2016-06-24 17:11:00

የመላ ኦርቶዶክሳውያን ኣቢያተ ክርስቲያን ሲኖዶስ፥ ተእልኮ በወቅታዊው ዓለም


ከባለፉት ምእተ ዓመታት ወዲሁ ብዙ ማኅበራዊ ፖለቲካዊ ሥነ ምርምራዊ ለውጦች ተከስተዋል፡ ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ባለ ዓለም ፊት በባለህበት ተራመድ ሕይወት ቆማ መቅረት እይገባትም፡ ስለዚህ ከወቅታዊው ሁነት ውጭ ሆኖ መኖር እንደማይገባት የማያጠያይቅ ጉዳይ ነው። ስለዚህ ከዚያ ጥንታዊው መንፈሳዊ ባህሏ፡ ትውፊት ሳትላቀቅ በድግምግሞሽ ሕይወት ሳትቀር ከዚያ ውስጣዊ ሃብቷ ለወቅታዊው ጥያቄ መልስ የሚያሰጣት ኃይልና ጥበብ ታገኛለች፡ የሚል ሃሳብ በክሬታ በመካሄድ ላይ ካለው የመላ ኦርቶዶክሳውያን ኣቢያተ ክርስቲያን ሲኖዶስ መፍለቁ ሲር የዚና አገልግሎት አስታወቀ።

የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በወቅታዊ ዓለም

ሲር የዜና አገልግሎት እንደገለጠው፥ የቁስጥንጥንያ የውህደት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ፓትሪያክ ቃለ አቀባይ ኣባ ጆን ክርይሳይጊስ የሲኖዶሱ ተጋባእያን የአሥሩ የኦርቶዶክሳውያን አቢያተ ክርስቲያን ፓትሪያክ ና ሊቀ ጳጳሳሳት ባለፈው ሰኞ እ.ኤ.አ. ስኔ 20 ቀን 2016 ዓ.ም. የጀመሩት ውይይት ዝግ ሲሆን የዕለቱ ጉባኤ ሂደት በተመለከተም በእያንዳንዱ የጉባኤ ቀን ከቀትር በኋላ ልክ ሦስት ሰዓት ተኵል ከውጭና ከውስጥ ለመጡት የተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ልኡካን ጋዜጠኞች በፓሪይርኮቹ ቃለ አቀባዮች ኣማካኝነት መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን፡  ሲኖዶሱ የተጀመረው የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ተልእኮ በወቅታዊው ዓለም በሚል ርእስ ሥር የተጠናቀረው ሰነድ ተንተርሶ የሚካሄድ ነው፡ ይኽ ሰነድ በተራውም ያንን የመላ ኦርቶዶክሳውያን ኣቢያተ ክርስቲያን ሦስተኛ ሲኖዶስ “ሰላም ፍትህ ነጻነት ወድማማችነት ፍቅር በሕዝቦች መካከል እዲረጋገጥ እንዲሁም ዘጋዊነት ዘረኝነት ጨርሶ እንዲወገድ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተዋጽኦ” በሚል ርእስ ሥር በ1986 ዓ.ም. ተጠናቅሮ የነበረው ሰነድ ዓቢይ ግምት የሰጠ መሆኑ ቃለ አቀባዩ የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጠቀሰው ሲር የዜና አገልግሎ ያመለክታል።

የጸኣተኞች አገር የውህድነ ተግባር ማበረታታት

የኦርቶዶክሳውያን ኣቢያተ ክርስቲያን በተለያዩ አገሮች ተሰደው በሚገኙት ምእመናን የተሞሉ ናቸው፡ እነዚህ ስደተኞች ምእመናን ዘወትር በብፁዓን ፓትሪያኮቻቸውን የሚወከሉ ለመሆናቸው የማይዘነጉ ናቸው ያሉት ኣባ ክርይሳቭጊስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰው እነዚህ ምእመናን ስደተኞች ከ 14 የኦርቶዶክሳውያን አቢያተ ክርስቲያን የተወጣጡ መሆናቸውም በማስታወስ ሲኖዶሱ እነዚህ ጸአተኞች ምእመናን ለማዋሃድ የኦርቶዶክስ ኣቢያተ ክርስቲያን ተግባር ርእስ ዙሪያ ሰፊ ውይይት እያካሄደ ነው ሲሉ ማብራራታቸ  ሲር የዜና ኣገልግሎት አስታወቀ።

ወንድማማችነት መንፈስ የተካነው የሲኖዶሱ ሂደት

የሮማኒያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ቃለ አቀባይ ኣባ ኢኑት ማቭርቺ በበኵላቸውም የሲኖዶሱ ሂደት ወንድማማችነት መንፈስ የተካነ መሆኑ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቁመው የኦርቶዶክስ ኣቢያተ ክርስቲያን ያላቸው ልዩ መለያቸው ልዩነት ሳይሆን ሃብት ነው፡ ስለዚህ ሃብት ለመሆኑ ግንዛቤው ሲኖራቸው በጋራ ወቅታዊው ዓለም ለሚያቀርበው ተጋራጦ በመወጣት ለሚሰጡት መልስ ብርታት ነው። ሲኖዶሱ የእግዚኣብሔር ጸጋ ነው እንዳኡ የገለጠው ሲር የዜና ኣገልግሎት አክሎ፥ ተጋባእያኑ የእግዚኣብሔር ቤት ውህድነት ነው፡ ይኸንን በማስተዋልም በፍቅር በመቀራረብ በጋራ የሚሰጡት መልስ እየለዩ መሆናቸው ጠቅሰው ሲኖዶሱ ከዚህ ቀደም የተካሂዱት ሲኖዶስ ቅጅ አይደለም ሲሉ የተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ መጠናቀቁ ሲር የዜና ኣገልግሎ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.