2016-06-29 15:55:00

ሢሜተ ጵጵስና በኢትዮጵያ ለሃዋሳ አገረ ስብከት


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢትዮጵያ የሃዋሳ አገረ ስብከት ሐዋርያዊ መስተናብር እንዲሆኑ ክብሩ ኣባ ሮበርቶ በርጋማስኪ የኣምቢያ ሥዩም ጳጳስ ብለው እንደ ሰየሙዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።

ብፁዕ አቡነ ሮበርቶ በርጋማስኪ በሚላኖ ክፍለ ሃገር በምትገኘው ሳን ዶናቶ ሚላነሰ ወረዳ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 1954 ዓ.ም. የተወለዱ የሳሊዚያን ማኅበር አባል በመሆን እ.ኤ.አ. መስከረም 8 ቀን 1975 ዓ.ም. የመጀመሪያ ማህላ በፒነሮሎ ከተማ ከዛም እ.ኤ.አ. መስከረም 13 ቀን 1981 ዓ.ም. በሮማ ከተማ ዓቢይ ማህላ የፈጸሙ መሆናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አያይዞ፥ ብፁዕ አቡነ በርጋማስኪ ከ 1975 እስከ 1982 ዓ.ም. በቶሪኖ ከተማ ፍልስፍና በቅድስት መሬት ክረሚሳን የቲዮሎጊያ ትምርህታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 1982 ዓ.ም. በብረሺያ ከተማ በኰምቦኒ ማኅበር አባል በሃዋሳ አገረ ስብከት ቀዳሜ ጳጳስ በነበሩት በነፍሴ ኄር በብፁዕ አቡነ ኣርሚዶ ጋስፓሪኒ ማዕርገ ክህነት መቀበላቸው ገልጦ፥  ማዕርገ ክህነት ከተቀበሉ በኋላም በኢትዮጵያ ዲላ ከተማ ከ 1982 እክሰ 1993 ዓ.ም. በመቂ ሃገረ ስክበት ሥር በዝዋይ ቆሞስ በመሆን ከ 1993 እስከ 2007 ዓ.ም. አገልግለው በአዲስ አበባ መካኒሳ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የሳሊዚያን ተግባር ዋና አስተዳዳሪ በመሆ ከ 2007 እስከ 2009 ዓ.ም. ከዛም ከ 2009 ዓ..ም. ወዲህ በዲላ የረዳኢተ ቅድስተ ማርያም ቁምስና ቆሞስና የሃዋሳ አገረ ስብከት የጳጳስ ረዳትትና የተልእኮና እንዲሁም የካህናት ጉዳይ ለሚከታተለው ምክር ቤት አማካሪ በመሆ እንዳገለገሉ ያመለክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.