያስተላልፉት መእክት እንደሚታደልና ይኽ የድምጸ ራእይ መልእክት ሚኒዩክ በሚገኘው ማእከላዊ አደባባይ እንሚተላለፍም አስታውቀዋል።

በጋራ ለኤውሮጳ በሚል ርእስ ሥር በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጉባኤ የካቶሊክ ወንጌላዊት የኦርቶዶክስና የአንግሊካን አቢያተ ክርስቲያን እንቅስቃሴዎች ግኑኝነታቸው በተለያየ መስክ አብረው የሚያከናውኑት አገልግሎት ሁሉ የሚዳስስና ያንን የ15 ዓመቱ የጋራ ግኑኝነት የአፍቅሮተ ዘቤት መስራች ኪያራ ሉቢክ ካቶሊካዊው የቅዱስ ኤጂዲዮ እንቅስቃሴ መሥራች ፕሮሰር አንድረያ ሪካርዲና የሌሎች አቢያተ ክርስቲያን እንቅስቃሴዎች መሥራቾች ጭምር በጋራ ያነቃቁት የጋራ ውይይት የሚያበረታታ እቅድ ሲሆን ይኸንን በማስታወስ እነዚህ እንቅስቃሴዎች ከመንፈስ ቅዱስ የተቀብሉት የማኅበራቸው ዓላማ በቤተ መዘክር ለማስቀመጥ ሳይሆን ለኤውሮጳ ለማሳወቅና ኤውሮጳን ለማገልገል ባጠቃላይ ለመላ ሰው ዘር አገልግሎት መሆኑ ለመመስከር መጠራታቸው የሚያስታውስ ዓውደ ጉባኤ መሆኑ ጂሶቲ ያመለክታሉ።

የዚህ የ 2016 ዓ.ም. ጉባኤ ሌላው እይታውም እ.ኤ.አ. በ 2017 ዓ.ም.  ከሚታሰበው የሉተራን ህዳሴ  ዝክረ 500ኛው ዓመት ላይ ያኖረ ሲሆን በጉባኤው የመጀሪያው ቀን ውሎው ብፁዕ ካርዲናል ካስፐርና ወንጌላዊው ጳጳስ የጀርመን ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን ሊቀ መንበር ክብሩ ማርጎት ካስማን ንግግር ያስደመጡም ሲሆን። ሚጥሮፖሊታ ሰራፊም ንግግር ከሚያስደመጡ ታዳሚዎች አንዱ ሲሆኑ ቅዱስ አባታችንና ብፁዕ ወቅዱ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ የሚያስተላልፉት የድምጸ ራእይ መልእክት በጉጉት እየተጠበቀ መሆኑ የአቢያተ ክርስቲያን እንቅስቃሴዎች በጋራ ለኤውሮጳ ቅዋሜ ሊቀ መንበር ዲየጎ ጎለር ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጧል።

ከኤውሮጳ እግጅ ሩቅ ከሆነው ክፍለ ዓለም የመጡት ቅዱስ አባታችን እውነተኛው የኤውሮጳዊነት ትርጉሙን እየመሰከሩ ናቸው። የኤውሮጳ ስርወ ባህል ክርስትና መሆኑና ኤወሮጳዊነት ይኸንን ስር መሰረቱን እስካላከበረ ድረስ በቀላሉ ለተለያየ ችግር እንደምትጋለጥ ካለው ወቅታዊው ሁኔታ ጋር በማዛመድ የሚሰጡት ምእዳን ለኤውሮጳ የሚያስፈልጋት ጥሪ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.